‹‹በማንነታችሁ በመኩራት፣ ልዩነትን ሳይሆን አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ለተሻለ ዕድገትና ብልፅግና መሥራት ይኖርባችኋል፡፡››
የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪን ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በሰጣቸው ጊዜ የተናገሩት፡፡ ዩኒቨርሲቲው ክብሩን የሰጣቸው ለአገራቸው ዕድገትና ለሰላም መስፈን ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ከግምት በማስገባት እንደሆነ በዕለቱ ተወስቷል፡፡ ፕሬዚዳንት ካጋሜ ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ላስመረቃቸው ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክትም ዲግሪ መያዝ ብቻ በቂ ባለመሆኑ አፍሪካን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት እንዲረባረቡ አሳስበዋል፡፡