Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናፓርላማው በኤርትራ ላይ የሚሰጠውን መመርያ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን መከላከያ ሚኒስትሩ ገለጹ

  ፓርላማው በኤርትራ ላይ የሚሰጠውን መመርያ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን መከላከያ ሚኒስትሩ ገለጹ

  ቀን:

  የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ ፓርላማው በቀጣይ መሆን አለበት ብሎ የሚሰጠውን መመርያ ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም የአገር መከላከያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፓርላማ አባላት አረጋገጡ፡፡

  ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሣ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፓርላማው ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ መንግሥት ለሻዕቢያ መንግሥት ትንኮሳ ተመጣጣኝና አስተማሪ ዕርምጃ እንዲወሰድ ባስቀመጠው ውሳኔ መሠረት ከቅርብ ቀን በፊት የመከላከያ ሠራዊት የሻዕቢያን ተደጋጋሚ ትንኮሳ ተከትሎ አስፈላጊውን ተመጣጣኝ ዕርምጃ ወስዷል፡፡

  ‹‹ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን በወሰደው ዕርምጃ ሠራዊታችን በፈለገው ጊዜ አስፈላጊውን ዕርምጃ መውሰድ የሚችል ብቃቱም ሆነ አቅሙ እንዳለው አረጋግጧል፤›› ብለዋል፡፡

  በተወሰደው ዕርምጃም የሻዕቢያ መንግሥት በራሱ ጭንቀት ውስጥ እንዲገባና በውስጣዊ ሁኔታው እንዲጠመድ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡

  በመሆኑም ሠራዊቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በቅርቡ በሚገባ ማሳካቱን በቀጣይም ሻዕቢያ ከዚህ ድርጊቱ የማይቆጠብ ከሆነ ሠራዊቱ ተገቢና አስተማሪ የሆነ ዕርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

  የምክር ቤቱ የመከላከያና ደኅንነት ጉዳዮች ልዩ ኮሚቴ ለሚኒስትሩ ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል በኤርትራ ላይ የሚወሰደው ተመጣጣኝ ዕርምጃ እስከ ምን ድረስ ነው የሚቀጥለው? ለምን የማያዳግም ዕርምጃ አይወሰድም? የሚሉ ጥያቄዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

  ዶ/ር አደሃነ ኃይሌ (የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትርና የምክር ቤቱ አባል) የኤርትራ መንግሥት ወይም የሻዕቢያ መንግሥት በኤርትራ ስለመኖሩ እንደማያምኑ ይልቁኑ በኤርትራ የሚገኘው የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂና ቡድናቸው መንግሥት እንደሆነ ከገለጹ በኋላ ‹‹ተመጣጣኝ ዕርምጃ የሚባለው ነገር ማቆም አለበት፡፡ የኢሳያስ መንግሥትን ከኤርትራ ሕዝብ ጀርባና ከራሳችን ጫንቃ ላይ ማውረድ አለብን፡፡ ይህንን ማድረግም ተመጣጣኝ ዕርምጃ ነው፤›› ሲሉ ሐሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

  ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ ተመጣጣኝ ዕርምጃ የመንግሥት ምርጫ መሆኑን፣ ይህ የሆነበት ምክንያትም የኢትዮጵያን ሕዝብ ከድኅነት የማውጣት ተልዕኮ እንዳይደናቀፍ ሲባል የተመረጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  ይህ ምርጫም ኢትዮጵያን አስተማማኝ ሰላም ያላት አገር እንዳረጋት ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ላይ ከእኛ ጋር ሳይመከር የሚፈጸም ሥራ የለም፤›› ብለዋል፡፡

  የአገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል ጦርነት ባለመመረጡም ሕዝቦች ተጠቃሚ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡

  ‹‹በቀጣይ በኤርትራ ባለው መንግሥት ላይ መፈጸም ያለበትን መንግሥትና ይህ ምክር ቤት በሚሰጡት መመርያ መሠረት ለመፈጸም ዝግጁ ነን፤›› በማለት የምክር ቤቱ አባል ዶ/ር አድሃነ የሰጡትን አስተያየት በአስተያየትነት እንደሚቀበሉት አቶ ሲራጅ ገልጸዋል፡፡

  በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የመጡት የሙርሌ ጐሳዎች የፈጸሙትን ግድያና ዘረፋ በተመለከተ መከላከያ ሠራዊቱ ጥንቃቄ የተሞላበት ሰላማዊ አማራጭን መከተሉን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ይህ የሆነበት ምክንያትም ኃይል መጠቀም የተሰረቁ ሕፃናትንና ሌሎች ንብረቶችን ለማስመለስ አማራጭ ባለመሆኑ ነው፤›› ብለዋል፡፡ መከላከያ ሠራዊቱ ባለው መረጃ መሠረት 103 ሕፃናት ተሰርቀው የነበረ መሆኑን በእስካሁኑ ጥረት 91 መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡

  የተቀሩትን እንዲሁም ከዚህ ቀደምም በሙርሌዎች የተሰረቁ ሕፃናትን ለማስመለስ እየተጣረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

  የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጐሳ አባላት በጋምቤላ ክልል በቅርቡ የፈጸሙት ጥቃት በጉዳት ደረጃ ትልቅ እንደነበር በመግለጽ መከላከያ ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት ወንጀል የፈጸሙትን የሙርሌ ጐሳ አባላት ሙሉ ማንነት መያዙን ሕፃናቱንና የተዘረፉ ከብቶች ከተመለሱ በኋላ ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በመሆን በሕግ እንዲጠየቁ እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡

  መከላከያ ሠራዊቱ በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን ዳርፉርና በአብዬ ዞን በጠቅላላው 12,500 ሰላም አስከባሪ ማሳለፉን በዚህም በሁሉም ተልዕኮዎች ስኬት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

  በአሁኑ ወቅት በሶማሊያ 4,600 በላይ የኮንቲንጆንት ሠራዊት አባላትና ከ20 በላይ የኃይል ማዘዣ አባላት መኮንኖች መሰማራታቸውን ጠቁመው፣ በቅርቡ በሃልጌ በኢትዮጵያ ሠራዊት ካምፕ ላይ አልሸባብ ለመቃጣት የሞከረውን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የመጣውን ጦር በመደምሰስ አልሸባብ ላይ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ የላቀ ኪሳራ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

  ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ በኢትዮጵያ በኩል ስለደረሱት ጉዳቶች መረጃ አልቀረበም፡፡ ከምክር ቤቱ አባላትም ጥያቄ አልቀረበም፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...