Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቅዱስ ጊዮርጊስ ለ13ኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለ13ኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነ

ቀን:

– የክለቦች የተፎካካሪነት አቅም ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል

‹‹ፕሪሚየር ሊግ›› የሚለውን ስያሜ ካገኘ ሁለት አሠርታትን ሊደፍን ከጫፍ ደርሷል፡፡ የ2008 የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱን መርሐ ግብር ሊያጠናቅቅ ሁለት ጨዋታ የቀረው አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወዲሁ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ እስካሁን ለፕሪሚየር ሊጉ ፉክክር ከተዘጋጁት 18 ዋንጫዎች የ13 ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ይኽም የክለቦችን የተፎካካሪነት አቅም ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ እያነጋገረ ይገኛል፡፡

 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በተለያየ ስያሜ ሲከናወን የቆየውን የአገሪቱን የሊግ ፉክክር መከታተላቸውን ይናገራሉ፡፡ ይህን ያህል ዓመታት በቆዩበት የአዲስ አበባ ስታዲየም ትዝብታቸው፣ እግር ኳሱ በጊዜ ሒደት ከመለወጥ ይልቅ በነበረበት እንኳ መቀጠል አለመቻሉ ያበሳጫቸዋል፡፡ አቶ እንግዳወርቅ ተገኝ የሚደግፉት ክለብ መኖሩን ባይክዱም ባለው ነገር ደስተኛ ባለመሆናቸው ማንነቱን መናገር እንደማይፈልጉ ጭምር ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የታላቋን የእግር ኳስ አገር የሊግ ስያሜ ይዞ ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ ዘንድሮ 18ኛ ዓመቱን እያገባደደ ይገኛል፡፡ የውድድር ዓመቱ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉ በተመሠረተበት ዓመት ይወዳደር የነበረው በታችኛው ሊግ ሲሆን፣ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ከተቀላቀለበት ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በ1991፣ በ1992፣ በ1994፣ በ1995፣ በ1997፣ በ1998፣ በ2000፣ በ2001፣ በ2002፣ በ2004፣ በ2006፣ በ2007 እና በ2008 የውድድር ዓመታት የሊጉን ዋንጫ አንስቷል፡፡ በ1990 እና በ1993 ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ በ1996 እና በ1999 ሐዋሳ ከነማ፣ በ2003 ኢትዮጵያ ቡናና በ2005 የውድድር ዓመት ደደቢት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻሉ ክለቦች ናቸው፡፡

ከእነዚህ ክለቦች የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሁለት ጊዜ ለማንሳት ዕድል ያገኘው ሐዋሳ ከነማ በ1999 ዓ.ም. በነበረው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በአዲስ አበባ ክለቦች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሊጉ ለሁለት በመከፈሉ ምክንያት እንደሆነ የሚናሩት አቶ እንግዳወርቅ፣ እንደ እግር ኳስ ተመልካችነታቸው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑም ሆነ ክለቦች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተለይ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ የመጣው የክለቦች የተፎካካሪነት አቅም እየወረደ መምጣት ሊያሳስባቸው እንደሚገባ ይጠቁማሉ፡፡

ምክንያቱን አስመልክቶ አስተያየት ሰጪው፣ አዲስ የውድድር ዓመት በመጣ ቁጥር እሳቸውን ጨምሮ በርካቶችን የሚያወያየው ሊጉን በአሸናፊነት ስለሚያጠናቅቀቅ ክለብ ሳይሆን በወራጅ ቀጣና ውስጥ ሆነው ስለሚዳክሩት ቡድኖች ከሆነ መሰነባቱን ጭምር ይናገራሉ፡፡ እንደ አቶ እንግዳወርቅ፣ የእግር ኳስ ቤተሰቡም ሆነ ሚዲያው ብዙውን ጊዜ በእግር ኳሱ ዙሪያ ጠንካራ ትችትና አስተያየት እያሰሙ የሚደመጠው የአገሪቱ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት ሲደርስበት እንደሆነ፣ ከዚህ በበለጠ ሊያስጨንቃቸው የሚገባው ግን ለብሔራዊ ቡድኑ መሠረት ስለሆኑት ክለቦች መሆን እንደነበረበት ያክላሉ፡፡

‹‹መሠረት የሌለው ቤት እንደማይገነባ ሁሉ ብሔራዊ ቡድን ያለክለቦች እንዴት ስኬታማ እንዲሆን ይጠበቃል?›› በማለት የሚጠይቁት አስተያየት ሰጪው፣ ቢያንስ ለእግር ኳሱ የሚፈሰውን የገንዘብ መጠን እንኳ ሊመጥን የሚችል ተሳትፎ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ነው የሚያስረዱት፡፡ እንደ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሉ በ2008 የውድድር ዓመት ብቻ የፕሪሚየር ሊጉ አካል የሆነው ሐድያ ሆሳዕና መውረዱን ያረጋገጠው ቀደም ብሎ ነው፡፡ ሁለተኛውን ወራጅ ለመለየት ግን አሁንም ሦስት ክለቦች ሥጋት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ክለቦቹም አርባ ምንጭ ከተማ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ዳሽን ሲሆኑ፣ አርባ ምንጭ ከተማ 29 ነጥብ ይዞ ኤሌክትሪክና ከዳሽን ቢራ የተሻለ ዕድል አለው፡፡ ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ከሲዳማ ቡና ከሜዳው ውጪና በሜዳው ደግሞ ድሬዳዋ ከተማን ያስተናግዳል፡፡ 26 እና 24 ነጥብ ይዘው ቀጣዩን ደረጃ የያዙት ኢትዮ ኤሌክትሪክና ዳሸን ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከሜዳው ውጪ ወላይታ ድቻንና በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ያስተናግዳል፡፡ ዳሽን ቢራ በበኩሉ፣ ከሜዳው ውጪ ከሐዋሳ ከተማና አዳማ ላይ ከአዳማ ከተማ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የፕሪሚየር ሊግ ቆይታውን የሚወስን ይሆናል፡፡ እስካሁን ባለው የደረጃ ሰንጠረዥ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ 51 ነጥብ፣ አዳማ ከተማ 42 ነጥብ፣ ኢትዮጵያ ቡና 39፣ ሲዳማ ቡና 35፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 34፣ ሐዋሳ ከተማና ወላይታ ድቻ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 34፣ ደደቢት 33፣ መከላከያ 31፣ ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ 30 ነጥብ ይዘው ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ፡፡

  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...