Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት ለፓርላማ ሲቀርብ የወንዶች ከተሳትፎ መታቀብ አነጋግሯል

  የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት ለፓርላማ ሲቀርብ የወንዶች ከተሳትፎ መታቀብ አነጋግሯል

  ቀን:

  የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት ሪፖርት ሐሙስ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በቀረበበት መደበኛ ስብሰባ፣ ሴት የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችና ክርክሮች ሲያቀርቡ ወንድ አባላት ትንፍሽ ሳይሉ ስብሰባው መጠናቀቁ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡

  በሁኔታው የተገረሙ አባላትም እርስ በርስ ሲሳሳቁ ታይተዋል፡፡ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ደምቢቱ ሐምቢሳ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ሴቶችና ሕፃናትን የሚመለከቱ በርከት ያሉ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችን ዳሰዋል፡፡ ለተነሱላቸው ጥያቄዎችም በባልደረቦቻቸው በመታገዝ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

  የዕለቱን ስብሰባ የመሩት ምክትል አፈ ጉባዔዋ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በመሆናቸው ግጥምጥሞሹም የበለጠ ፈገግ አሰኝቷል፡፡ ነገር ግን አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ በአዳማ በሚካሄደው የኦሕዴድ ማዕከላዊ ስብሰባ ተሳታፊ በመሆናቸው፣ በመደበኛ ስብሰባው አልተገኙም፡፡

  ሚኒስትሯ ሪፖርታቸውን ካቀረቡ በኋላ በሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ እምዬ ቢተው አማካይነት፣ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት የተሰበሰቡ ስምንት ጥያቄዎችና ከኅብረተሰቡ የደረሱ ተጨማሪ ስምንት ጥያቄዎች ቀርበው ነበር፡፡

  ለተነሱት ጥያቄዎች በሚኒስቴሩ አመራሮች ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ምክትል አፈ ጉባዔዋ መድረኩን ለምክር ቤቱ አባላት ለጥያቄና ውይይት ክፍት አድርገው ነበር፡፡ አሥራ ሁለት አባላት እያንዳንዳቸው ሁለትና ከዚያ በላይ የያዙ ጥያቄዎችንና ማብራርያ የሚሹ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን፣ ሁሉም ሴት የምክር ቤት አባላት ብቻ ነበሩ፡፡

  ከስብሰባው በኋላ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ ሴት የምክር ቤት አባል፣ ‹‹ጉዳዩ ለእኛም ከማስገረም አልፎ ሲያሳስቀን ነበር፤›› ብለዋል፡፡

  አሁን በሥራ ላይ ባለው አምስተኛው የፓርላማ ዘመን የሴት አባላት ቁጥር 211 ወይም 38.7 በመቶ ሲሆን፣ ካለፉት አራት የፓርላማ ዘመናት ትልቁ ተብሎ ይጠቀሳል፡፡

  ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ከዳሰሱዋቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ለዓመታት በጉዲፈቻ ወደ ወጭ አገሮች ተልከው አድራሻቸው የማይታወቁ ሕፃናት ጉዳይ ይገኝበታል፡፡ ሚኒስትሯ እንዳሉት ከ2007 ዓ.ም. በፊት በውጭ አሳዳጊዎች ከተወሰዱ ሕፃናት ውስጥ የ2,273 አድራሻቸው አይታወቅም፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የ175 ሕፃናት ወላጆች ለሚኒስቴሩ ቀርበው ያሳወቁና እንዲፈለጉላቸው የጠየቁ ናቸው፡፡

  እንዲሁም ከ1998 ዓ.ም. በፊት የተወሰዱ ሕፃናትን በተመለከተ መረጃዎች ከኮንቴይነሮች ውስጥ ሳይቀር በማፈላለግ፣ እንደ አዲስ እየተደራጁ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

  እስካሁንም በጉዲፈቻ ወደተለያዩ አገሮች የሄዱ የ5,062 ሕፃናትን መረጃ የማደራጀት ሥራ መከናወኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ‹‹የወደፊቷ ዓለም ዲጂታል ትሆናለች ሲባል ሰውን ማዕከል ማድረግ አለበት››

  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሪስ፣ በኢትዮጵያ በተካሄደው...

  መልካም ምኞት የተገለጸለት የዓለም እግር ኳስ ንጉሡ ፔሌ

  በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዘው የዓለም እግር ኳስ ንጉሡ...

  ‹‹እኔ እኮ ብቻዬን አይደለሁም››

  አንድ አዋቂ ወደ ሌላ አዋቂ መኖሪያ ሄዶ እንዲህ ብሎ...

  የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያው ምሁር ገጠመኝ

  አንድ ሰኞ ቀን ከሌጎስ አንድ ሰዓት ተኩል ብቻ የሚወስደው...