Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዝንቅበብዙ ሰዎች ስብስብ የአውሮፕላን ቅርፅ በመሥራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጊነስ ወርልድ ሪኮርድን...

በብዙ ሰዎች ስብስብ የአውሮፕላን ቅርፅ በመሥራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጊነስ ወርልድ ሪኮርድን ይዟል

ቀን:

በብዙ ሰዎች ስብስብ የአውሮፕላን ቅርፅ በመሥራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጊነስ ወርልድ ሪኮርድን ይዟል:: ኤርባስ ኤ 350 ኤክስ ደብሊው ቢ (A 350xWB)
በማስመሰል በሰዎች የተሠራው ቅርፅ በአየር መንገዱ ጊቢ ውስጥ ለእይታ የቀረበ ሲሆን፣ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ተመዝግቧል::

ቀለም ያዘ ልቤ

ከእምነት – ተለይቶ

- Advertisement -

ከፍቅር – ተፋ’ቶ

ሰው ፈርቶ – ሰው ጠልቶ

ቀለም ላይቀበል – ምሎ ተገዝቶ

የተሸሸገውን

የተደበቀውን

አገኘሽውና የልቤ ስፍራውን፣

አንኳኩተሽ – ብትከፍችው

ከፍተሽ – ብታጸጂው

አጽድተሽ – ብታጥኚው

አጥነሽ – ብታጠምቂው፣…

የተሸሸገበት – ምሽጉን ናደና

ፊደል አልቀበል – ማለቱ ቀረና

ለእውቀት ተሸንፎ – ልቤ እጁን ሰጠና፣…

በአንቺው ፍቅር ጠርቶ

በአንቺው እውነት ጸድቶ

በእምነትሽ ተረ’ቶ

‹‹ወውደድ›› ተጻፈበት፡-

ቀለም ያዘ ልቤ፣ ልብሽን አግኝቶ፡፡

ጌትነት እንየው፣ ዕውቅትን ፍለጋ፣ 2004 ዓ.ም.

*****

ቤላሩሳውያንን እርቃናቸውን እንዲሠሩ ያደረገው የፕሬዚዳንታቸው ንግግር

የ61 ዓመቱ የቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሺንኮ በፈጠራ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽንስ ቴክኖሎጂና በፕራይቬታይዜሽን ዙሪያ ንግግር እያደረጉ ነው፡፡ በንግግራቸው መሃል የሦስቱን ዘርፎች ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን እሳቸውም ሆኑ ሕዝባቸው እንደሚስማሙበት እምነታቸውን ገልጸው፣ ለዚህም ሕዝቡ ጠንክሮ እንዲሠራ ‹‹ጌት አንድሬስድ ኤንድ ወርክ›› ብለው ይናገራሉ፡፡

 ፕሬዚዳንቱ ማስተላለፍ የፈለጉት መልዕክት ጠንክራችሁ ሠርታችሁ ራሳችሁን አሳድጉ የሚል እንድምታ ቢኖረውም፣ ቤላሩሳውያኑ ለፕሬዚዳንቱ ንግግር ምላሽ የሰጡት በሥራ ቦታ እርቃናቸውን ሆነው በመሥራት ነው፡፡

ብዙዎችም ሙሉ ለሙሉ አሊያም ሀፍረታቸውን ብቻ ሸፍነው ሲሠሩ መዋላቸውን የሚያሳይ ፎቶ በየማኅበራዊ ድረ ገጾቻቸው ለጥፈዋል፡፡ በዚህም የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ ሙዚቀኞችና ጋዜጠኞች ተሳታፊ መሆናቸውን ዘ ሰን ዘግቧል፡፡

*******

ራሳቸውን ለማጥፋት አቅደው ያልተገበሩ 120 ተማሪዎችን ስም በክንዱ ላይ ያስነቀሰ ሙዚቀኛ

ከብዙ ዓመታት በፊት ነው፡፡ ሮብ ናሽ ለተባለው ካናዳዊ ሙዚቀኛ ከአንድ ትምህርት ቤት የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል፡፡ መልዕክቱም አንዲት ሴት ተማሪ ራሷን እንዳጠፋች፣ ጓደኛዋም ራሷን እንደምታጠፋ ቃል መገባባታቸውን የሚገልጽ የስንብት ኑዛዜ ጽፋለች የሚል ነበር፡፡ ኑዛዜው ላይ ግን የጓደኛዋን ማንነት አልጠቀሰችም፡፡ ናሽ ከዚህን ጊዜ ወዲህ አርፎ አልተኛም፡፡

ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው፣ ናሽ አሁን ላይ ሕፃናትና ታዳጊ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዳያጠፋ፣ በሕይወት ዘመን ብዙ ውጣ ውረዶች እንደሚገጥሙና ይህንንም ተጋፍጦ በማሸነፍ መኖር እንደሚቻል አጽንኦት የሚሰጡና ተማሪዎች ራሳቸውን ከሚያጠፉ ይልቅ ለመልካም ጉዳይ እንዲነሳሱ በሚያደርጉ ንግግሮቹ ታዋቂ ሆኗል፡፡

ናሽ የራሱን የሕይወት ተሞክሮ መሠረት አድርጐ ተማሪዎችን በማራኪ ንግግር ለማነሳሳት ከመሥራቱ ባለፈም፣ 120 ራሳቸውን ለማጥፋት አስበው ከድርጊቱ የተቆጠቡ ተማሪዎችን ስምና ፊርማ በክንዱ ላይ አስነቅሷል፡፡

ራስን ማጥፋት ሁለተኛው የሞት ምክንያት በሆነባት ካናዳ፣ በየትምህርት ቤቶች እየተዘዋወረ አነሳሽ ንግግሮችን የሚያደርገው ናሽ፣ ‹‹ለተማሪዎች ራስን ከማጥፋት መኖር የተሻለ እንደሆነ እየነገርኩ ነበር፡፡ ንግግሬን ስጨርስ አንዲት ተማሪ እያለቀሰች የተጠቀለለ ወረቀት ሰጠችኝ፡፡ ራሷን ለማጥፋት የኑዛዜ ቃሏ ነበር፡፡›› ሲል የገጠመውን ያስታውሳል፡፡ ልጅቷ ከድርጊቱ ከተቆጠቡት መካከል አንዷ ናት፡፡

በዓመት 150 ዝግጅቶችን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በማቅረብ ለሕፃናት ግንዛቤ የሚያስጨብጠው ናሸ፣ ክንዱ ላይ ባለፈው ወር ያስነቀሰውን ራሳቸውን ከማጥፋት የተቆጠቡ ታዳጊዎች ስምና ፊርማ፣ ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ ሁሉ ገልጦ በማሳየት፣ በሕይወት ዘመን ለመጋፈጥ የሚያስቸግሩ ገጠመኞች ቢኖሩም፣ መፍትሔ እንዳላቸውም ይመክራል፡፡

******

ሶሪያዊው ስደተኛ ቁም ሳጥኑን ሲያፀዳ ያገኘውን 150,000 ዩሮ ለፖሊስ አስረከበ

ሶሪያዊው ስደተኛ ሙሃናድ፣ በጀርመን በልግስና ካገኘው መጠለያ ቤት ውስጥ ከነበረ ቁም ሳጥን ያገኘውን 100,000 ዩሮ የያዘ የቁጠባ የባንክ ደብተርና 50 ሺሕ ዩሮ ጥሬ ገንዘብ ለፖሊስ ማስረከቡን ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡

የ25 ዓመቱ ሙሃናድ፣ ገንዘቡን ያገኘው ከመጠለያ ቤቱ ጋር አብሮ የተቸረውን አሮጌ የልብስ ቁም ሳጥን ሲያፀዳ ነው፡፡

‹‹ሁሉም ዩሮዎች አዳዲስ ነበሩ፡፡ ስለሆነም የውሸት መስለውኝ ነበር፡፡ ሆኖም ለማጣራት ባደረኩት ጥረት እውነተኛ መሆናቸውን ተገነዘብኩ›› ሲል ለጀርመኑ ጋዜጣ ቢልድ ተናግሯል፡፡

የገንዘቡን እውነተኛነት እንደተገነዘበ ለጀርመን ፖሊስ በማስረከቡም፣ አድናቆትን አትርፏል፡፡

የጀርመን ፖሊስ ቃል አቀባይ ‹‹ወጣቱ ምሳሌ የሚሆን ተግባር በመፈጸሙ ክብር ይገባዋል፤›› ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ከሶሪያ ጀርመን የተሰደደው ሙሃናድ፣ ያገኘውን ገንዘብ ታማኝ ሆኖ በመመለሱ፣ የገንዘቡ ሦስት በመቶ ይሰጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...