Thursday, May 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየጤናው ዘርፍ ጫናዎችን በ2030 ለመግታት

የጤናው ዘርፍ ጫናዎችን በ2030 ለመግታት

ቀን:

ኢትዮጵያ የኤችአይቪ ኤድስን፣ የወባንና የቲቢን ሥርጭት ለመግታት እየሠራች ሲሆን፣ እስካሁን በተሠሩ ሥራዎችም ለውጥ መታየታቸውን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይናገራል፡፡ ሆኖም እነዚህ ተላላፊ በሽታዎች አሁንም የጤናው ዘርፍ ጫና ናቸው፡፡

በአገሪቱ ከቀዳሚዎቹ ገዳይ በሽታዎች በሁለተኛ ደረጃ ከሚገኘው ኤችአይቪ ኤድስ ጋር 722,000 ሰዎች አብረው እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ በዓለም የቲቢ ጫና ካለባቸው አገሮች ኢትዮጵያ በዘጠነኛ ደረጃ ስትገኝ፣ የቲቢ መድኃኒት የተላመደ ቲቢና የቲቢና ኤችአይቪ ጫና ካለባቸው ቀዳሚዎቹ 30 አገሮችም አንዷ ናት፡፡ በዓመትም ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ የወባ በሽታ ይመዘገባል፡፡

ይህንን ለመከላከልና እ.ኤ.አ. በ2030 ሥርጭቱን ለማጥፋት ለሚሠራው ሥራ ግን ኢትዮጵያ ብቻ የምትይዘው በጀት በቂ አይደለም፡፡ በመሆኑም መንግሥት ከሚበጅተው በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ዕርዳታ ማግኘቱም ወሳኝ ነው፡፡

- Advertisement -

ሰሞኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ወርቁ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫም፣ ግሎባል ፈንድ ኤችአይቪ ኤድስን፣ ወባንና ቲቢ በሽታዎችን ለመከላከል የ379 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማግኘቷን አስታውቀዋል፡፡

ገንዘቡም እ.ኤ.አ. ከ2018 እስከ 2021 ባሉት ዓመታት ቲቢን፣ ወባንና ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል ይውላል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከግሎባል ፈንድ ከፍተኛ ዕርዳታ ከሚያገኙ ቀዳሚ አገሮች አንዷ ናት፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2002 እስከ 2017 ኤችአይቪ ኤድስ፣ ወባንና ቲቪን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ሕክምና ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷንም የሚኒስቴሩ መግለጫ ያሳያል፡፡

ዶ/ር ከበደ እንደሚሉትም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚመድበው በጀትና ከአጋር ድርጅቶች በሚገኘው ዕርዳታ፣ ጉልህ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡፡ የሕፃናት ሞት ቀንሷል፣ የኤችአይቪ ኤድስ፣ የቲቢንና የወባ ቁጥጥርን ማጠናከር ተችሏል፣ ሕክምናና ክብካቤ ተጠናክሯል እንዲሁም የእናቶችን ጤና ማሻሻል ተችሏል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2002 እስከ 2017 በነበሩት ዓመታትም ከኤችአይቪ ኤድስ ጋር የተያያዘ ሞትን በ70 በመቶ፣ ከቲቢ ጋር የተያያዘ ሞትን በ36 በመቶ እንዲሁም ከወባ ጋር የተያያዘ መሞትን በ80 በመቶ መቀነስ ተችሏል፡፡

በ2017 ማብቂያ 431,431 ሰዎች የፀረ ኤድስ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች የቲቢ ሕክምና ያገኙ ሲሆን፣ 90 ሚሊዮን አጎበር ወባማ በሆኑ አካባቢዎች መሠራጨታቸው ተነግሯል፡፡

ከ2015 እስከ 2017 በነበረው የትግበራ ጊዜም፣ መንግሥት ግሎባል ፈንድና ሌሎች አጋሮች ባደረጉት ኢንቨስትመንት እ.ኤ.አ. በ2014፣ 333,000 የነበረው የፀረ ኤድስ መድኃኒት ሽፋን በ2017 ወደ 431,431 በማደግ የ30 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት የ2016 ግሎባል ሪፖርት ደግሞ ከ2010 እስከ 2015 በወባ የመያዝና የመሞት ሁኔታ 50 በመቶ መቀነሱን አስፍሯል፡፡ አያይዞም 25 ሚሊዮን አጎበር መሠራጨቱን ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በቲቪ፣ በኤችአይቪና በወባ መከላከል ዙሪያ ከራሷ በጀትና ከዕርዳታ ሰጪዎች በምታገኘው ለውጥ ብታስመዘግብም፣ ፕሮግራሞችን በአግባቡ በመምራት በኩል ችግሮች አሉባት፡፡ ሚኒስቴሩ ያሠራጨው መግለጫ እንደሚያሳየውም፣ በግዥና አቅርቦት አስተዳደር፣ በፕሮግራም መምራት፣ የዕርዳታ ገንዘብን በማወራረድና ደረጃውን የጠበቀና የተሟላ ሪፖርት በማቅረብ በኩል ክፍተት ታይቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...