Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየተጠረጠሩ ዜጎችን ወደ ሕግ ለማቅረብ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች አመራሮች ዳተኝነት እንዳለባቸው ተገለጸ

የተጠረጠሩ ዜጎችን ወደ ሕግ ለማቅረብ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች አመራሮች ዳተኝነት እንዳለባቸው ተገለጸ

ቀን:

ከወራት በፊት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተቀስቅሶ የበርካቶችን ሕይወት ለቀጠፈውና በመቶ ሺሕ ለሚቆጠሩት መፈናቀል ምክንያት በሆነው ግጭት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ወደ ሕግ ከማቅረብ አኳያ፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አመራሮች ዘንድ ዳተኝነት እንዳለ ተነገረ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትርና የፌዴራልና የክልሎች የጋራ የፀጥታ ምክር ቤት ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ረቡዕ ጥር 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በመኮንኖች ክበብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች እጃቸው አሉባቸው ተብለው የተጠረጠሩና የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ግለሰቦች ወደ ሕግ ከማቅረብ አኳያ፣ በሁለቱም ክልሎች አመራሮች መዘግየቶች ይታያሉ፡፡

በሁለቱ ክልሎች እጃቸው አለበት ተብለው ከተጠረጠሩና የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው 55 ሰዎች መካከል እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉት 15 ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሁለቱ ክልሎች ሲነፃፀሩም በሶማሌ ክልል የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው 29 ዜጎች መካከል 12 የሚሆኑት በክልሉ መንግሥት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስረድተዋል፡፡ በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የእስር መዘዣ ከወጣባቸው 26 ሰዎች መካከል የክልሉ መንግሥት ሦስት ዜጎችን ብቻ በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ከጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ በሁለቱ ክልሎች ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ከኦሮሚያ ክልል በግጭቱ ተሳትፈው ከተያዙት 98 ተጠርጣሪዎች መካከል 54 በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ሲያዙ፣ ቀሪዎቹ በፌዴራል ፖሊስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡  ከሶማሌ ክልል ደግሞ በግጭቱ የተሳተፉ 29 ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ገልጸው፣ አምስቱንም ተጠርጣሪዎች የፌዴራል ፖሊስ ብቻ መያዙን መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አቶ ሲራጅ ግን እንደጠቆሙት፣ ለግጭቱ መባባስ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ለክልሎች አመራሮች ከፌዴራል መንግሥት ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው ግጭት እንደተረጋጋ የጠቆሙት አቶ ሲራጅ፣ ሰኞ ታኅሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት  የሰው ሕይወት ጠፍቷል፡፡ ሕይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥራቸው ስንት እንደሆነና የት አካባቢ ይኖሩ እንደነበር ሚኒስትሩ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

አቶ ሲራጅ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት እንደተናገሩት፣ አገሪቱ ሰላሟ እየተረጋጋ እንደመጣና ለዚህም ሰላም መምጣት የአገሪቱ የፀጥታ ኃይል፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...