አስፈላጊ ግብዓቶች
½ ኪሎ ዓሳ ተቀቅሎ የተፈጨ
3 እንቁላል አስኳሉና ዞፉ የተለየ
3 የሾርባ ማንኪያ የፉርኖ ዱቄት
1 የሾርባ ማንኪያ ፐርሰሜሎ
ትንሽ ነጭ ሽንኩርት፣ የተከተፈ ጨው ቁንዶ በርበሬ
አሠራር
- ዓሳ፣ የእንቁላል አስኳል፣ ዱቄት፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ፐርሰሜሎ በጉድጓዳ ሳህን ማደባለቅ፡፡
- የተመታ የእንቁላል ዞፍ በተራ ቁጥር 1 ከተዘጋጀው ድብልቅ ጋር ማዋሀድ፡፡
- በመጥበሻ ላይ በፈላ ዘይት የዓሳና የእንቁላል ድብልቁን በማንኪያ እያወጡ ጨምሮ እያገላበጡ መጥበስ፡፡
አራት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)