‹‹አታሞውን ምታው
አርገው ደምቧ ደምቧ
እንደወለደች ላም
አታሰኘው እምቧ፡፡›› ይባላል ለበዓል ክብር፣ ለክተት ስሪት ነጋሪት ሲመታ:: መቺውን ለማትጋት የሚወረወር ቃል ነው፡፡ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ጥር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲከበር ከባሕረ ጥምቀት አንዱ በነበረው ጃንሜዳ በአራት ኪሎ በኩል ወደየአጥቢያቸው ያለፉትን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ፣ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ታቦተ ሕግ በታላቅ አጀብ ከዘለቁት ምዕመናን ጋር ከተሰለፉት ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ነጋሪት ሲሆን፣ ሌሎቹ እነ በገና፣ እምቢልታ፣ ጥሩምባ ወዘተም በዐውደ ጉዞው ታይተዋል፡፡
***