Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

እኔ የምለዉፌዴራሊዝምና የሲቪል ፖለቲካ እንቅስቃሴ

ፌዴራሊዝምና የሲቪል ፖለቲካ እንቅስቃሴ

ቀን:

ሱራፌል ተሾመ

ገራችን ኢትዮጵያ፣ በተለይም የፌዴራል ርዓቱ በተግባር ላይ ከዋለ በኋላ ባሉ መታት፣ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ አንዳንድ ጊዜ ዝባዊነት ያላቸው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በመንግ ራቹ ፓርቲ ውስጣዊ ግጭት ምክንያት የተነሱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች በተለያዩ ገራችን ክፍሎ ይስተዋላሉ፡፡ 1960ዎቹ አብቦ ቀጥሎም በተሰነዘረበት ያልተመጣጠነ ርምጃ ከስሞ የቆየው የሲቪል ፖለቲካ እንቅስቃሴም ከወታደራዊው መንግ መውደቅ በኋላ እንደገና ይወት ዘርቶ ገሪቱ ፖለቲካ ላይ የራሱን ሚና እየተጫወተ አሁን ያለንበት ደረጃ ደርሰናል፡፡ የምንመራበት የፌዴራል ርዓት በዋና አረጋግጠዋለ የሚለው የብ ረሰቦች የጋራ ተጠቃሚነትና እኩልነት ሲሆን፣ ይህንንም ለማስፈጸም ረቱን ያደረገ የክልሎች አወቃቀር ተግብሯል፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ በተደጋጋሚ የሚነሱ ተኮር ግጭቶችን ከማስተናገዳችን አን ፌዴራሊዝችን ግቡን ለመምታት የሚያስችል ርዕዮተ ለማዊና ተግባራዊ ብቃት አለው ወይ የሚል ጥያቄ ከሽግግር መንግ አንስቶ ሲሰማ ቆይቷል፡፡  እ.ኤ.አ. 2012 ገደማ ወዲህ የተነሱና ዜጎችን አደባባይ ያስወጡ ጥያቄዎችና ግጭቶች ደግሞ ከወትሮው በተለየ መልኩ ረዘም ላለ ጊዜ ከመቆየታቸው ባሻገር በአንድ አካባቢ መወሰን አቁመዋል፡፡ ገራችን ወቅታዊ ሁኔታም ከመሻሻልና ወደ ራዊ መግባባት ከመድረስ ይልቅ ቀድመው መመለስ በነበረባቸው የማንነትና የድንበር ውዝግቦች ተተብትቧል፡፡

እንግዲህ አሁን ያለንበት የፖለቲካ መድረክ ነዚህ አለመረጋጋቶች ጥላ ያጠላበት መሆኑን የተረዱ ይሎች በጋራና በተናጠል የመፍት ሳብ ያፈላልጋሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ መንግትና መንግትን የመረቱ ፓርቲዎች፣ ገር ውስጥና በውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ሰፋ ባለ ሁኔታ ደግሞ ባልተደራጀ መንገድ ወቅቱ በፈቀደው ሁኔታ ድም የሚያሰማውን ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊን እንደ ፖለቲካ ይሎች ወስደን ገሪቱን ድል ለመወሰን የሚጠቅሙ የመፍት አቅጣጫዎችን መነጋገር ይኖርብናል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህ ፍም ለመዳሰስ የሞክርኩት ከደርግ ውድቀት ጀምሮ ተግባራዊ ያደረግነው ርን ረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ምን ተነስቶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ቻለ? በተለይም ታሪካዊ አንድምታን ባገናዘበ መልኩ ርን ረት ያደረገው ፌዴራሊዝማችን ምን አቋም ላይ ይገኛል የሚሉትን ጥያቄዎች ነው፡፡

የጽ አወቃቀር ይህን ይመስላል፡፡ በመጀመሪያ ክፍል 1960ዎቹ እስከ 1983 ዓ.ም. (ዳዊ መንግ) ቀጥሎም 1983 ዓ.ም. እስካሁን ያለውን (ፌዴራል መንግ) የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪካችንን በማንሳት ርን ረት ያደረገ ፌዴራሊዝም እንዴት የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ እንደተቀላቀለ እዳስሳለ፡፡ በሁለተኛ ክፍል የምንከተለው ርን ረት ያደረገ ፌዴራሊዝም እስካሁን በምን ይነት መንገዶች እንደተጓዘ ለማሳየት መልካም ገጽታዎችን፣ ስህተቶችን እያረመ የመጣበትን መንገድ፣  የፈታቸውና ያልፈታቸው ችግሮችን በመጥቀስ የማንነት ጥያቄን በምን ይነት ሁኔታ እንዳስተናገደ ለማሳየት እሞክራለ፡፡ ስተኛና አራተኛ ክፍል አሁን ያለንበት የፖለቲካ ትኩሳት ላይ እንዴት ልንደርስ ቻልን? ብሔርን ረት ያደረገ ፌዴራሊዝማችን ላይ እርምት ማድረግ ይኖርብናል ወይ? የሚሉትን አንኳር ሳቦች አቀርባለ፡፡ ፌን የምጨርሰው ገር ጉዳይ ይመለከተኛል እንደሚል ማንኛውም ዜጋ ያነሳዋቸውን የመወያያ ነጥቦች አብላልቼ ማጠቃለያ የሚሆኑ ግላዊ አስተያየቶችን በመሰንዘር ይሆናል፡፡

ርን ረት ያደረገ ፌዴራሊዝም እንዴት ልንገነባ ቻልን?

የቀዳማዊ ይለ ላሴ ዙፋን ኤርትራን ጨምሮ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተወረወሩ አመ መናጋት ሲጀምር፣ ገራችን ውስጥ ከዚህ በፊት ትልቅ ቦታ ያልነበራቸው መፈክሮች በሺ የሚቆጠሩ ወጣት ተማሪዎችና በተለያዩ ይወት መስክ ላይ ያሉ የተገዢው መደብ አባላትን አደባባይ ማዋል ጀመሩ፡፡ የአመ መንስዎቹ እንደተነሱበት ቦታ የተለያየ ይዘት ቢኖራቸውም በግንባር ቀደምትነት የሚመደቡትየኤርትራ ጉዳይ”  እየተባለ ይጠራ የነበረው የመገንጠል ጥያቄ፣መሬት ላራሹ ለላብ አፍሳሹ”  በሚለው መፈክር የሚታወሰው የመሬት ባለቤትነት ጥያቄና የብ ረሰቦች የእኩልነትና የራስን በራስ የማስተዳደር መብት ነበሩ፡፡ የዘውዳዊው ርዓት እነዚ ችግሮች የመፍታት አቅምም ሆነ ረታዊ ፍላጎት ባለማሳየቱ በአውሮፓውያን የትግል ልት ራሳቸውን ልጥነው ካደራጁ ወጣት ምሁራንና በደረሰበት የመልካም አስተዳደር ጦት የመፍት ያለህ ሲል የቆየው ወታደር  ከወከላቸው መኮንኖች ጋር ገሪቱን ፈንታ ለመወሰን ግብግብ ጀመረ፡፡

ይህን የታሪክ አጋጣሚ ሰላማዊ በሆነ ለውጥ ወይም ልጣን ሽግግር መለወጥ ያልቻለው የንጉነገ መንግ በአጭር ጊዜ በወታደራዊው ደርግ ልጣኑን ተቀምቶ የታሪክ ተመልካች ለመሆን በቃ፡፡ የደርግ መንግ የተማሪዎችንና የመላው ኢትዮጵያውያን የትግል አጀንዳ የነበረውን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄን በወቅቱ የአብዛኛውን ዝብ ቀልብ ተቆጣጥሮ ከነበረው ርዕዮተ ዓለማዊ ፍልስፍና አንድ ገጽ በመጠቀም የገጠር መሬቶችንና የከተማ ቤቶችን ወርሶ ለዜጎች አከፋፈለ፡፡ ይህን ርምጃ በበጎ ይን ተመልክቶ ነገር ግን ያልተመለሱ ጥያቄዎችንና ልጣን ምንጭ ዝባዊ ፈቃድ እንጂ ወታደራዊ ይል መሆን የለበትም በሚል የኢትዮጵያ ሲቪል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በህቡዕና በአደባባይ ለጥቂት ጊዜ ቢቀጥልም በአሰቃቂ ሁኔታ ለመክሰም ተዳርጓል፡፡ ከደርግ አደን የተረፉና ቀድሞውንም ተዘጋጅተው ወደ ተራዘመ የትጥቅ ትግል የገቡ ይሎች ትግሉን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ቢያፋፍሙትም የሲቪል የፖለቲካ እንቅስቃሴ ግን ጊዜውም ቢሆን ተዳፈነ፡፡

