ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ሰመራ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚና የፕሬዚዳንት ምርጫ በድጋሚ ለአንድ ወር ተራዘመ፡፡
ምርጫው የተራዘመው ፊፋ በምርጫው ሒደት ላይ እየተነሱ ያሉ ቅሬታዎች ሳይፈቱና መግባባት ላይ ሳይደረስ ምርጫው እንዳይካሄድ ትዕዛዝ በማስተላለፉ መሆኑ ታውቋል፡፡
ካሁን ቀደም በአውሮፓውያን የገና በዓልና በምርጫው ላይ የሚሳተፉ ዕጩዎች ተሳትፎ ላይ በተነሳ ቅሬታ ምክንያት ምርጫው ስለተራዘመ ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወሳል፡፡