Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአቶ ዳኜ መላኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

አቶ ዳኜ መላኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

ቀን:

  • አይመጥኑም በሚል የቀረበባቸው ቅሬታ ውድቅ ተደርጓል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ለወራቶች ክፍት ሆኖ የቆየው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሥልጣን ላይ አቶ ዳኜ መላኩን  ሾመ፡፡

እስከ ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሠሩ በቆዩት አቶ መድኅን ኪሮስ ምትክም አቶ ፀጋዬ አስማማውን ሾሟል፡፡

አቶ ዳኜ መላኩንና የምክትላቸውን እንዲሁም ለከፍተኛ ፍርድ ቤት 34 ዳኞችን፣ ለመጀመርያ ፍርድ ቤት የ75 ዳኞችን ሹመት ደብዳቤ በመላክ ፓርላማውን የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አቶ ዳኜ መላኩ ዕድሜያቸው 53 ሲሆን፣ ከ25 ዓመት በላይ በዳኝነት ሥራ ያገለገሉና ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ነበሩ፡፡

ምክትላቸው ሆነው የተሾሙት አቶ ፀጋዬ አስማማው ነጋ የሕወሓት ታጋይ የነበሩና ከትጥቅ ትግል በኋላ በትግራይ ክልል የሕግ አማካሪነት፣ በመGለ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት፣ እስከ ሹመት ጊያዜቸው ድረስ ደግሞ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት አገልግለዋል፡፡

አቶ ካደፎ አይዳሂከ የተባሉ የምክር ቤቱ አባል አቶ ዳኜ መላኩ በዳኝነት ሥራ ለመንግሥት የሚያደሉ በመሆናቸው፣ ለዚህ ሥራ አይመጥኑም በሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በሰጡት አስተያየት አቶ ዳኜ መላኩ በጥሩ ሥነ ምግባር፣ ፍትሐዊ ውሳኔ በመስጠት የሚታወቁ ከሕዝብ የቀረበ ቅሬታም እንደሌለባቸው በመግለጽ ትችቱን ውድቅ አድርገዋል፡፡

በዚህ ምላሽ መሠረት ወደ ድምፅ መስጠት የተካሄደ ሲሆን፣ ትችቱን የሰነዘሩት አቶ ካዳፎ ሹመቱን ደግፈው ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ ሌላ የምክር ቤቱ አባል ባደረጉት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በመሆኑም ፓርላማው 109 ዳኞችን እንዲሁም ሁለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ሹመትን አፅድቋል፡፡  

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...