Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኦሮሚያ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና ዕቅዶቻቸው

የኦሮሚያ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና ዕቅዶቻቸው

ቀን:

ከአጨቃጫቂው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ በተጓዳኝ ከኦሮሚያ ክልል ተወክለው በዕጩነት የቀረቡት ተወዳዳሪዎች፣ ቢመረጡ በቀጣይ የሚሠሩዋቸውን ሥራዎችና ዕቅዶቻቸውን በባለድርሻ አካላት አስገመገሙ፡፡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለስምንት ዓመት የሚያገለግል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አቅርበዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ያቀረባቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ባለፈው ረቡዕ ጥር 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢሊሌ ሆቴል ያቀረቡት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ፣ የእግር ኳሱ ዕድገትና መፃኢ ዕድል በመሠረታዊነት ከሚጠቀሱት ብዙዎቹን አካቶ የያዘ ነው፡፡ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጥቅል መዋቅራዊ ይዘት ጀምሮ ሥልጠናና ምልመላ እንዲሁም በታዳጊ ወጣቶችና በክበብ ደረጃ የሚቋቋሙ ቡድኖች ስለሚኖራቸው ቅርፅና ይዘት ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ አንፃር ምን መምሰል እንደሚገባው በዝርዝር አካቶ የያዘ ከመሆኑ ጎን ለጎን የክልሉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ቢመረጡም፤ ባይመረጡም ስትራቴጂክ ዕቅዱ ለተቋሙ እስከጠቀመ ድረስ ኃላፊነቱን ለሚረከበው አመራር እንደሚያስረክቡ ጭምር ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ የምርጫ ታሪክ በጥናት የተደገፈ ስትራቴጂክ ሰነድ ይዞ በመቅረብ የኦሮሚያ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ‹‹የመጀመርያ›› እንደሚያደርጋቸው ሰነዱን ለመገምገም የተገኙ ባለድርሻ አካላት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

የክልሉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ይህን ስትራቴጂክ ሰነድ እንዲያቀረቡ በዋናነት ያነሳሳቸው፣ ቢመረጡ ለእግር ኳሱ ምን መሥራት እንደሚጠበቅባቸው፣ ከማን ጋር እንደሚሠሩ፣ ለወቅታዊው የእግር ኳስ ችግር ምን ዓይነት መፍትሔዎችና አቅጣጫዎች ማለትም የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ይዞ ከመንቀሳቀስ አኳያ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ባለው አግባብ ሥራዎችን ለማከናወን ይቻል ዘንድ በማሰብ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ጭምር አስረድተዋል፡፡

እንደ ክልሉ ዕጩዎች እምነት ብቻ ሳይሆን በሰነዱም እንደተካተተው፣ እግር ኳስ በስሜት ሳይሆን በስሌት መመራት ይኖርበታል ብለው ያምናሉ፡፡ ከምረጡኝ ዘመቻው ጎን ለጎን ይህን የመሰለውን ሰነድ ያቀረቡት የክልሉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ ለወራት የዘለቀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ሒደት በአሰልችነቱ ይገልጹታል፡፡

በአጨቃጫቂነቱ እየቀጠለ ባለው የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ምርጫ፣ የኦሮሚያን ክልል በመወከል ሦስት ዕጩ ተወዳዳሪዎች ቀርበዋል፡፡ የጅማ አባ ጅፋር እግር ኳስ ክለብ ሥራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ለፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የቀረቡ ሲሆን፣ አቶ ከማል ሁሴንና ዶ/ር ኃይሌ ኢቲቻ ደግሞ ለሥራ አስፈጻሚ ምርጫው የቀረቡ ናቸው፡፡

ሦስቱ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ቢመረጡ ሕዝባዊ መሠረት ያለው እግር ኳስን ከማስፋፋት አንፃር ሊሠሩዋቸው ያቀዷቸውን በሰነዱ አካተዋል፡፡ በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የቆየውና የሚታወቀው አሠራር ውድድሮችን ከመምራት ያለፈ አይደለም፡፡ ይህ በዘመናዊ የእግር ኳስ ዓለም እንደማያስኬድ የሚያምኑት የሰነዱ አቅራቢዎች፣ ለዚህም ሁነኛው መፍትሔ የተቋሙን መዋቅር በመፈተሽ ተገቢው አካል በተገቢው ቦታና ጊዜ መጠቀም የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው የሚያከናውኗቸው ስለመሆኑ ጭምር ሰነዱን መነሻ በማድረግ ያብራራሉ፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...