አስፈላጊ ነገሮች
Ø ዶሮ
Ø ሽንኩርት
Ø በርበሬ
Ø ዘይት
Ø ቅቤ
Ø ነጭ ሽንኩርት እና ዝንጅብል (የተፈጨ )
Ø የተቀቀለ እንቁላል ( ተቀቅሎ የተላጠ )
Ø ኮረሪማ
Ø ሎሚ ( ለዶሮው ማጠቢያ )
Ø ጨው
አሠራር
Ø ውኃ ተለቅ ባለ ድስት ማፍላት
Ø ዶሮውን ካረዱ በኋላ የፈላው ውሃ ውስጥ እየነከሩ ላባውን በሚገባ ማፅዳት
Ø በሚገባ ከታጠበ በኋላ ቆዳውን መላጥና ብልቶቹን ገነጣጥሎ ማውጣት
Ø የተገነጣላውን ብልት በሎሚና በጨው ለ 30 ደቂቃ ያህል መዘፍዘፍ
Ø ሽንኩርቱን በርከት አድርጎ ልጦ አድቅቆ መክተፍ እና ተለቅ ባለ ድስት መጣድ
Ø ሽንኩርቱ ውኃውን እንደጨረሰ ዘይትና በርበሬ እንዳስፈላጊነቱ መጨመርና እያማሰሉም በደንብ ማብሰል
Ø ኮረሪማ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብሉን መጨመር፣ ውኃም ጠብ እያረጉ የሽንኩርቱ ቅርፅ እስኪጠፋ ማቁላላት
Ø የተዘፈዘፈውን ዶሮ በደንብ ማጠብና አጥንቶቹን ማስተካከል፣ሥጋውንም ሠንጠቅ ሠንጠቅ ማድረግ
Ø ከዚያም በንፁህ ውኃ አለቅልቆና ውኃውን አድርቆ ቁሌቱ ላይ መጨመር
Ø ቅቤ እንዳስፈላጊነቱ ከተደረገ በኋላ ሥጋውን ከቁሌቱ ጋር በደንብ ማሸት፣ እንዲሁም ለመረቁ የሞቀ ውኃ መጥኖ መጨመር
Ø ሥጋው በሚገባ ከበሰለና መረቁ ከተስተካከለ በኋላ የተላጠውን እንቁላል ሰንጠቅ ሰንጠቅ አርጎ ማስገባት ጨዉንም አስተካክሎ ማውጣት
– ሰዋስው ‹‹ባህላዊ ምግቦችና አሠራራቸው›› (2008)