የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሰሞኑን በወሰነው መሠረት ክሳቸው ተቋርጦ የሚፈቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች ግለሰቦችን በተመለከተ ነገ ጥር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. መንግሥት መግለጫ እንደሚሰጥ ታወቀ። መግለጫውን የሚሰጡት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አንባዬ መሆናቸው ታውቋል።
ክሳቸው እንዲቋረጥ ከሚወሰንላቸው በተጨማሪ በሌሎች የህግ አግባብ ይቅርታ አግኝተው የሚለቀቁ የተፈረደባቸው ፖለቲከኞችን በተመለከተም ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።