Monday, January 13, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኤሌክትሪክ መቆራረጥ በአዲስ አበባ ለንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንቅፋት መሆኑ ተገለጸ

የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በአዲስ አበባ ለንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንቅፋት መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

spot_img

አዲስ አበባ ከተማ በሦስት አቅጣጫ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ታገኛለች፡፡ የመጀመሪያው በደቡብ በኩል ከከርሰ ምድር፣ በምሥራቅ በኩል ከለገዳዲና ድሬ ግድቦችና በምዕራብ በኩል ከገፈርሳ ግድብ ውኃ ታገኛለች፡፡ በሰሜን በኩል የውኃ ምንጭ ባለመኖሩ አነስተኛ ጉድጓድ በመቆፈር ውኃ ለማቅረብ እየተሞከረ ይገኛል፡፡

ነገር ግን በተለይ በተያዘው ሰኔ ወር በከፍተኛ ደረጃ የኃይል መቆራረጥ እያጋጠመ በመሆኑ፣ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ያመረተውን ውኃ ለተጠቃሚዎች ማድረስ እንዳልቻለ ገልጿል፡፡

በዚህም መኖሪያ ቤቶች፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማት (የጤናና የትምህርት ተቋማት) እና ንግድ ቤቶች የንፁህ ውኃ አቅርቦት እጥረት እየገጠማቸው መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ በቀን 608 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ ያመርታል፡፡ ይህም የመጠጥ ውኃ ሽፋኑን 92 በመቶ አድርሶታል፡፡

‹‹ይህን ውኃ ለተጠቃሚው በማድረስ በኩል በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያጋጠመ ያለው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንቅፋት ሆኗል፤››  በማለት የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸዋል፡፡

ከንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የጥራት ጉዳይም እየተነሳ ይገኛል፡፡ በተለይ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ከተከሰተው አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ጋር ውኃ ተፈልቶ እንዲጠጣ ከሚመክረው ምክር ጋር የውኃ ጥራት ጉዳይ ጥያቄ እየተነሳበት ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሒደት መሪ ወ/ሮ እፀገነት ተስፋዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ የሚያመርተው  ውኃ ዓለም አቀፍ የውኃ መስፈርቶችን ያሟላ ነው፡፡

ወ/ሮ እፀገነት እንደሚሉት፣ መሥሪያ ቤታቸው የሚያመርተው ውኃ ከጅምሩ በክሎሪን ታክሞ የሚሰራጭ ነው፡፡ ውኃው ከተሰራጨ በኋላ ለተጠቃሚዎች ሲደርስ በብርጭቆ ውስጥ ከ0.3 እስከ 0.6 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ክሎሪን አለው፡፡ ይህ በመሆኑም ውኃው በሚጓጓዝበት ወቅት ተዋስያን ቢገቡበት እንኳ የመግደል ኃይል አለው፡፡

‹‹ነገር ግን የውኃ ቧንቧ ያለባቸው ቦታዎች ንፁህ ካልሆኑ፣ የዛጉ የውኃ ቱቦዎች ካሉ ችግር ሊኖር ይችላል፡፡ በተለይ የውኃ ጣዕም፣ ሽታና ከለር የተለወጠ ከሆነ ኅብረተሰቡ ለሚመለከተው አካል መጠቆም ይኖርበታል፤›› በማለት ወ/ሮ እፀገነት አስጠንቅቀዋል፡፡

በከተማው የተከሰተው የውኃ አቅርቦት ችግር ለግልና ለአካባቢ ንፅህና ጠንቅ እየፈጠረ በመሆኑ፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጡን ማስቀረት ወሳኝ እንደሆነ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት እየጣለ የሚገኘው ከባድ ዝናብ፣ ንፋስና መብረቅ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡

በተለይ በአዲስ አበባ የሚገኙት የኤሌክትሪክ ማሰራጫዎችና ማከፋፈያዎች ዕርጅና የተጫናቸው በመሆናቸው፣ ከአገልግሎት ውጪ እየሆኑ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይኼንን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት፣ ለውኃ ማሰራጫዎች የተለየ መስመር በመዘርጋት ላይ ቢሆንም፣ አዳዲስ መስመሮች ሳይቀር ለዚህ ችግር እየተዳረጉ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ታፈረ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሰሞኑን በሚጥለው ከባድ ዝናብና ነፋስ በተለይ በአዲስ አበባ የሚገኙት አሮጌ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡

‹‹ይኼንን ችግር ለመፍታት ችግር ሲፈጠር በፍጥነት የሚጠግን ቡድን ተቋቁሟል፡፡ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የውኃ መስመሮች የራሳቸው የኃይል መስመር እንዲኖራቸው ይደረጋል፤›› በማለት አቶ ገብረ እግዚአብሔር ገልጸዋል፡፡

ይኼንን ግንባታ ለማካሄድ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 20 ሚሊዮን ብር ለመክፈል መስማማቱን አቶ ገብረ እግዚአብሔር አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤተሰብ ኃላፊነት የተሸከሙ ሕፃናት

በመማሪያና በለጋ ዕድሜያቸው የቤተሰብ ኃላፊነት ተጭኖባቸው ከትምህርት ገበታ ርቀው...

አሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት ትንቅንቅ ማብቂያው መቼ ይሆን?

በናኦድ አባተ በአውሮፓውያን ዘንድ በስፋት የሚታወቀው “A House Divided Against...

መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ላይ ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል!

በአገር ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከሚጠይቁ ገቢ ምርቶች መካከል...

ስለመነጋገር እስኪ እንነጋገር

በገነት ዓለሙ ዴሞክራሲ መብቶችና ነፃነቶች የሚሠሩበት የሕዝብ አስተዳደር ነው፡፡ ሰብዓዊ...