Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአተት ሕክምና 24 የሕክምና ጣቢያዎች ተለዩ

ለአተት ሕክምና 24 የሕክምና ጣቢያዎች ተለዩ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተስፋፋ ለመጣው አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ሕሙማን ሕክምና የሚሰጡ 24 የሕክምና ጣቢያዎች መመረጣቸውን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በአሥሩም ክፍለ ከተሞች የሚገኙት ጤና ጣቢያዎቹ ለሕሙማኑ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችሉ ግብዓቶች የተሟሉላቸው መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በኦሮሞ ባህል ማዕከል በሰጠው መግለጫ እንዳሳወቀው፣ የአተት ምልክቶች የታዩባቸው ግለሰቦች በአፋጣኝ ወደእነዚህ የጤና ጣቢያዎች ማምራት አለባቸው፡፡

በአገሪቱ የተከሰተውን ኤልኒኖና ላኒና ተከትሎ በመጣው ሙቀትና ንጽሕና መጓደል ሳቢያ አተት ከየካቲት ወር ጀምሮ በአገሪቱ በተለይም በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የታየ ሲሆን፣ ከሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ሕሙማን ተገኝተዋል፡፡ አተት የያዛቸው ግለሰቦች ሁለት ብቻ የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በአጠቃላይ ወደ 25 ታማሚዎች ተመዝግበዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አህመድ ኢማኖ እንደተናገሩት፣ የበሽታው የሥርጭት መጠን እየተስፋፋ በመምጣቱ ሕዝቡ ጥንቃቄ ሊወስድ ይገባል፡፡ ምክንያቱም እንደ አዲስ አበባ ባሉ የተጨናነቀ የኑሮ ሁኔታ ባለባቸው ከተሞች አተት በቀላሉ ይሠራጫል፡፡ በዓለም የጤና ድርጀት መረጃ መሠረት በአተት ምክንያት የሰውነትን ፈሳሽ ንጥረ ነገር በፍጥነት ስለሚወጣ በሦስት ሰዓት ውስጥ ሕክምና ካልተገኘ የታማሚ ሕይወት ሊያልፍ ይችላል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም በአተት ሳቢያ የሞቱ አሉ ቢባልም ዳይሬክተሩ እስካሁን በበሽታው ሕይወቱ ያለፈ ሰው አለመኖሩንና በላብራቶሪ ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህ ቀደም በ2000 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ አተት መከሰቱና የሞቱ ሰዎችም እንደበሩ ይታወሳል፡፡ ዳይሬክተሩ አሁን ከቀደመው ጊዜ በተሻለ ቅድመ ዝግጅቶች በመደረጋቸው በሽታውን በአጭር ጊዜ ለማቆም እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ ለአተት ሕክምና ከሚሰጡት 24 ጤና ጣቢያዎች ውጪ ወዳሉ የሕክምና መስጫዎች ሕሙማን ሲሄዱ፣ ተቋማቱ የሚያስፈልገውን ሕክምና ሰጥተው ከ24 ጣቢያዎች ወደ አንዱ መላክ እንዳለባቸውም አክለዋል፡፡ ‹‹ከአተት ሕሙማን ምልክቶቹን የሚያሳዩት 20  በመቶው ብቻ ሲሆኑ፣ የተቀሩት ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ፤›› በማለትም ከፍተኛ ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

አተት ከግልና አካባቢ ንፅሕና ጉድለት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ የምግብና የመጠጥ ንፅሕናን መጠበቅ፣ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ፣ በምግብ ዝግጅትና አቅርቦት ወቅት እጅን በሚገባ በሳሙና መታጠብና ከሕሙማኑ ጋር ከሚደረግ ንክኪ ራስን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ናቸው፡፡ ተቅማጥ፣ ትውከት፣ የአፍ መድረቅ፣ የዓይን መሰርጎድ፣ የእግር ቁርጥማት፣ ድካምና መሰል ምልክቶች ሲታዩ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ያስፈልጋል፡፡ ሕክምና እስኪገኝ ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽን ለመተካት ኦአርኤስ ወይም አንድ ሊትር ውኃ በአንድ የሻይ ማንኪያ ጨውና በስድስት የሻይ ማንኪያ ስኳር በጥብጦ መጠጣት ይመከራል፡፡ ስለበሽታው መረጃ ለማግኘት በ8335 ወይም 952 ነፃ የስልክ መስመር መደወል እንዲሁም በሽታው ከተከሰተ በ939 ደውሎ አንቡላንስ መጥራት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...