Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እስከ ሰኔ መጨረሻ 32 ሺሕ የጋራ ቤቶች ይጠናቀቃሉ...

ከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እስከ ሰኔ መጨረሻ 32 ሺሕ የጋራ ቤቶች ይጠናቀቃሉ አለ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ በተለያዩ ችግሮች እየተንጓተተ ቢሆንም፣ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ 32 ሺሕ ቤቶች እንደሚጠናቀቁ ተመለከተ፡፡

በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) የሚመራ ቡድን ሐሙስ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በተለያዩ ሳይቶች ጉብኝት አድርጓል፡፡

አስተዳደሩ በአጠቃላይ ከሚገነቧቸው 94,070 ቤቶች ውስጥ በመጋቢት 2010 ዓ.ም. 22 ሺሕ ቤቶችን፣ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ደግሞ 50 ሺሕ ቤቶችን የማጠናቀቅ ዕቅድ ነበረው፡፡

ነገር ግን የኮንትራክተሮችና የአማካሪ ድርጅቶች አቅም ደካማ መሆን፣ የግብዓት አቅርቦት መስተጓጎል፣ የጉልበት ሠራተኛ እጥረትና የመሳሰሉት ችግሮች ተወሳስበው በመቀጠላቸው የግንባታው ዕቅዱ እየተሳካ አይደለም ተብሏል፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ በአሁኑ ወቅት የገንዘብ አቅርቦት ችግር የለም፡፡ 20 ቢሊዮን ብር ለሁለቱ ፕሮግራሞች ተበጅቷል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት የተፋዘዙ ኮንትራክተሮችና የተፋዘዙ አማካሪዎች አሉ፡፡ ይህንን በመቀየር ሌት ከቀን መሠራት አለበት፤›› ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን በ20/80 እና በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም በአጠቃላይ 32 ሺሕ ቤቶችን ለማጠናቀቅ የዕቅድ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

መንግሥት ይፋ ባደረገው አራት የመኖሪያ ቤቶች ፕሮግራም በተለይ በ10/90፣ በ20/80 እና በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን ከ900 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ እየቆጠቡ በመጠባበቅ ላይም ይገኛሉ፡፡

በ40/60 ፕሮግራም 19 ሺሕ ተመዝጋቢዎች ሙሉ ክፍያ አጠናቀው እየጠበቁ ሲሆን፣ በ20/80 ደግሞ በ1997 ዓ.ም. ተመዝግበው የሚጠባበቁ ነዋሪዎች በርካታ ናቸው፡፡

ነገር ግን መንግሥት በዓባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ከሚገኘው ከታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ቀጠሎ ትኩረት የሰጠው ለቤቶች ልማት ነው ቢባልም፣ የመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ግን እየተንጓተተ በርካቶችንም ተስፋ እያስቆረጠ መምጣቱ እየተገለጸ ነው፡፡

መንግሥት በ2008 ዓ.ም. እና በ2009 ዓ.ም. ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ 30 ቢሊዮን ብር በጀት የያዘ ሲሆን፣ በተቀመጠው ጊዜ ግንባታውን አጠናቆ ብሩን የሚወስድ ኮንትራክተር እንኳ እየጠፋ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ የኮንትራክተሮችን ደካማነት አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው በበኩላቸው፣ የተገነቡ ሕንፃዎችን በማሳየት የኮንትራክተሮችን የተለያየ የአቅም ደረጃ አስረድተዋል፡፡

በአንድ ሳይት፣ በአንድ ቀን፣ በተለያዩ ኮንትራክተሮች የተጀመሩ ሕንፃዎች የአንደኛው ለመጠናቀቅ ሲቃረብ፣ የአንዱ ደግሞ ገና በስትራክቸር ግንባታ ላይ መሆኑን አቶ አባተ ጠቁመዋል፡፡

እነዚህን የተለያዩ አሠራሮች በማስተካከል ዕቅዱን ለማሳካት እንደሚሠራ አቶ አባተ ገልጸዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...