Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ንብረት ወደ መጋዘን አሽሽተዋል የተባሉ ተከሳሽ በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው

የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ንብረት ወደ መጋዘን አሽሽተዋል የተባሉ ተከሳሽ በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው

ቀን:

  • ንብረቱን በመደበቅ የተጠረጠሩ ተከሳሽ በ100 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ

ከአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ዕቃ ማከማቻ መጋዘን ውስጥ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ንብረቶች በአንድ አይሱዙ በመጫን በመጋዘን ውስጥ መደበቃቸው የተረጋገጠባቸው ተከሳሽ፣ በአንድ ዓመት ከአራት ወራት እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ፡፡ ቅጣት የተጣለባቸው ተከሳሽ አቶ አብዮት ከድር የሚባሉ ሲሆን፣ ያጓጓዙትን ንብረት በመጋዘናቸው ውስጥ ደብቀዋል ተብለው እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጥላሁን ታደሰ ደግሞ፣ የ100 ሺሕ ብር ዋስ አስይዘው በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ቅጣት የተጣለባቸው አቶ አብዮት ጉዳያቸው የታየውና ጥፋተኛ የተባሉት በሌሉበት ነው፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ክሱን ሲመረምር ከርሞ፣ ፍርደኛው የባለሥልጣኑ ንብረት የሆነውን ዕቃ በአንድ አይሱዙ መኪና ጭነው በአቶ ጥላሁን ታደሰ መጋዘን ማራገፋቸው ወንጀል ሕግ ቁጥር 677(1) ሥር የተደነገገውን መተላለፋቸው በመረጋገጡ፣ ጥፋተኛ እንዳላቸው ፍርድ ቤቱ በፍርዱ ገልጿል፡፡

ፍርደኛው ጥፋተኛ ከተባሉ በኋላ ዓቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ እንዳለው ተጠይቆ እንደገለጸው፣ የወንጀል ደረጃው ከፍተኛ እንዲባልለትና ሌሎችን ያስተምራል የተባለውን ቅጣት እንዲቀጡ ጠይቋል፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ክሱን ሲመረምር፣ በአንድ አይሱዙ የተሞላ ንብረት በመጋዘን ተራግፎ በመገኘቱ፣ በኤግዚቢትነት የተያዘ ከመሆኑ አንፃር የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው ሊባል ስለማይችል ‹‹መካከለኛ›› መባል አለበት ብሏል፡፡ ድርጊቱን የፈጸሙት ለሁለት በመሆኑ በግብረ አበርነት የተፈጸመ ወንጀል በመሆኑ፣ ለዓቃቤ ሕግ አንድ የክስ ማክበጃ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 84(1) መሠረት እንደተያዘለት ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ አቶ አብዮት ከድርን ያርማቸዋል፣ ሌሎችን ያስተምራል ብሎ ያመነበትን በአንድ ዓመት ከአራት ወር ቅጣት እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጥቶ፣ ፖሊስ እስረኛውን በማፈላለግ ቅጣቱን እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በመጋዘናቸው ውስጥ የባለሥልጣኑ ንብረት ተደብቆ በመገኘቱ ‹‹ተከላከሉ›› የተባሉት አቶ ጥላሁን ታደሰ፣ በወንጀል ሕግ ቁጥር 683 መሠረት መሆኑን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ሲያመለክቱ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ተከሳሹ ዋስትና ቢፈቀድላቸው ቀርበው የክርክር ሒደቱን ይፈጽማሉ የሚል እምነት እንደሌለው አስረድቶ፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67(ሀ) መሠረት ዋስትና እንዳይፈቀድላቸው መቃወሙን አስታውሷል፡፡

ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግ ተቃውሞ ‹‹አግባብ ነው አይደለም?›› ተከሳሹ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67(ሀ) መሠረት ግዴታውን ሊፈጽም ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለውን መመርመሩን አስረድቷል፡፡ የተጠቀሰው አንቀጽ ተከሳሽ ግዴታውን ሊፈጽም አይችልም ተብሎ ‹‹ሲገመት›› ዋስትና ሊከለከል እንደሚገባ በግልጽ መደንገጉን ጠቁሟል፡፡ ነገር ግን ‹‹ግምት›› የሚለው ቃል ካለው የትርጉም ስፋት አንፃር ተከሳሹ ግዴታውን ሊፈጽም አይችልም ለማለት በቂ መንደርደሪያ ምክንያቶች ሊኖር እንደሚገባም ገልጿል፡፡ ‹‹ግምት›› የሚለው በሰፊው ከተተረጎመ ሕግ አውጪው የዋስትና መብት ሊከለክላቸው ያልፈለገውን ተከሳሾች፣ የዋስ መብት እንዲከለከሉ መንገድ እንደሚከፍትና ሕጉም የታቀደለትን ዓላማና ግብ እንዳይመታ በትርጉም እንዲዘጋ ስለሚያደርግ፣ በአግባቡ መተርጎም እንዳለበት ፍርድ ቤቱ በብይኑ አብራርቷል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ፣ ‹‹ተከሳሽ ጥፋተኛ ቢባል ሊቀጣ ከሚችለው ቅጣት ክብደትና ይከላከል ከመባሉ አንፃር በዋስ ቢለቀቅ ግዴታውን አክብሮ ሊቀርብ አይችልም፤›› በማለት ዋስትና የተቃወመበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ በበቂ ሁኔታ ያላስረዳ መሆኑን ተንትኗል፡፡ በመሆኑም ተከሳሹ በዋስ እንዲፈቱ በሙሉ ድምፅ ብይን መስጠቱን ፍርድ ቤቱ አክሏል፡፡

በመሆኑም አቶ ጥላሁን ታደሰ የሚተዳደሩት በንግድ ሥራ መሆኑንና ካፒታላቸውም 500 ሺሕ ብር እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ በመግለጻቸው፣ የ100 ሺሕ ብር ዋስትና አስይዘው ከእስር እንዲፈቱና የመከላከያ ምስክሮቻቸውን በውጭ ሆነው እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡፡ የባለሥልጣኑን ንብረት በመውሰድና በመሰወር ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት አቶ ተሾመ አበበ፣ አቶ ጎርፉ ጠንክር፣ አቶ ተሻለ ገነነ፣ አቶ ወርቁ ሙለታ፣ አቶ ማንደፍሮ ጌታቸው፣ አቶ ሲሳይ ኃይሌ፣ አቶ መኮንን ተመስገንና አቶ መስፍን ይትባረክ በብይን በነፃ መለቀቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...

ወዘተ

ገና! ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤ ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ። በዳዴ ዘመኔም፣ በ'ወፌ ቆመችም!'፤ አውዴ ክፉ ነበር...