Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያና ኬንያ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ስምምነት ፈረሙ

ኢትዮጵያና ኬንያ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ስምምነት ፈረሙ

ቀን:

ኢትዮጵያና ኬንያ ከላሙ የወደብ ከተማ እስከ አዲስ አበባ ድረስ የሚዘረጋ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት ስምምነት ፈረሙ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የሁለቱ አገሮች መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ናቸው፡፡ ስምምነቱ የተደረገው ኬንያ ቀደም ብላ በተመሳሳይ ከኡጋንዳ ጋር አድርጋው የነበረውን ስምምነት ማቋረጧን ካስታወቀች ከአንድ ወር በኋላ መሆኑም ተዘግቧል፡፡

በኬንያ ርዕሰ ከተማ ናይሮቢ ይፋዊ የሦስት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ጋር በዘርፉ የተለያዩ ጉዳዮች ላይም ስምምነት አድርገዋል፡፡

ከስምምነታቸውም ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው የነዳጅ መስመር ዝርጋታው ሲሆን፣ መስመሩ በሁለት አቅጣጫዎች የሚዘረጋ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በመጪው ዓመት ታኅሳስ ወር እንደሚጀመር ስምምነት የተደረሰበት መስመር ከናኩሩ-ኢሲዮሎ-ሞያሌ-ሐዋሳ አድርጎ አዲስ አበባ የሚደርሰው መስመር አንደኛው ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ከላሙ-ኢሲዮሎ-ሐዋሳ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡ የነዳጅ መስመሩ ዝርጋታ ቀደም ባሉት ዓመታት የላሙ ወደብን ከቀጣናው አገሮች ጋር በማስተሳሰር በጋራ የመሠረተ ልማት ግንባታን ለማከናወን ስምምነት የተደረገበት የ15 ቢሊዮን ዶላር አካል እንደሆነም የሁለቱ አገሮች መሪዎች በናይሮቢ የኬንያ ቤተ መንግሥት በተደረገው ሥነ ሥርዓት ወቅት አስታውቀዋል፡፡

በተመሳሳይም ሁለቱ አገሮች እ.ኤ.አ. በ2012 የጋራ ምድር ባቡር ኮሚሽንና የፕሮጀክት አስተባባሪ ኮሚቴ ለማቋቋም ባደረጉት ስምምነት መሠረት ወደ ትግበራ መግባት የሚያስችላቸውንም ስምምነት መፈራረማቸው ከናይሮቢ የሚወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም የሁለቱ መንግሥታት ተወካዮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት መፈራረማቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በነዳጅና በተፈጥሮ ጋዝ፣ በስፖርት፣ በጤና፣ በድንበር ዘለል የእንስሳት ጤና ትብብሮችና በትምህርት ዘርፎች ላይ የተደረጉት ስምምነቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...