የደርግ መንግ ገሪቷ ውስጥ የነበረውን የፊውዳል ርዓት በጣጥሶ የአብዮታዊነት መስመርን ቢከተልም ዳዊ ማንነት ሳይቀር የማዕከላዊ መንግትነት ሚናን መጫወት ጀመረ፡፡ የኤርትራ ጉዳይና የብ ረሰቦች የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ደርግ በዘረጋው አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የፖለቲካ አቅጣጫዎች በበቂ ሁኔታ ሊመለሱ ባለመቻላቸው ከዚህም በተጨማሪ በሰሜናዊው ገራችን ክፍል የተፋፋመው የትጥቅ ትግል ከብዙ ኢትዮጵያውያን ደም መፋሰስ በኋላ ለፍሬ በቅቶ ወታደራዊው መንግትም በዋነኛነ አስከብረዋለ ያለውን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ማስከበር እንኳን ሳይችል የፖለቲካውን መድረክ ስረከበ፡፡ በዚህ የፖለቲካ ምዕራፍ ውስጥ በሁለቱም ዳዊ መንግታት (ንጉዊና ወታደራዊ) አስተዳደሮች በአብዛኛው ተዘንግቶ የቆየው የብ ረሰቦች የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄና በተለይም በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማርና የመራት መብት፣ ትጥቅ ትግል ለገቡ የፖለቲካ ይሎች ግን ዋነኛ የመታገያ አጀንዳ ነበር፡፡ ሁለቱም ዳዊ መንግታት ተመሳሳይ አስተዳደራዊ አውራጃዎችን ረት አድርገው ልጣንን በማዕከላዊነት ይዘው በመቀጠላቸው የዜጎች የራስን በራስ የማስተዳደርን ጥያቄ በአጥጋቢ ሁኔታ ለመመለስ ሳይችሉ አልፈዋል ማለት እንችላለን፡፡

በደርግ መደምሰስ ማግ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አብዛኛውን የፖለቲካ ይሎች ተፉ የምክክር መድረኮች ተዘጋጅተውና ገሪቷ ድል ላይ ውይይት ተደርጎ የብ ረሰቦች የጋራ ተጠቃሚነትና እኩልነት ያረጋግጣል የተባለ መንግትና ያንንም የሚተገብር ርን ረት ያደረገ የፌዴራላዊ ሥርዓት ሲገነባ፣ የኤርትራ ጉዳይ ደግሞ በኢትዮጵያውያን መካከል የጋራ መግባባት ሳይደረስበት መፍት ተሰጥቶታል፡፡ የፌዴራል ርዓቱም ሆነ ርዓቱ ረት የሆነው መንግ ገሪቱ ውስጥ አንራዊ ሰላም በማስፈን ለረጅም ጊዜ የቆየ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት ቢፈጥሩም በመግቢያዬ ላይ በጠቀስኳቸው የብ ግጭቶችና የማንነት ቀውሶች ምክንያት ከመነሻው ጀምሮ ከወቀሳ አላመለጡም፡፡

የምንከተለው የፌዴራል ሥርዓት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ የተለያየ በረሰባዊ ማንነት ባላቸው ገሮች ረዘም ላለ ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ የፌዴራል ሥርዓት የሚዋቀረው በውስጡ በሚገኙ ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር በሚችሉ አካባቢያዊ መንግታትና ልጣኑ በተገደበ ማዕከላዊ መንግ ነው፡፡ አካባቢያዊ መንግታት ስቱንም የመንግ አውታሮች በክልሉ ነዋሪዎች በማዋቀር ክልላቸውን ሲያስተዳድሩ የፌዴራል መንግ ደግሞ የሁሉም ክልሎች አንራዊ ስብጥርን በማገናዘብ መዋቅሩን በመላው ገሪቱ ይዘረጋል፡፡ ገራችን ፌዴራል ሥርዓት ከዘጠኝ ክልል መንግታት ሁለት ከተማ አስተዳደሮችና ፓርላሜንታዊ ሥርዓት ከሚከተል ፌዴራል መንግ የተዋቀረ ሲሆን ክልሎች ደግሞ በዋናነት ብሔርን ረት ድርገው ተካልለዋል፡፡ ክልሎች በዋናነት ብሔርን ረት አድርገው ይዋቀሩ እንጂ በውስጣቸው ከአንድ ብሔረሰብ በላይ መያዛቸው አልቀረም፡፡  ይህም የሆነው ገራችን የሚገኙ ብሔርና ብሔረሰቦች ዝብ ብዛትም ሆነ በሚይዙት የቆዳ ስፋት ተመጣጣኝ አቋም ላይ የሚገኙ ባለመሆናቸውና በተለይ እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች ክልላዊ መንግ የመመረት አቅም ስለሌላቸው ከሌሎ መሰል ብሔሮች ጋር ተቀናጅተው አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ይመስለኛል፡፡  የምንከተለው የክልሎች አወቃቀር ብሔርን ረት ያደረገ ይሁን እንጂ አንድ ብሔር አንድ ክልል የሚል መፍት አይደለም፡፡ ነገር ግን ገሪቱ ውስጥ የተቋቋሙት ክልሎች ለምን በአሁኑ ሁኔታ እንደተካለሉ የሚያስረ አጥጋቢ መልስ ሲሰጥ አይታይም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች በመቶ የሚቆጠሩ ተወላጅ ያላቸው ብሔረሰቦች በክልልነት የመደራጀት ዕድል አግኝተው በራሳቸው ቋንቋ የመማርና የመራት መብታቸው የተከበረበት ሁኔታ ሲኖር፣ በሌሎች ቦታ ደግሞ በሚዮን የሚቆጠር ተወላጅ ያላቸው ብሔረሰቦች በክልል ደረጃ አስተዳደራቸውን የማዋቀር ድል አላገኙም፡፡ መንግ አንድ ብሔር በክልልነት ራሱን ለማወጅ የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ የሚፈቅድ ሲሆን በተግባር ግን ላይ የዋለበት አጋጣሚ እስካሁን አልተከሰተም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የክልሎች አወቃቀር በውስጡ ለአደረጃጀት ጥያቄዎች የተጋለጠ በመሆኑ ብሔሮች የሚያነሱት የወረዳ፣ የልዩ ወረዳ፣ የዞንና የልዩ ዞን ይገባኛል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡

