Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትወጥነት ያጣው የፕሪሚየር ሊግ ጉዞ

ወጥነት ያጣው የፕሪሚየር ሊግ ጉዞ

ቀን:

የኢትዮጵያ ፕሪሚያር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት 11 ሳምንታት ውስጥ የተመዘገቡት ነጥቦችና መረብ ላይ ያረፉት ቁጥሮች እያሸቆለቆለ መጥቷል፡፡ በተለይ ጨዋታዎቹ ያለምንም ግብ ማጠናቀቃቸውና እኩል ግብ ሲጠናቀቅ ማየት እየተለመደ በመምጣቱ የስፖርት ተመልካቹን ያሰለቸ ይመስላል፡፡

ባለፉት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመናት በበላይነት ያጠናቅቃሉ ተብለው ግምት የሚሰጣቸው የነበሩ ክለቦች፣ ዘንድሮም በተመሳሳይ መንገድ እየሄዱ ነው፡፡ በአንፃሩ ፕሪሚየር ሊጉ ሁሌም በበላይነት የሚያጠናቅቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀላሉ ጨዋታን አሸንፎ መውጣት ሲቸገር ቢስተዋልም፣ የደደቢት ወቅታዊ የድል ጉዞ ከወዲሁ ትልቅ ግምት እንዲቸረው አስችሎታል፡፡

ደደቢት ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች በሰባቱ ሲያሸንፍ በአራቱ ደግሞ ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ችሏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንፃሩ ዘጠኝ ጨዋታዎችን አከናውኖ አራቱን ሲረታ በአምስቱ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት ደደቢት 25 ነጥቦችን ሲሰበስብ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ቀሪ ጨዋታ እያለው 17 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ወጥ አቋም ማሳየት የተቸገሩት ክለቦች የክልል ከተማ ክለቦች ጥንካሬ እንደ መንስኤ ቢነሳም፣ በሊጉ ልምድ ያላቸው ክለቦችና ያላቸው የተጫዋቾች አቅም ከሚያስመዘግቡት ውጤት ጋር ተመጣጣኝ አለመሆኑ በተለያዩ ባለሙያዎች አስተያየት እንዲሰነዘርባቸው አስችሏል፡፡

ዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀል የቻሉት የተለያዩ የክልል ክለቦች፣ በተሻለ ሁኔታ ከሰንጠረዥ ወገብ በላይ ሲገኙ በተቃራኒው በፕሪሚየር ሊጉ ልምድ ያላቸው ክለቦች እያሽቆለቆሉ መምጣታቸውና የአሠልጣኞች ስንብት ከመስማት ውጪ መሠረታዊ ምላሽ ሲቀመጥ አለመስተዋሉ እንደ ክፍተት እየተነሳ ይገኛል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተፎካካሪነታቸው የሚታወቁትና በተመልካችም ሆነ በሜዳቸው የማይበገሩ የነበሩ ክለቦች ወራጅ ቀጣና ላይ መቀመጥ ትኩረትን የሳበ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ድሬዳዋ፣ ኤሌክትሪክና አርባ ምንጭ ከተማ የዚሁ ማሳያ ናቸው፡፡ ክለቦቹ በቂ ተጫዋች ቢኖራቸውም፣ ከሁለት ጨዋታ በላይ ማሸነፍ ተስኗቸዋል፡፡ በሊጉ አናት ላይ የሚገኘው ደደቢት ጉዞው መልካም የሚባል ቢሆንም፣ ባለፉት ዓመታት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መጠናቀቂያ ላይ የሠራው ስህተት የዋንጫ ጉዞውን ሲያደናቅፍ ተስተውሏል፡፡ በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመሪው ደደቢት የሚያከናውነው ጨዋታ የሚያመላክተው ፍንጭ ይኖራል የሚለው ሐሳብ የብዙኃኑ ነው፡፡   

ወራጅ ቀጣና ላይ የሚገኙ ክለቦች በአሠልጣኞች ቅያሪ አማካይነት የሚያመጡት ውጤት ተጠባቂ እንደሆነ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በአንፃሩ ለሊጉ አዲስ የሆኑ የክልል ከተማ ክለቦችም ዘላቂ ውጤት በቀጣዮቹ አምስት ሳምንታት ውስጥ ይጠበቃል፡፡

ሊጉን ደደቢት በ25 ነጥብ ሲመራ፣ አዳማ በ18 ይከተላል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ17 ነጥብ እንዲሁም ፋሲል በ16 ነጥብ ሦስተኛና አራተኛ ደረጃ በመያዝ ተቀምጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...