Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

የክረምቱ ዝናብ እየተጠናከረ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ ጎዳናዎችም በዝናብና ጎርፍ መጥለቅለቅ እየተቸገሩ ይገኛሉ፡፡ ነዋሪዎች በቀን ተቀን እንቅስቃሴያቸው ወቅት የተቸገሩበት፣ በተለይ መንገዶችን በእግር ለማቋረጥ የሚንገላቱበት፣ አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞችና ሕፃናት እጅጉን የሚቸገሩባቸው አጋጣሚዎች ዝናብ በጣለ ቁጥር ይከሰታሉ፡፡

አዳዲስ መንገዶች ሳይቀር በጎርፍ ውኃ ተሞልተው ለሰዓታት መንገደኞችን አልፎ አልፎም ተሽከርካሪዎችን የሚያስቸግሩበት አኳኋን ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ለዱሮ ጀምሮ እስካሁን ድረስ እየታየ ያለው መንገዶች ሲገነቡ፣ የውኃ ማስተላለፊያ ሥርዓቶች የሚገነቡባቸው ሥልቶች አጠያያቂ እንዲሆኑ እያደረገ ነው፡፡

ዘመናዊ መንገዶች ቢነጠፉም፣ ዘመናዊነታቸውን የማይመጥን ጎርፍ ይተኛባቸዋል፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ተሸርሽረው ለአደጋ መንስዔ ይሆናሉ፡፡ ይህ የተለመደ፣ የማይቀየር፣ ከዓመት ዓመት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሻገር እንዲኖር መኃላ የተገባለት ሥርዓት እስኪመስል ድረስ ሊለወጥ ያልቻለ ጣብቂያ ሆኗል፡፡

ከዚህ በተጓዳኝ መሻሻል አላሳይ ያለው ነገር ደግሞ ዝንብ ሲመጣ ጠብቆ መንገድ መቆፈርና ለአደጋ ምቹ እንደሆን አደርጎ የመተው ዝንባሌ ነው፡፡ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ እየተረጋ የሚገኘው መንገድ መጓተት ለዚህ ምስክር ነው፡፡ አንዴ በጀት የለም፣ ሌላ ጊዜ አላግባብ ለመንገዱ የተመበደው ገንዘብ ባክኗል ወዘተ እየተባለ በየሬዲዮ ጣቢያው የሚደጠው ሙግት ለመንገዱ ምንም አልፈየደ፡፡ መንገዱ እንደተመነቃቀረና ገደል እንደሆነ ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ ተተወ እንጂ ለውጥ አልመጣም፡፡

ይህ መንገድ ለዕድሳት ተብሎ መቆፈሩን ያላቁ፣ በዚያ መንገድ ካለፉ የቆዩ አሽከርካሪዎች ከሌላ አቅጣጫ በመጡበተ ፍጥነት ለአደጋ ሲጋለጡ እየታየ ነው፡፡ መንገዱ ዕድሳት ላይ ስለመሆኑ ወይም ለዚያ ተብሎ ስለመቆፈሩና በሥራ ላይ ስለመሆኑ የሚገልጹ ምንም ዓይነት የመንገድ ምልክቶች አለመቀመጣቸው ደግሞ መቼም የማንሻሻል፣ ስለ አደጋ ዘምሮ አዳሪ እንጂ ዘምኖ ኗሪ ለመሆን እንዳልተፈጠርን አስመስሎናል፡፡

በሌሊት ያውም በዝናብ ወቅት፣ ለዕይታ አዳጋች በሆነ የአየር ፀባይ ወቅት የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ከአደጋ ለመታደግ ቀላሉን ነገር ማከናወን ለቀባሪው ማርዳት ይሆናል፡፡ ከዚህ ባሻገር በልደታ አካባቢ ከሦስት ክረምት በላይ በውኃ ተሞልቶ ለክፉ አደጋ የሚጣራውን ጉድጓፍ የሚመለከው ማጣቱም አስገራሚ ብቻም ሳይሆን፣ በየደረጃው ያሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋረድ ኃላፊዎችን ቸልተኛነት የሚያስብቅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ አሰቃቂ አደጋ ደርሶ ዋይታ ከማብዛት ቀድሞ መዘጋጀት ጠቃሚ ነውና አስተዳደሩ፣ ደንብ አስከባሪዎችና ሕዝቡ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን በቸልታ ባይመለከቱ መልካም ይመስለኛል፡፡

(አለልኝ አበጋዝ፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...