Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹በዕድሜ ጎዳና ላይ የጉዞ ትዝታ››

‹‹በዕድሜ ጎዳና ላይ የጉዞ ትዝታ››

ቀን:

ማዕከላዊ እስር ቤት ተዘግቶ ወደ ሙዚየምነት እንደሚለውጥ በተገለጸ በጥቂት ቀናት ለንባብ የበቃው የ100 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው በለጠ ገብሬ መጽሐፍ፣ የጸሐፊውን የማዕከላዊ ትውስታ ያትታል፡፡ በእስር ቤቱ ስለደረሰባቸው እንግልትና በወቅቱ አብረዋቸው ታሰረው ከነበሩ ሰዎች ጋር ስለነበራቸው ታሪክም የሚዳስስ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡ ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም.  ‹‹በዕድሜ ጎዳና ላይ የጉዞ ትዝታ›› በሚል የተመረቀው ሁለተኛው መጽሐፍ የማዕከላዊ የእስራት ዘመናቸው ምን ይመስል እንደነበር ያሳያል፡፡ በምርቃቱ ዕለት፣ ከጸሐፊው ጋር አብረው ታስረው የነበሩት ጌታቸው ደባልቄ አጭር ግጥም ጽፈው በአበበ ባልቻ አስነብበዋል፡፡ በማዕከላዊ አብረው መገረፋቸውን አብረው መሰቃየታቸውን የእሳቸውና የደራሲው የሕይወት አንድ አካል መሆኑን የሚገልጽ ግጥም ነበር፡፡ አብሯቸው ታስሮ የነበረው ነቢይ መኰንን ስለ መጽሐፉ አጭር ዳሰሳ አቅርቧል፡፡ አበበ ባልቻ ከመጽሐፊቱ የአንዱን ምዕራፍ ቀንጭቦ አንብቧል፡፡ አቶ በለጠ ከዓመታት በፊት ‹‹በዕድሜ ጎዳና ላይ ትዝታ›› የሚል የመጀመርያውን ቅጽ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡ አቶ በለጠ ከመንግሥት ሹመኝነት ባሻገር በኪነ ጥበቡ መስክ  በተዋናይነት በተለይ የሚታወቁት፣ በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ በተደረሰው አፋጀሺኝ ቴአትር እንደ አፋጀሺኝ ሆነው የሴት ገጸ ባሕሪን በተጫወቱበት ነው፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...