ኒው ዚላንድ የሚለው ስም የተገኘው በኔዘርላንድስ ከሚገኝ ዚላንድ የተባለ አካባቢ ነው። በማኦሪ ቋንቋ አዎቴያሮአ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ‹‹ረጃጅም ነጭ ደመናዎች የሞሉበት አገር›› የሚል ትርጉም አለው። ኒው ዚላንድ እንግዳ የሆኑ የዱር እንስሳት የሚገኙባት አገር ስትሆን መብረር በማይችሉ አእዋፍ ዝርያዎች ብዛት ረገድ የትኛውም የዓለም ክፍል አይወዳደራትም። ቱዋታራ በመባል የሚታወቀው እንሽላሊት መሰል እንስሳም የሚገኘው በኒው ዚላንድ ነው፤ ይህ በደረቱ የሚሳብ ፍጡር እስከ መቶ ዓመት ድረስ ሊኖር ይችላል!
በአገሪቱ ውስጥ ካሉት አጥቢ እንስሳት መካከል በሌላ በየትኛውም አገር የማይገኙት፣ የተወሰኑ የሌሊት ወፍ ዝርያዎችና እንደ ዓሣ ነባሪዎችና ዶልፊኖች ያሉ አንዳንድ ትላልቅ የባሕር አጥቢዎች ብቻ ናቸው።
- ንቁ! (2017)