የራሳችንን ድል በራሳችን ለመወሰን ቆርጠን የተነሳነው እኛ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ዝቦች በሚል ጭብጥ የሚጀምረው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ራስን በራስ የማስተዳደር ነትን የሚፈቅድ ቢሆንም ያንን ለመተግበር የመረጠው የክልሎች አወቃቀር ግን ከላይ ለጠቀስኳቸው የብሔረሰብ ጥያቄዎች መንስ ፡፡ መንግሥቱ እንዲህ ይነት የማንነት ጥያቄዎችን የሚያስተናግድበት የራሱ አካሄዶች ቢኖሩትም ችግሮቹ በዘላቂነት የሚፈቱት ብሔራዊ መግባባት የተደረሰበት የክልሎች ማንነት አወሳሰን ሲኖር ነው የሚል አመለካከት አለኝ፡፡  ይህንን ርዕስ በአራተኛው የጽ ክፍል ለመዳሰስ የሞከርኩ ሲሆን በሚቀጥለው ክፍል ደግሞ የምንከተለው ብሔርን ረት ያደረገ የክልሎች አወቃቀርን ወደ ፖለቲካው መድረክ ያስተዋወቀው የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም እንዴትና በምን ሁኔታ አሁን ወዳለንበት አቋም እንደ ደረሰ አቀርባለ፡፡

ብሔርን መረት ያደረ ፌዴራሊዝም እስካሁን እንዴት ሊቀጥል ቻለ?

የፌዴራል ርዓቱ ይዞ የመጣው በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማርና የመራት መብት፣ ክልላዊና አካባቢያዊ መንግሥት የመዘርጋት ድል በአብዛኛው ገሪቱ   ክፍል በመልካም ገጽታነት እንደተወሰደ በሰፊው ይታመናል፡፡ ይህን መብትና ድልንም በመጠቀም  ክልሎችና በውስጣቸው የሚኖረው ዝብ በርካታ አዎንታዊ ርምጃዎችን ተራምደዋል ብንል ድፍረት አይሆንም፡፡ በአገራችን የሚገኙ ቋንቋዎች በንግግርም ይሁን በጽፈት መስክ ድገት ማሳየታቸው፣ ያልተማከለ አካባቢያዊ አስተዳደሮች በመፈጠራቸው ምክንያት የሚስተዋለው የብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራስ የማተዳደር ልምድ ማካበት ዚያ በተረፈ በተግባር ላለፉት ሁለት አሥርት መታት በአገሪቱ ውስጥ አንራዊ ሰላም በማስፈን ለረጅም ጊዜ የቆየ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት መፍጠሩ የፌዴራል ሥርዓቱ የሚታወስባቸው መልካም ገጽታዎች ሆነው ይቆጠራሉ፡፡

