Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመቻቻል እሴትን የሚያጎለብት አገራዊ የቪዲዮ ውድድር ተጀመረ

የመቻቻል እሴትን የሚያጎለብት አገራዊ የቪዲዮ ውድድር ተጀመረ

ቀን:

‹‹ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት በዚህ ዘመን ሰዎች ዋጋና ክብር እንዳላቸው እንዲሰማቸው የሚያደርግና የየራሳቸው ሐሳብና ህልም ያላቸው ሰዎች ተሰሚነት የሚያገኙበትን ማኅበረሰብ ለመፍጠር መቻቻል አስፈላጊ ነው፤›› የሚለውን መሠረተ ሐሳብ የሚያንፀባርቅ የቪዲዮ ውድድር መጀመሩን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ይህ የቪዲዮ ውድድር “Our Ethiopia” [ኢትዮጵያችን] በሚል ጭብጥ የሚካሄድ ሲሆን በውድድሩም የመቻቻል እሴቶችን ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡

በዚህ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ክፍት በሆነው የቪዲዮ ውድድር የፊልም ባለሙያዎች የሦስት ደቂቃ ርዝመት ያለውና፤ ስለ ኢትዮጵያ ብዝኃነት ጠንካራ ጎኖች፣ ስለአገሪቱ ተግዳሮቶች፣ እንዲሁም ዜጎቿ መቻቻልን እና የርስ በርስ መከባበርን ለመደገፍ ማድረግ ያለባቸውን ነገሮች የሚያሳይ መሆን ይኖርበታል፡፡

ሁሉም ቪዲዮ በአማርኛ ቋንቋ መሠራት ያለበት ሲሆን፣ የእንግሊዝኛው ትርጉም በጽሑፍ በቪዲዮው ላይ መካተት ይኖርበታል፡፡ ኤምባሲው እዳመለከተው በማንኛውም ቪዲዮ ላይ ሃይማኖትን፣ ዘርን፣ ባህላዊ እሴቶችን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሠረት ያደረገ አድልዎን ያለመቀበል መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተወዳዳሪዎች ሥራቸውን እስከ የካቲት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ብቻ በዩቲዩብ ወይም በአሜሪካ ኤምባሲ የሕዝብ ጉዳዮች ክፍል “Our Ethiopia” የቪዲዮ ውድድር ፖ.ሣ.ቁ. 1014 በሲዲ ወይም ዲቪዲ ማስገባት እንደሚቻል፣ ቪዲዮውን ዩቲዩብ በሚቀበላቸው ማናቸውም የአቀራረብ መንገዶች መጫን እንደሚቻል፣ ቪዲዮው ከተጫነ በኋላ አድራሻው        በ[email protected] መላክ እንደሚኖርበት ኤምባሲው አሳስቧል፡፡

የውድድሩ አንደኛ ደረጃ አሸናፊ 80, 000 ብር የሚገመት ሽልማት ተሸላሚ ሲሆን፤ ሁለተኛ ለሚወጣ 50,000 ብር እና ሦስተኛ ለሚወጣ 30, 000 ብር የሚገመት ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡

የቪዲዮው ውድድር ኤምባሲው ነፃና አዎንታዊ የሐሳብ ልውውጥን በማበረታታት፣ ተቻችሎ የመኖርን እና የብዝኃነትን አዎንታዊ ሚና ለማጉላት የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ብሏል፡፡

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...