Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢትዮጵያና ኤርትራ ውጥረት እንዳይባባስ ተሰግቷል

የኢትዮጵያና ኤርትራ ውጥረት እንዳይባባስ ተሰግቷል

ቀን:

የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት እንዳይባባስና ወደ ጠቅላላ ጦርነት እንዳይሸጋገር ተሰግቷል፡፡ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሁለቱም አገሮች አለመግባባታቸውን በድርድር እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረበ ይገኛል፡፡

በድንበር ውዝግብ የተነሳ በ1990 ዓ.ም. ወደ ሙሉ ጦርነት የገቡት ሁለቱም ጎረቤት አገሮች፤ ከ16 ዓመታት በኋላ እንደገና ወደ ጠቅላላ ጦርነት እንዳይገቡ በብዙዎች ተሰግቷል፡፡ አሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሁለቱም አገሮች ከጦርነት እንዲታቀቡ አሳስበዋል፡፡

በአገሮቹ መካከል የቆየው ሰላምም ጦርነትም አልባ ሁኔታ ባለፈው እሑድ የተቀየረ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፆረና ድንበር አካባቢ በሁለቱም አገሮች መከላከያ ኃይሎች መካከል መደበኛ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል፡፡

አንዳንድ የሪፖርተር ምንጮች እንደሚሉት፣ ከግጭቱ በኋላ የኤርትራ መከላከያ ኃይል አንዳንድ ስትራቴጂካዊ ምሽጎችን ለቆ ወደ ኋላ ያፈገፈገ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወታደሮች ከሁለቱም ወገኖች መገደላቸው ታውቋል፡፡

ግጭቱን በትክክል ማን እንደጀመረው እስካሁን በገለልተኛ ወገን ያልተረጋገጠ ሲሆን፣ ሁለቱም አገሮች እርስ በርስ በመወነጃጀል ላይ ይገኛሉ፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ ለተሰነዘረበት ጥቃት ሲከላከል ሁለት መቶ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አባላት ተገድለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በግጭቱ ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን ባይገልጽም፣ መከላከያ ኃይሉ አስፈላጊውን የአጸፋ ምላሽ አድርሶ ወደ ቀድሞ ቦታው መመለሱን ይናገራል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱ መቋረጡ ይፋ ቢያደርግም ምንጮች እንደሚሉት ቡሬንና ፆረና ጨምሮ በተለያዩ የድንበር ግንባሮች ውጥረት መንገሱና ከባድ የጦር መሳሪያ ልውውጥ መሰማቱን ቀጥሏል፡፡

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ግጭት እንዳይባባስ ሥጋት ያደረበት ሲሆን፣ በተለይ ተመድና የአሜሪካ መንግሥት ሁለቱም አገሮች ወደ ከፋ ