Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየጥምቀት በዓል በየአገሮቹ

የጥምቀት በዓል በየአገሮቹ

ቀን:

የጥምቀት በዓል በኦስትሪያ፣ በኮሎምቢያ፣ በክሮሽያ፣ በቆጵሮስ፣ በፖላንድ፣ በኢትዮጵያ (ቀኑ ይለያል)፣ በጀርመን አንዳንድ ግዛቶች፣ በጣሊያን፣ በስሎቫኪያ፣ በስፔንና በኡራጋይ ሕዝባዊ በዓል ሆኖ ይከበራል፡፡ በአውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ በዩናይትድ ኪንግደምና በአሜሪካ ሕዝባዊ በዓል ሆኖ ባይከበርም ዕለቱ ታስቦ ይውላል፡፡

አውስትራሊያ

በአውስትራሊያ የሚገኙ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት በተለይም ካቶሊክ፣  የጥምቀት በዓልን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያከናውናሉ፡፡ አብዛኞቹም  ክርስቶስ ኢየሱስ ሲወለድ ስጦታ በማምጣት የጎበኙት ሰብአ ሰገል ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ቢሆንም ብዙዎቹ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ለተጠመቀበት ሥርዓት ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በኋላ ምዕመኑን በማሰባሰብ ግብዣ ያደርጋሉ፡፡ በአውስትራሊያ ጥምቀት ትምህርት በሚዘጋበት በጥር መጀመርያ ስለሚውል ባህር ዳርቻ በመሄድና በመዝናናት የሚያሳልፉም አሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አውስትራሊያ

 

በዩናትድ ኪንግደም

በዩናይትድ ኪንግደም ጥምቀት ኢየሱስ ሲወለድ በሰብአ ሰገል መጎብኘቱንና ጥምቀቱን አስመልክቶ ይከበራል፡፡ በዕለቱም ሁሉም የገና በዓል ማድመቂያዎች የሚነሱበት፣ የክሪስማስ ዛፍ መብራቶች የሚጠፉበት ነው፡፡ የገና ዛፍን ከጥምቀት በኋላ ማቆየትም እንደ መጥፎ ዕድል ማሳቢያ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ሰው የገና ዛፍና ማድመቂያዎቹን ከየቤቱ የሚያወጣ ሲሆን፣ ሱቆች ደግሞ የሚጠቀሙት የገና ዛፍና መብራት ግዙፍ ስለሚሆን መብራቱን ብቻ አጥፍተው ቀስ በቀስ የገና ዛፉን ያፈርሳሉ፡፡

ካናዳ

ጥምቀት በካናዳ ሕዝባዊ በዓል ባይሆንም ብዙ ክርስቲያኖች በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ይሳተፋሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ልዩ አገልግሎትን ይካፈላሉ፡፡ በማታ የትምህርት አገልግሎትም በክርስትና የጥምቀት ትርጉም ምን እንደሆነ ይማራሉ፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ሰዎች ፊታቸውን በማስክ በመሸፈን ዘመድ አዝማድና ጓደኛ ቤት በመሄድ ይዘፍናሉ፣ ይደንሳሉ፡፡ አልኮል መጠጦችና ጣፋጮችም ይጋበዛሉ፡፡

ጀርመን

ጥምቀት የገና ወቅት ማብቂያ ማሳያ ነው፡፡ በመሆኑም በጉተምበርግ፣ በባቫሪያና ሳክሶኒ አንላልት ጥምቀት ሕዝባዊ በዓል ሆኖ ይከበራል፡፡ እንደ ካናዳ ሁሉ ምዕመኑ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ስለጥምቀት ይማራል፡፡ በጥምቀት ዋዜማ ሰዎች ተሰባስበው ዓመቱ የጤናና የመልካም ዕድል እንዲሆን ይጠጣሉ፡፡ ለዚህ በዓል ሲባልም ልዩ የሆነው ‹‹ቦክቢር›› ይጠመቃል፡፡ ይህ ቢራ ጠንካራና ከሌሎች የቢራ ዓይነቶችም ከፍተኛ የአልኮል ይዘት አለው፡፡

ሕፃናትም ኢየሱስ ሲወለድ ዕጣን፣ ከርቤና ወርቅ ያመጡትን ሦስቱ ሰብአ ሰገል የለበሱት ዓይነት በመልበስ ከዲሴምበር 25 እስከ ጃንዋሪ 6 ማለትም ከውልደቱ እስከ ጥምቀቱ ድረስ በየቤቱ በመዞር ስለኢየሱስ መወለድ ይዘምራሉ፡፡ ከየቤቱም ገንዘብ በመጠየቅ ለዕርዳታ ድርጅት ያስረክባሉ፡፡

ጀርመን

 

ጣሊያን

 በጣሊያን ጥምቀት የሚከበረው የክርስቶስን ሰውነትና አምላክነት አመላክቶ በመጥምቁ ዩሐንስ መጠመቁን ለማስታወስ ነው፡፡ በዕለቱ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ባንኮችና ትምህርት ቤቶች ይዘጋሉ፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠውም በዋና መንገዶች ብቻ ነው፡፡

ሜክሲኮ

በሜክሲኮ ለገና ዋዜማ ብቻ ሳይሆን ለጥምቀት ዋዜማም ልጆች ስጦታ ይበረከትላቸዋል፡፡ ጥምቀት በክርስትና እምነት ተከታዮች የሚከበር ቢሆንም፣ ሕዝባዊ በዓል አይደለም፡፡ ሆኖም ከጥምቀት ጋር በተያያዘ በሚኖረው ፌስቲቫል በዕለቱ የሜክሲኮ ጎዳናዎችን በመኪና ለመጠቀም አዳጋች ነው፡፡

ፖላንድ

ጥምቀት በፖላንድ ሕዝባዊ በዓል ነው፡፡ በአብዛኞቹ የፖላንድ አካባቢዎች ትልቅ በዓል ሲሆን፣ ጎዳናዎችም በጥምቀት በዓል ዘፈኖችና ትዕይንቶች ይደምቃሉ፡፡ የጎዳና ትዕይንቱም በአብዛኛው የሚያተኩረው ሰብአ ሰገል ኢየሱስ ሲወለድ ስጦታ እንዳመጡ ሁሉ፣ ሰዎች ለታዳሚው ጣፋጭ በማደል ነው፡፡ ቀሳውስት ደግሞ ስለጥምቀት አስፈላጊነት በማስተማር ቤቶችን ይባርካሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በየበራቸው አናት ላይ ውኃ፣ ዕጣንና ከርቤ የያዙ ሦስት ትናንሽ ሳጥኖች ያስቀምጣሉ፡፡ ይህም ሰብአ ሰገል ለኢየሱስ ያመጡለትን ስጦታ ለማስታወስ ነው፡፡

ፖላንድ

 

ሩሲያ

በሞስኮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን በረዶዋማ በሆነ ውኃ ውስጥ በመግባት ጥምቀትን ያከብራሉ፡፡ ጥምቀት በሩሲያ ዋና በዓል ሲሆን፣ የክርስቶስ መወለድና መጠመቅ የሚታወስበት ነው፡፡ ጥምቀት የተቀደሰ፣ ንፁህና ጥምቀቱም በሽታን የሚፈውስ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ሩሲያ

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...