Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

ከሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ዋቢ ሸበሌ አካባቢ የደረሰው አደጋ አስገርሞኛል፡፡ አንድ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪ መንገድ የሚያቋርጠውን እግረኛ መግጨቱና ከገጨም በኋላ የነበረውን ሁኔታ እንደው ቢያስተምረን ብዬ ነው መጻፌ፡፡

የክረምቱ ዝናብ እያካፋ እግረኞችንም በከባዱ የመጣውን ዝናብ ለመሸሽ መጠለያ ፍለጋ፣ ታክሲ የሚሳፈሩም ወደ ታክሲ ለመግባት ይራወጣሉ፡፡ መኪኖችም ከላይ ወደታች ይርመሰመሳሉ፡፡ በዚህ መሐል ከኮሜርስ ወደ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት አቅጣጫ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ሜክሲኮ አደባባይ ላይ ተኮልኩለዋል፡፡ የትራፊክ እንቅስቃሴው ወደ መጨናነቁ ያደላ ቢመስልም፣ ቆመው እግረኞችን ለማሳለፍ የሚጥሩ አሽከርካሪዎች ግን አልታጡም፡፡

በቆሙና በሚንቀሳቀሱ መኪኖች መሐል እየተሽሎከሎኩ በማለፍ ዝና ያተረፉት፣ አንዳንዴም ከአቅም በላይ ሙዚቃ እያስደለቁ የሚነጉዱት ሞተር ብስክሌተኞች አደጋ በማድረስም፣ ለአደጋ በመጋለጥም እየባሰባቸው ይገኛል፡፡ በሜክሲኮ አደባባይ የታዘብነውም ከዚህ ዓይነቱ ድርጊት የሚመደብ ነው፡፡

ሞተረኛው መንገድ የሚያቋርጠውን እግረኛ አላስተዋለም፡፡ ምንም እንኳ ተሽከርካሪዎች ቆመው እግረኞችን በማሳለፍ ላይ ቢሆኑም፣ ይህ ሞተረኛ ግን ለዚህ ተግባር ጊዜ የነበረው አይመስልም፡፡ ይህ በመሆኑም በቅጽበት መንገድ በሚያቋርጠው እግረኛ ላይ ጉዳት ከማድረስ አልፎ አሽከርካሪውም ለጉዳት የተዳረገ ይመስለኛል፡፡ አወዳደቁ ለጉዳት በሚዳርገው አኳኋን ነበር፡፡ አለባበሱም ቢሆን አናቱ ላይ ካጠለቀው የራስ ቅል ጉዳት መከላከያ በቀር፣ ከአደጋ ለከላከል የሚያስችለው አልነበረም፡፡ ለቅድመ ጥንቃቄው እግረኛ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ባያስቀር እንኳ አሽከርካሪዎቹን ሊረዳ የሚችል የእግር፣ የእጅም ሆነ የሌላ ሰውነት ጉዳትን የሚቀንስ መከላከያ ቢለብሱ ጥቅሙ ለራስ ነው፡፡

በሜክሲኮ አካባቢ ያየነው አደጋ በእርግጥ ከአሽከርካሪው ይልቅ መንገደኛውን ለበለጠ ጉዳት የዳረገ ነበር፡፡ ይሁንና አደጋ የደረሰበት መንገደኛ ዕርዳታ እንዲያገኝ የተደረገበት መንገድ ግን አሳዛኝ ነበር፡፡ በሰዎች ከመከበብ በቀር አፋጣኝ ሕክምና ማግኘት የሚችልበትን ብልኃት ያስገኘ አልነበረም፡፡ ወደ ኋላ ላይ እንደተመለከትነው ገጭው ሞተረኛ ታክሲ ተኮናትሮ ይሁን ወይም ሌሎች ተጋግዘው ያደረጉት ባላውቅም ተጎጂው መንገደኛ እንደምንም ወደ ሕክምና ተቋም የተወሰደ ይመስለኛል፡፡

