አዲሱ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሳ ቢሂ ማክሰኞ ጥር 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዚዳንት በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውንና በቆይታቸውም ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል፡፡ ሚኒስትሩ በበኩላቸው፣ ሶማሌላንድ ባልተረጋጋችው ሶማሊያ የራሷን ሰላም በማስጠበቅና ሰላማዊ ምርጫ በማድረግ አዲሱን ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ችላለች ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱም በተመረጡ በአጭር ጊዜ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ መቻላቸውን ያብራሩ ሲሆን፣ በቆይታቸውም በወደብና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ከተለያዩ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ለሪፖርተር ገልጸዋል (ፎቶ በታምራት ጌታቸው)