Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊሰመጉ መንግሥት ዜጎችን ከቤት ንብረት ማፈናቀሉን እንዲያቆም ጠየቀ

  ሰመጉ መንግሥት ዜጎችን ከቤት ንብረት ማፈናቀሉን እንዲያቆም ጠየቀ

  ቀን:

  የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ከሰሞኑ መንግሥት የወሰደው ቤት የማፍረስ ዕርምጃ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት የጣሰ ነው አለ፡፡

  ዜጎች ለበርካታ ዓመታት ቤት ሠርተውና ትዳር መሥርተው ከሚኖሩበት ከሕዝቡ ጋር በቂ ምክክር ሳይደረግና በተለይም በክረምት ወቅት ቤቶችን ማፍረስ የዜጎችን መጠለያ የማግኘት መብት፣ ሰብዓዊ ክብርና ብሎም የመኖር ዋስትናቸውን ጭምር የሚጻረር ድርጊት ነው በማለት ሰመጉ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ቤት የማፍረስ ሒደት ተቃውሟል፡፡

  ሰመጉ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ‹‹እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ሕገ መንግሥቱንና ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የፈረመቻቸውን የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ስምምነቶች በተለይም የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንን በግልጽ የሚጻረር ነው፤›› በማለት ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

  ሰመጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ክፍላተ ከተሞች ከከተማዋ ማስተር ፕላን ጋር አይጣጣምም በሚል ምክንያት በርካታ ቤቶችን ሕገወጥ ናቸው በማለት፣ በአፍራሽ ግብረ ኃይል የማፍረስ ሒደት ውስጥ መግባቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሆነ ገልጿል፡፡

  በዚህም መሠረት በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ወረገኑ በሚባል ቦታ ላይ ለበርካታ ዓመታት ቤት ሠርተው፣ ትዳር መሥርተው የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰው ቆርቆሮ፣ በርና መስኮታቸው እየተነቃቀለ በአፍራሽ ግብረ ኃይል መወሰዱን ተጎጂዎቹ ለሰመጉ ማስረዳታቸውንና ሰመጉም ባለሙያዎችን ልኮ ጉዳዩን መመልከቱን በመግለጫው አካቷል፡፡

  በተመሳሳይ ሁኔታ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀጣና 01 መንደር 06 በተለምዶ አጠራር ቀርሳና ኮንቶማ ቁጥራቸው 9,617 የሚደርስ አባወራዎች በጠቅላላ 19,624 ነዋሪዎች ከ10 እስከ 15 ዓመት ከኖሩበት ቦታ፣ ‹‹ሕጋዊ አይደላችሁም፡፡ ቦታው ለቄራ አገልግሎት ስለሚፈለግ ልቀቁ፤›› መባላቸውን እንዲሁ ለሰመጉ ማመልከታቸውን መግለጫው ገልጿል፡፡

  በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኢርቱ ተክለሃይማኖት ቀጣና 4፣ ከ250 በላይ አባወራዎች ለበርካታ ዓመታት ከኖሩበት ሥፍራ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ቤታቸውን ከነሙሉ ንብረቱ በአፍራሽ ግብረ ኃይል መፍረሱን በመግለጽ፣ እንዲሁ ለሰመጉ አቤቱታ ማቅረባቸው በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

  ስለሆነም መንግሥት በግጭቱ ለዜጎች ሕይወት መጥፋት፣ አካል መጉደልና ንብረት መውደም ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የዜጎችን አስከፊ መፈናቀል እንዲያስቆም፣ ጉዳዩ በጥንቃቄ ተጠንቶ ካሳ ለሚገባቸው ሁሉ እንዲከፈልና ቤታቸው ለፈረሰባቸውና በየቦታው ተበትነው ለሚገኙ ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ሁሉ ሕጋዊ፣ ሰብዓዊና ቁሳዊ እገዛ፣ እንዲሁም መፍትሔ እንዲሰጧቸው ሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...