አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 2 ኪሎ ግራም የተቆራረጠ አጥንት የሌለው የበሬ ወይም የበግ ሥጋ
- 2 ኪሎ ግራም በትንንሹ የተቆራረጠ የበሬ ወይም የበግ አጥንት ከነሥጋው
- 4 መካከለኛ ጭልፋ (400 ግራም) ቀይ የተገረደፈ ሽንኩርት
- 5 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
- 3 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
- 2 የሾርባ ማንኪያ እርድ
- 4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
- 2 እግር ርጥብ በሶብላ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ባሮ
- 2 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
- 2 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 መካከለኛ ጭልፋ በደቃቁ የተከተፈ የሾርባ ቅጠል ግንድ
አዘገጃጀት
- ሥጋውን አጥንቱን በቀዝቃዛ ውኃ ማጠብ፤
- አንዴ ብቻ አገንፍሎ ውኃውን መድፋት፤
- በሙቅ ውኃ ጥዶ ጨው ጨምሮ እንዲበስል አልፎ፣ አልፎ እያማሰሉ መጠበቅ፤
- ግማሽ ብስል ሽንኩርቱን፣ ባሮ ሽንኩርቱን፣ ርጥብ ቅመሙን፣ እርዱን፣ ቅቤና የሾርባ ቅጠሉን ግንድ ጨምሮ እያማሰሉ ማንተክተክ፤
- ሲበስል ነጭ ቅመም፣ በሶብላና ቃርያ ጨምሮ መጠነኛ መረቅ እንዲኖረው አድርጎ በማውጣት ለገበታ ማቅረብ፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)