Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየተመረጡ ልዩ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ድርጅቶች በባለሥልጣኑ እየደረሰባቸው ያለውን ችግር ተናገሩ

የተመረጡ ልዩ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ድርጅቶች በባለሥልጣኑ እየደረሰባቸው ያለውን ችግር ተናገሩ

ቀን:

  • 263 የልዩ መብት ተጠቃሚዎችና 42 ልዩ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች እንዳሉ ተጠቆመ

በኢንዱስትሪና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ልዩ የጉምሩክ መብት ተጠቃሚዎች በተሰጣቸው ልዩ መብት ለመጠቀም እንዳይችሉ፣ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተለያዩ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች አስፈጻሚዎች ችግር እየተፈጠሩባቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡

ልዩ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ተጠቃሚዎቹ ሰኔ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ባለሥልጣኑ በግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ ለግማሽ ቀን አዘጋጅቶት በነበረ የውይይት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ ከቀረጥ ታሪፍ መቀያየር ጋር ተያይዞ፣ የጉምሩክ አስፈጻሚዎች ከቀረጥ ነፃ መግባት ያለበትን ማቴሪያል አንድ ጊዜ ይቀረጣል ይሏቸዋል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከተመዘገቡት ዝርዝር ዕቃዎች ውስጥ የለም ይባላሉ፡፡ እዚያ ሂዱ፣ እዚህ ሂዱ በማለት ከፍተኛ የሆነ ቢሮክራሲ የገጠማቸው መሆኑንና በተሰጣቸው ልዩ መብት ተጠቅመው መሥራት መቸገራቸውን አስረድተዋል፡፡ በቅጅ ዶክመንት እስከ 30 ቀናት መጠቀም እንደሚቻል ባለሥልጣኑ ቢፈቅድም፣ ላኪዎች የተሟላ ሰነድ ለመላክ እስከ ሁለት ወራት ስለሚፈጁ፣ ያስያዙት ዋስትና እዚያው የሚቀር በመሆኑ ሊሻሻል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የፍተሻና አተረጓጎም በጉምሩክ ከሚታዩ ችግሮች መካከል መሆናቸውን የገለጹት ልዩ ተጠቃሚዎቹ፣ በዚህ ምክንያት ዕቃ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ለበርካታ ቀናት እንደሚቆሙም ገልጸዋል፡፡ ከሚመለከታቸው አካሎች ጋር ተናቦ የመሥራት ሁኔታ እንደሌለም አክለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ፍተሻና ሰነድ ከማግኘት ጋር በተያያዘ ቅድሚያ የመጠቀም መብቶችን በሚመለከት ችግሮች እየገጠሟቸው መሆኑን የሚጠቁሙት ነጋዴዎቹ፣ ኤርፖርት ጉምሩክ የሚያስተናግዳቸው እንደማንኛውም ነጋዴ መሆኑንና የልዩ መብት ተጠቃሚዎች የሚባሉበት የተለየ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ልዩ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ (Authorized Economic Operator) ተብለው የተመረጡት ድርጅቶች ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሏቸው እንዲደረግ የጠየቁት ነጋዴዎቹ፣ ይህ መብት ከተሰጣቸው ጊዜ ጀምሮ እንደ አገር በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የሚለው እንቅስቃሴ ስንት ስንት በመቶ እንደደረሰ እንዲገለጽላቸው ጠይቀዋል፡፡ ‹‹መንግሥት ከያዘው ዕቅድና እኛ ከሠራነው አንፃር ምን ያህል ኢኮኖሚው ተንቀሳቅሷል?›› ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

በተለያዩ የጉምሩክ ጽሕፈት ቤቶች የተመደቡ አስፈጻሚዎች፣ ነጋዴዎቹ የሚያስመጧቸው ዕቃዎችን በሚመለከት እውቀት እንደሌላቸው የገለጹት ነጋዴዎቹ፣ ባለሥልጣኑ በሰው ላይ ከመሥራት ይልቅ ሲስተም ላይ ማተኮሩ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አንዳንድ አስመጪ ነጋዴዎች ደግሞ እንደተናገሩት፣ የተሰጠው ልዩ መብት ቀርቷል በሚል ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው መሆኑንም ነው፡፡ የተመደቡ አስፈጻሚዎች የሚመጡ ዕቃዎችን ስለማያውቋቸው፣ አስመጪው ቢነግራቸውም ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ ለማስለቀቅ እስከ ሁለት ወራት እንደሚፈጅባቸውም የውይይቱ ተካፋዮች ተናግረዋል፡፡

በማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪ የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ላኪና አስመጪዎች የጉምሩክ ልዩ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የገለጹት፣ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የጉምሩክ ሥርዓት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ባልቻ ሲሆኑ፣ ነጋዴዎቹ ያነሷቸው ችግሮችን ሊኖሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ የልዩ መብት ተጠቃሚ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ቁጥር 263 መሆኑን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ በዓለም ደረጃ የጉምሩክ ሥርዓት የሚያገኙበት ሥርዓት መሆኑንና ቀልጣፋ የሆነ የጉምሩክ አገልግሎት ማግኘት ስለሚገባቸውም ዕድሉ መሰጠቱን አክለዋል፡፡

በገቢዎችና ጉምሩክ 11 ሺሕ ፈጻሚ ሠራተኞች መኖራቸውን የጠቆሙት ምክትል ዳይሬክተሩ፣ ነገር ግን ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ላይ በቂ የሆነ ክህሎት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በርካታ የሠራተኞች ፍልሰትም ሌላው ችግር መሆኑን አክለዋል፡፡ ምክንያቱም የተሻለ ክፍያ ስለሚያገኙ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት አቅም የሚፈጠርበት ሁኔታ ላይ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በባለሥልጣኑ ልዩ መብት የሚሰጣቸው 263 ነጋዴዎችና ልዩ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች (የማይፈተሹ) 42 ነጋዴዎች (ድርጅቶች) መሆናቸውም ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...