Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአፍላ ወጣትነት እርግዝናን ለመታደግ

የአፍላ ወጣትነት እርግዝናን ለመታደግ

ቀን:

በአፍላ ዕድሜ ማርገዝ ላረገዘችው፣ ለሕፃኑም ሆነ ለቤተሰብ ችግርን አስከትሎ የሚመጣ ነው፡፡ በአፍላ ዕድሜ ማለትም የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚያስቀምጠው ከ15 እስከ 19 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ አፍላዎች እርግዝና በውስብስብ ችግሮች የታጀበና ለሕፃኑም ሞት ምክንያት ነው፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2014 ያወጣው ሪፖርትም ከ15 እስከ 19 የዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ሴቶች ሁለተኛው የሞት ምክንያት በዚሁ ዕድሜ ማርገዛቸው ነው፡፡ በየዓመቱም ሦስት ሚሊዮን ያህሉ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ውርጃ ያከናውናሉ፡፡

ከአፍላዎች የሚወለዱ ሕፃናት ሞትም ከ20 እስከ 24 የዕድሜ ክልል ውስጥ ካሉት እናቶች ከሚወለዱት እጅግ የበለጠ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እ.ኤ.አ. ከ1990ዎቹ ወዲህ የሴቶች በአፍላ ዕድሜ የመውለድ ሁኔታ ቢቀንስም፣ 11 በመቶ የሚሆኑት ውልደቶች በአፍላ ዕድሜ የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ ከዚህ 95 በመቶ ያህሉ ደግሞ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ይከሰታል፡፡

የ2014ቱ የድርጅቱ ቆጠራ የሚያሳየውም፣ በዓለም በአንድ ሺሕ የአፍላዎች እርግዝና ከአንድ እስከ 299 ልጆች መወለዳቸውንና ከእነዚህም አብዛኞቹ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች መሆናቸውን ነው፡፡ የአፍላ እርግዝናም ለእናቶችና ለሕፃናት ሞት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ለጤና መጓደልና ለድህነትም የሚዳርግ ነው፡፡

ከጥር 1 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ‹‹ለጤናማ እናትነት ይብቃ ማርገዝ በአፍላ ወጣትነት›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የእናትነት ወር አስመልክቶ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጥር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫም፣ በኢትዮጵያ በአፍላ ዕድሜ የሚያረግዙ 13 በመቶ መድረሳቸውን አስታውቋል፡፡

የሚኒስትር ዴኤታው አማካሪ አቶ ግርማ አሸናፊ እንደሚሉት፣ በዓመት ከሚረገዙት ሕፃናት መካከልም 13 በመቶው ከ15 እስከ 17 የዕድሜ ክልል ካሉ አፍላ ወጣቶች የሚፀነሱ ናቸው፡፡  

ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ከወሊድ ጋር ተያይዞ ለሚከሰተው ሞትና ሕመም በአፍላነት ዕድሜ የሚከሰት እርግዝናና ወሊድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አቶ ግርማ የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2016 ያወጣውን መረጃ ጠቅሰው እንደገለጹትም፣ በዓመቱ በዓለም 303 ሺህ ያህል እናቶች ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ ሞተዋል።

ከአፍላዎች የሚወለዱ ሕፃናት ለተለያዩ የጤና ችግሮች የሚጋለጡ ሲሆን፣ እናቶችም ለደም ግፊትና ማነስ፣ ጊዚውን ላልጠበቀ ምጥ እንዲሁም ለፊስቱላ ይጋለጣሉ።

ለጤናማ እናትነት ትኩረት ሰጥታ መንቀሳቀስ ከጀመረች አሥራ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረችው ኢትዮጵያ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ሞትና  ሕመም ለመከላከል የአፍላ ወጣትነት እርግዝናን መታደግ የሚያስችል መሪ ዕቅድ አዘጋጅታለች፡፡

የአፍላነት እርግዝናን ለመከላከል ያስችላል፣ የሚከሰተውን ሞትና ሕመምም ይታደጋል የተባለውን ዕቅድ ለመተግበርም መርሐ ግብር መነደፉን አቶ ግርማ ተናግረዋል።

መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትም ዕቅዱን የሚተገብሩት ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀደም  የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በጤና ተቋማት ውስጥ  ብቻ ያተኮረ በመሆኑ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት ባለመቻሉም የዘንድሮው የእናቶች ቀን አከባበር ከፌዴራል እስከ ክልል ድረስ የግንዛቤ ማስጨበጫ በመፍጠር  የሚከናወን ይሆናል፡፡

የጤናማ እናቶች ቀን የሚከበረው በዓለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ 12ኛ ጊዜ ነው፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...