ሊቢያ ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች በመጀመርያው ዙር 21 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ምሽት ከትሪፖሊ ሊመለሱ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፣ ተመላሾቹ ዛሬ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ይደርሳሉ፡፡
በቀጣዩ ዙር 45 ዜጎች ከትሪፖሊና ከቤንጋዚ የጉዞ ሰነድ ተሰጥቶአቸው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ዝግጅት መጠናቀቁን ጽሕፈት ቤቱ ገልጾ፣ ዜጎችን ከሊቢያ ለመመለስ የተጀመረው ጥረት ከዓለም የስደተኞች ድርጅት ጋር መንግሥት ባደረገው ቅንጅት መሆኑን አስታውቋል፡፡