Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​‹‹የስኳር መድኃኒት አግኝቻለሁ›› የሚሉት ዶክተርና የባለድርሻዎች አስተያየት

​​​​​​​‹‹የስኳር መድኃኒት አግኝቻለሁ›› የሚሉት ዶክተርና የባለድርሻዎች አስተያየት

ቀን:

ግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ‹‹ያገኘሁት መድኃኒት ሁለቱንም ዓይነት የስኳር ሕመሞች ይፈውሳል›› በሚል ርዕስ ዶ/ር ፋንታሁን አበበ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ተከትሎ በርካቶች ለዝግጅት ክፍሉ የተለያዩ አስተያየቶች መሰንዘራቸው ይታወሳል፡፡ ከእነዚህ መካከል የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት ይገኙበታል፡፡ ዶ/ር ፋንታሁንም አሉኝ የሚሏቸውን ማስረጃዎች ያቀርባሉ፡፡ አስተያየቶቹንና ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ዶ/ር ፋንታሁን አበበ በ2004 ዓ.ም. ዕውቅና ካለው ከአትላስ ኮሌጅ ኦፍ ኸልዝ ሳይንስ በጥርስ ሕክምና በዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ እንዲሁም ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ1996 ዓ.ም. በአካውንቲንግ ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡ የምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ጁኒየር ዴንታል ሰርጅን ሆነው እንዲያገለግሉ በ2005 ዓ.ም. የሙያ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ዶ/ር ፋንታሁን አገኘሁ በሚሉት የስኳር መድኃኒት ላይ አስተያየት የሰጡ የሕክምና ባለሙያዎች ግኝቱ መድኃኒት ለመባል ሳይንሳዊ ማስረጃዎች እንደሌሉት፣ እንዲሁም በተለያዩ ሳይንሳዊ ሙከራዎች ማለፍ ሲኖርበት ይህ ሳይሆን መድኃኒት ነው ማለት እንደማይቻል ይከራከራሉ፡፡ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣንም ለግኝቱ ዕውቅና አለመስጠቱን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ዶ/ር ፋንታሁን ያቀረቡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ለምግብ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹‹ነን ካርቦኔትድ ኮፊ ፎር ሜድሲን›› በሚል ግኝቱ መርዛማ (አኪውት ቶክሲሲሲ) አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ዶክመንት በ2005 ዓ.ም. አግኝተዋል፡፡ ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት ደግሞ ‹‹ቢኤፍኤን ቡና ዘይት ማምረት ለመድኃኒትነት›› በሚል ለንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት የንግድ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የሚፈቅድ ማስረጃ በ2008 ዓ.ም. ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ መሠረትም ከንግድ ሚኒስቴር በ18/9/2008 ዓ.ም. ቢኤፍኤን ቡና ለመድኃኒት ማምረቻ የሚል የንግድ ስያሜ ተመዝግበው እንዲሰሠሩ ፈቅዶላቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሪፖርተር ለማጣራት ባደረገው ሙከራ ዶ/ር ፋንታሁን በ2006 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጽሕፈት ቤት አገኘሁ ከሚሉት መድኃኒት ጋር በተያያዘ ዕውቅና ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውን ነገር ግን ተጨማሪ መረጃዎችን በሁለት ወር ገደብ ውስጥ እንዲያቀርቡ ተጠይቀው አለማቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም የዓለም አእምሮ ንብረት ድርጅት ከኮሪያ አእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ ድርጅትና ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር በ2004 ዓ.ም. በተዘጋጀው የፈጠራ ውድድር ላይ ከተሳተፉት መካከል ምርጥ 15 ውስጥ መግባታቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት አግኝተዋል፡፡

ግኝታቸውንም በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተግባር ለማሳየትም ቦታ ጠይቀው ፈቃድ ማግኘታቸውን ፕሬዚዳንቱ የበላይ ጠባቂ ከሆኑት የጥሩ ዘር ኢትዮጵያ ፎር አፍሪካ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ማሞ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አቤል የሻነው እንደተናገሩት ዶ/ር ፋንታሁን በተቋሙ የማይክሮ ባዮሎጂ ምርመራ አስደርገው ኖርማል የሚል ውጤት ተሰጥቷቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ከዶ/ር ፋንታሁን ጋር ቀርቦ ለመነጋገር መወሰኑን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...