በአገራችን የሚገኙ ዘጠኝ ክልሎች የተቋቋሙት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 ረት ሲሆን ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሆነው ለመቋቋም የሚያስችላቸው መብትና የአራር ደትም በዚሁ አንቀጽ ተቀምጧል፡፡  ይሁንና የፌዴራል ሥርዓታችን ወጥ የሆነ የክልሎች ማንነት አወሳሰን አይታይበትም፡፡  አስቀድሞ በተጠቀሰው አንቀጽ ሥር የተዘረዘሩት ክልሎች በምን ፈርት የክልልነት ማዕረግ እንደተጎና ሌሎች ከፍተኛ የተወላጅ ቁጥር ያላቸው ብሔርና ብሔረሰቦች ደግሞ በአንድ ላይ ተዋህደው አንድ ክልል እንዲመርቱ እንደተገደዱ የሚተነትን ወጥ ፈርት ተቀምጧል ለማለት አያስደፍርም፡፡ ይህ በመሆኑም በአንዳንድ አካባቢዎች በመቶ በሚዮኖች የሚቆጠሩ ተወላጅና ተናጋሪ ያላቸው ብሔረሰቦችና  ቋንቋዎች በመማር ማስተማሩ ደትና ልላዊ መንግሥት ቋንቋነት የማገልገል ድል በማግኘታቸውም ቋንቋዎቹም ሆነ ተናጋሪዋቻቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ሲጎና ሌሎች ተመጣጣኝ የተወላጅ ቁጥር ያላቸው ብሔረሰቦችና ያንኑ ያህል ተናጋሪ ያላቸው ቋንቋዎች ግን ከዚህ ጥቅም መቋደስ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ይህ በመሆኑም አልፎ አልፎ የሚገነፍሉ በአብዛኛው ግን ተዳፍነው የሚቆዩ የክልልነት ይገባኛል ጥያቄዎች ከየአቅጣጫው ብቅ ማለታቸው አልቀረም፡፡

ከክልል እስከ ወረዳና ቀበሌ የሚዘልቀው የአስተዳደር ይገባኛል ጥያቄና ውዝግብ የመንግሥት መዋቀር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ተያይዞ ከሚነሳ የማንነት ጥያቄ ጋር ጎን ለጎን የሚሄድ የሕዝቦች እንቅስቃሴ መሆኑን ማወቅ ግድ ይለናል፡፡ ከዚህ አልፎም በክልል ድንበር አካባቢ የሚገኙ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና ሕዝቦች በየትኛው ክልል ይጠቃለሉ የሚለው ጉዳይም በክልሎች መካከል ያልተቋጩና ውስብስብ የማንነት ንትርክ ከመፍጠራቸው ባሻገር በየጊዜው ለዜጎች ይወት ማለፍና መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል፡፡

የሃያ ስድስት መት ዕድሜ ያለው የአገራችን ፌዴራሊዝም በክልሎች አወሳሰን ላይ ምንም ይነት የማሻሻያ ርምጃ ሳይወስድ የወረዳ የልዩ ወረዳ የዞንና የልዩ ዞን ጥያቄዎች ላይ ብቻ መጠነኛ ማስተካከያዎችን እያደረገ እስካሁን ቀጥሏል፡፡ የክልልነት ይገባኛል ጥያቄዎች እንዳሉ ቢታወቅም ከሕገ መንግሥቱ ደቅ አንስቶ የነበረው የክልሎች ቁጥር አልተቀየረም፡፡

በዚህ ሁኔታ ነው እንግዲህ ብሔርን ረት ያደረገው ፌዴራሊዝማችን 20ኛውን ተሻግሮ ወደ 21ኛ ክፍለ ዘመን ከመድረስ ባሻገር አሥርት መቁጠር የጀመረው፡፡ ከላይ ለማስቀመጥ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም የስኬትና የግድፈት ፉርጎዎችን አጣምሮ በአንድ ላይ በመያዝ የሚምዘገዘግ ባቡር ይመስላል፡፡ የስኬት ፉርጎዎች ለባቡሩ ፍጥነትና ምቾት አስፈላጊ በመሆናቸው ማብዛትና ይዘን መቆየት እንደሚኖርብን ሁሉ የግድፈት ፉርጎዎችን ቢቻል መጠገንየማይቻል ሲሆን ደግሞ ለተሳፋሪውና ለባቡሩ ንነት ሲባል ተወግደው መተካት ይኖርባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አስተዳደርና የሲቪል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ

ስለአገራችን ፌዴራላዊ አስተዳደር ሥርዓት ስናነሳ ከጥንስሱ አንስቶ እስካሁን ድረስ አብሮት የዘለቀውን የመድ ፓርቲ ሥርዓት በዚህ ሥርዓትም ብቸኛ ልጣን ተቆናጣጭ መሆን የቻለውን የገዥ ፓርቲዎች ስብስብን ማንሳት ግድ ይላል፡፡ ይህ ስብስብ የዘጠኙም ክልላት ምክር ቤቶችንና ክልላዊ አስተዳደሮችን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠሩ ዘጠኝ ፓርቲዎች የተዋቀረ ሲሆን አስኳሉ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልጣን ምንጭ የሆነውን የተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ድም በጋራ የያዙ አራት ፓርቲዎች  ያቋቋሙት ግንባር ነው፡፡ ከግንባሩ ውጭ ያሉ የገዥ ፓርቲ ስብስብ አባላት በተለምዶ አጋሮች በሚል ስያሜ ሲጠሩ ከክልላዊ መንግሥት ባሻገር በተወሰነ ደረጃ የፌዴራል መንግሥት ልጣን ሲካፈሉ ይስተዋላል፡፡ በአጭሩ ሪፐብሊካችን ውስጥ በየርከኑ ያሉ አውጪና አስፈ አካላት ሙሉ በሙሉ በግንባሩና አጋሮቹ የበላይነት የተዋቀረ እንደሆነ እናያለን፡፡