በየጊዜው በመንገድ አደጋ ምክንያት እየደረሰ ያለው አደጋ ለሺዎች ሕይወት መጥፋት፣ ለሺዎች አካል መጉደል፣ ለሚሊዮኖች ለሚቆጠር ሀብትና ንብረት መውደም ምክንያት ከሆነና ኢትዮጵያንም በመንገድ አደጋ ምክንያት አደገኛ ከተባሉ ዋና ዋና አገሮች ተርታ እንድትመደብ ዳርጓታል፡፡ በኢትዮጵያ በእያንዳንዱ አሥር ሺሕ ተሽከርካሪ ምክንያት በየዓመቱ 64 ሰዎች ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡ ይህ መሆኑም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ገዳይ ተሽከርካሪዎች ከተንሰራፉባቸው አገሮች ስምንተኛዋ ቀንደኛ አገር ተብላ እንድትፈረጅ ምክንያት ሆነዋል በማለት ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን ዘገባ አንብቤያለሁ፡፡

በአገሪቱ የሚሽከረከሩት መኪኖች ብዛት፣ የሚደርሰው ጉዳትና አደጋ እጅጉን ያልተጣጣሙ ሆነው መገኘታቸውንም ይኸው ጋዜጣ የዓለም ባንክን ጠቅሶ ጽፏል፡፡ ምንም እንኳ ከሌሎች ከተሞች አኳያ በአዲስ አበባ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ቁጥር አነስተኛ ነው ቢባልም፣ እያደገ የመጣው የትራፊክ መጨናነቅ በከተማው የትራፊክ ፍሰት ማኔጅመንት ላይ ጥያቄ እንዲነሳ ማስገደዱም በጋዜጣው ዘገባ ተጠቁሟል፡፡ ለመንገድ ትራፊክ አደጋ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች ተርታ የሚመደበው በተለይ በአዲስ አበባ በቂ የእግረኞች መንገድ አለመኖሩ ሲሆን፣ እንደ የዓለም ባንክ መረጃ መሠረት፣ 65 ከመቶው የአዲስ አበባ የመንገድ ኔትወርክ፣ እግረኞች የሚረማመዱባቸው መንገዶች እጥረት እንዳለበት ሪፖርተር መዘገቡ፣ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች እየደረሱ ያሉ አደጋዎች ምን ያህል ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የሚጠቁም ነው፡፡

ምንም እንኳ አሽከርካሪዎች ለሚደርሱት የመንገድ ላይ አደጋዎች ትልቁን ኃላፊነት የሚሸከሙ ቢሆኑም፣ እግኞችም መንገድ ሲያቋርጡና በመንገድ ሲጓዙ ሊጠነቀቁ እንደሚገባ መንገር ለቀባሪው እንደማርዳት ይሆናል፡፡ ጥንቃቄ ለራስ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ ከሳምንታት በፊት ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት አካባቢ የደረሰው አደጋ እዚህ ላይ ትምህርታዊ በመሆኑ መነሳት ያለበት ይመስለኛል፡፡

ሽንጣሙ የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ንብረት የሆነው ቢሾፍቱ አውቶቡስ ሙሉ ሰው እንደጫነ ከፒያሳ አቅጣጫ ቁልቁል እየተንደረደረ ይመጣል፡፡ እንግዲህ መኪናው ፍሬን እንቢ ብሎት አለያም መሪ አልታዘዝ ብሎት እንደሁ አላውቅም ብቻ ግን እንዳመጣጡ ቢሆን ስንቱን ጭዳ ባደረገ ነበር፡፡ ይሁንና የሾፌሩ ብርታት፣ የመንገድ ትራፊክ መብራት ከታች የሚመጡትን መኪኖች መያዙ ጥሩ አጋጣሚ ሆነና አውቶቡሱ በመንገድ አካፋይ ተንደርድሮ ሊቆም ችሏል፡፡

እጅግ አሰቃቂ አደጋ ከማድረስ በተዓምር ያመለጠው አውቶቡስ በራሱና በዕፅዋት ላይ ካደረሰው ጉዳት በቀር በተሳፋሪዎችና በእግረኞች ላይ ምንም ጉዳት አለማደረሱ እሰየው ቢያሰኝም፣ የመኪና አደጋ ግን የዕለት ተዕለት የነዋሪዎች ሰቀቀን በመሆኑ ሁሉም በየፊናው ሊያስብበት ይገባል፡፡  

(ያየህይራድ አምባው፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...