የገዥ ፓርቲዎች ስብስብ ልክ እንደ ፌዴራል ሥርዓታችን ሁሉ በዋነኛነት ብሔርን ረት ያደረገ መዋ መርጧል፡፡ ይህም በመሆኑ ከፌዴራል ሥርዓቱ በቀጥታ የሚወርሰው ወጥነት የጎደለው መርህ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በክልል አወቃቀር ላይ የታየው ወጥ ያልሆነ መርህ በገዥ ፓርቲው ስብስብም በግልጽ ይስተዋላል፡፡ በአንዳንድ አካባቢ ከፍተኛ የተወላጅ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች በራሳቸው ተደራጅተው የራሳቸውን ፓርቲ መሥርተው የፖለቲካውን ሜዳ ሲቀላቀሉ ሌሎች ተመሳሳይ ወይም አብላጫ የተወላጅ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች ይህን ድል በገዥ ፓርቲ በኩል ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከግንባሩ ጋር በአጋርነት የተለፉ ድርጅቶች ምንም ያህል ታማኝና ላማ አንድነት ቢኖራቸውም ከአጋርነት አልፈው አስኳል መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ወደ አስኳልነት የሚቀይራቸውም ራር እስካሁን አልተቀረ፡፡

ጥንታዊ የሕዝቦች ትስርና ፍልሰትን ባስተናገደችው አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰብ ተወላጆች በተለያየ የታሪክና ይወት አጋጣሚዎች ምክንያት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በማቅናት ኑሯቸውን መሥርተው መኖር ከጀመሩ ትውልዶች ተቆጥረዋል፡፡ የሕዝቦች ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና ኑሮ የመመሥ መብት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 31 ረት ጥበቃ የሚደረግለት በመሆኑ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያም አያሌ ዜጎች ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመንቀሳቀስ ሕይወታቸውን መሥርተው ይገኛሉ፡፡  በዚህ ምክንያት በዘጠኙም ክልሎች ውስጥ የክልሉ ገዥ ፓርቲ የማይወክላቸው ኢትዮጵያውያን በብዛት ከመገኘታቸው በላይ፣ በክልላቸውና በፌዴራል መንግሥት ውስጥ ፋይዳ ባለው ደረጃ ድምቸውን የማሰማት መብታቸው ትልቅ እክል አጋጥሞታል፡፡

ሕዝቦች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀሳቸውና በተለይም ከከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ወሰን ሳይኖራቸው በመቀላቀል ይማኖት ባህል ቋንቋቸውን ተካፍለዋል፡፡ በተወላጆች መካከልም ከእልፍ መታት የዘለቀ እርስ በርስ መጋባትና መዋለድ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጉራማይሌ ብሔር ሕዝብ ተፈጥሯል፡፡ ይህ ሕዝብ ከማንነቱ የተወሰነውን ብቻ መርጦ ካልሆነ በስተቀር ሙሉ ማንነቱን ይዞ የዚህ ብሔር ተወላጅ ነኝ ማለት የማይችል ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ሙሉ ማንነቱን አስጠብቆ የገዥ ፓርቲው ስብስብን መቀላቀል የማይችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የዚህ ሕዝብ ሙሉ ማንነት የሚወከለው ኢትዮጵያዊነት በሚለው ጥላ ሥር ብቻ ሲሆን ይህን ይዞ በፖለቲካው ውስጥ የራሱን አሻራ ማሳደር የሚችለውም በክልላዊ ወይም ብሔር ተኮር ሳይሆን በአገራዊ ፓርቲ ሲታቀፍ ነው፡፡

ከብሔር ተኮር አደረጃጀት በተጨማሪ ብረ ብሔራዊ ቅር የያዘ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በአገራችን የተፈቀደና አያሌ አቀንቃኞችን ያፈራ ሆኖ ሳለ ይህን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረግ የፖለቲካ ዳሩን የተቀላቀለው ከገዥ ፓርቲ ስብስብ ያለው የሲቪል ፖለቲካዊ በረሰብ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህ በረሰብ ከደርግ ውድቀት ማግሥት አንስቶ በግለሰብበብሔርና፣ ብረ ብሔር ቅር ሰፊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረግ በአንድ ወቅት ገዥ ፓርቲን የመገዳደር አቋም ላይ መድረስ ሲችል በሌላ ጊዜ ደግሞ ያለ እስካይመስል ድረስ በጭላንጭል ብቻ ተወስኖ ቆይቷል፡፡  በአጠቃላይ ከገዥ ፓርቲ ስብስብ ያለው የሲቪል ፖለቲካዊ በረሰብ  በፌዴራል ሥርዓቱ በማናቸውም ደረጃ ልጣን ባለቤት መሆን ባይችልም በተለያዩ ጊዜያት የክልልና የፌዴራል አውጪ አካላትን በአናሳነት ለመቀላቀል የበቃበት ሁኔታ ነበር፡፡ ባለፉት ሁለት ምርጫዎች ደግሞ ይህ ቁጥር ከማሽቆልቆል አልፎ በማዕከላዊም ሆነ በክልል ደረጃ  ያለው ውክልና ፈጽሞ ጠፍቷል፡፡

የአገራችን ሲቪል ፖለቲካ እንቅስቃሴ ለምን አሁን ያለበት አቋም ላይ እንደ ደረሰ ለማስረዳት የሚደረገው ክርክር በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎቹ በሚቀርቡ የሰማይና የምድር ያህል ልዩነትና ተቃርኖ ባላቸው የመከራከሪያ ነጥቦች የተሞላ ነው፡፡ በተከራካሪዎች በኩል ስሜታዊነትን ከሚጭሩ ጉዳዮች መካከል በመሆኑና ከዚህም አን በዚህ አንድ አንቀጽ ወይም አንድ ክፍል ብቻ አመክንዮአዊ ትንተና ለመስጠት ከመሞከር በሌላ ልመለስበት ቃል በመግባት በሁለቱም ወገን የሰላ ሳብ ፍጭት ተደርጎ አገራዊ መግባባት ላይ ካልደረስንባቸው አያሌ ጉዳዮች ተርታ መድበን ወደሚቀጥለው ክፍል እንለፍ፡፡

ብሔርን መረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ማብቂያው መቼ ነው?

      ለም የፌዴራሊዝም ሥርዓትን በመገንባትና ለአስተዳደር በማዋል አገራችን ኢትዮጵያ ከአርፋጆች ቢሆን እንጂ ከቀዳሚዎች የምትመደብ አገር አይደለችም፡፡ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ፣ ንድ፣ አውስትራሊያ ካናዳን የመሳሰሉ ግዙፍ ዴሞክራሲዎች ከምዕተ መታት በፊት ይህን የመንግሥት አወቃቀር የተገበሩ ሲሆን ከፍተኛ ስብጥር ያለውን ሕዝባቸውን በአንድነት ጠብቀው ለምዕተ መታት የዘለቀ ጉዞ ማድረግ  በመቻላቸው የፌዴራሊዝም ስኬት ማሳያ ተደርገው ይወሳሉ፡፡  በአን ደግሞ የባልካን አገሮች ጥምረት የነበረው የዩጎዝላቪያ ፌዴራሊዝም ስኬታማነቱን ጠብቆ መቀጠል አቅቶት ለመበታተንና ለእርስ በርስ ጦርነት መዳረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡

ፌዴራሊዝም እንደ ኢትዮጵያ ውስብስብ የሆነ የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊና በራዊ ትስ ላላቸው ሕዝቦች አመቺ የሆነ የመንግሥት መዋቅር መሆኑ ባይካድም አንድ አገር የፌዴራል ሥርዓትን በመከተሏ ምክንያት ብቻ የአገሪቱም ሆነ የሕዝቧ ጥቅም ይከበራል ማለት አይደለም፡፡ የፌዴራል ሥርዓት ሲገነባ የዜጎችን አብሮነት የሚያበለግና በውስጡ ያሉ ክልሎችን ለአንድ ብሔራዊ ህልውና የሚያልፍ መንገድ ካልተከተለ ደት የአገሪቱን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥ ክፍፍል ፈንታው ሊሆን ይችላል፡፡

የአገራችን ፌዴራል ሥርዓትም ይህ አደጋ በተወሰነ መልኩ እንዳንዣበበት ለመረዳት በየጊዜው በክልሎችና በብሔሮች መካከል የሚነሱ የማንነት፣ የድንበርና ልጣን ጥያቄዎች ማሳያ ይሆናሉ፡፡ የፌዴራል ሥርዓታችን ብሔርን ረት ያደረገ በመሆኑም የሚነሱ ግጭቶች በአካባቢያዊ አስተዳደሮች መካከል የተደረጉ ብቻ ሳይሆኑ፣ በብሔሮች ብሎም በሕዝቦች መካከል የተደረጉ ቅራኔዎች የሚሆኑበት ድል ይፈጠራል፡፡ ልጣን ላይ ያለው የፓርቲዎች ስብስብም እንዲሁ ብሔርን ረት ያደረገ መዋቀር የሚከተል ነውና በብሔሮች መካከል የሚፈጠር ቅራኔ ወዲያውኑ በአባል ፓርቲዎች መካከል የሚፈጠር ቅራኔን መጫሩ አይቀርም፡፡

አስተዳደራዊ ግጭቶች አስተዳደራዊ መፍት ይሻሉ፡፡  የብሔር ግጭቶች ግን አስተዳደራዊ ወይም ይል መፍትዎች ብቻ በዘላቂነት መፍታት አይቻልም፡፡ ይልቁንም ከመንግሥት የሚመጡ መፍትዎች እንደ ባዕድ የሚቆጠሩና ግጭትን የሚያባብሱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በመንግሥትና በፓርቲ አወቃቀር ላይ የሚታየው ብሔርን ረት ያደረገ ሽንሸና፣ በብሔሮች መካከል ለሚፈጠር ግጭት ከመፍትነቱ ይልቅ መንስነቱ ያመዝናል፡፡ የአንድ አገር ሕዝብ ዘር ቆጥሮና ብሔር ለይቶ የገባበት ግጭት ውጤቱ እንደማያምር ለማስረዳት 1990ዎቹ መጀመሪያ በሩዋንዳና በቦስንያ ሄርጎቪኒያ የተከሰቱ የብሔር ግጭቶችንና ነዚህ አገሮች የተከሰቱትን በራዊ ኢኮኖሚያዊና ከምንም በላይ ደግሞ ልቦናዊ ጠባሳዎችን በምሳሌነት መጥቀስ እንችላለን፡፡ በአጭሩ ይህ ይነት ጦስ ለአገራችን አይደለም ለጠላታችን የማንመኘው ነው፡፡

ይህን በማየት ብሔርን ረት ያደረገው ፌዴራሊዝማችንና ይህንንም የሚተገብረው ብሔር ተኮር የፖለቲካ ጥምረት የች አካልና መነሻ መሆኑን መገንዘብና ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ አካሄዱን አገራዊ ማንነት ላይ ባተኮረ ፍልስፍና የሚቀይርበት ጊዜ ደርሷል ለማለት እደፍራለ፡፡ እስካሁን የሄድንበት መንገድ ያስመዘገባቸውን ማናቸውንም ይነት ድሎች ሳንጥል የወደፊት ፈንታችን በወንድማማችነታችንና አብሮና ተከባብሮ የጋራ ማንነትን በማበል ላይ መሥርተን የብሔር ግጭትና መቃቃርን ታሪክ ርገን ማስቀረት ይኖርብናል፡፡ ይህም ላፊነት በቅድ የአገራችንን ሁለንተናዊ ጉዞን በመምራት ላይ የሚገኘው የገዥ ፓርቲዎች ስብስብ ላይ ይወድቃል፡፡

ማጠቃለያ

የሲቪል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በተፈቀደባቸውና ይህ መብት በተገደበባቸው ወይም በተከለከለባቸው አገሮች ሳይቀር ዜጎች የተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶችን አንስተው ይነጋገራሉ፡፡ ሳብ ልዩነቶችና አንድነቶች በዚህ ደት ውስጥ የሚከሰቱ ተፈጥሮ ሁነቶች ናቸው፡፡ አንዲት አገር በውስጧ ባሉ የፖለቲካ ይሎች መካከል መፈጠራቸው የማይቀረውን ሳብ ልዩነቶች የምታስተናግድበትና የምትፈታበት ጥበብ የራሷን ሁለንተናዊ ፈንታ የሚወስን ደት ነው፡፡ በዚህ ለመዳሰስ የሞከርኩት 1983 ዓ.ም. ጀምሮ በተግባር ላይ ስላዋልነው ብሔርን ረት ያደረገ የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀር ሲሆን ለአገራችን ያስገኛቸውን ጥቅሞችን ሳንክድ በአፈጻጸምም ይሁን በርዕ ዓለም ደረጃ ጉዳታቸው ያመዘኑ ጉዳዮችን ነቅሰን በማውጣት መጠገን ካልሆነም መቀየር ይኖርብናል የሚለውን ጭብጥ ነው፡፡ ፍሬ ነገሩ ብሔርን ረት ያደረገ ሽንሸና እንጂ ፌዴራሊዝም የችግሩ ምንጭ አለመሆኑንም ለማስረዳት የቀረበ ትንተና ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ያልተዳሰሱና በበቂ ሁኔታ ያልተብራሩ ርዕሶች እንደሚኖሩ አልጠራጠርም፡፡ ባይን በጭልፋ ይነት ሊባልም ይችላል፡፡ ወደፊት ከየወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር እያስታከኩ አስተያየቶቼን እንደምሰጥ ተስፋ አደርጋለ፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...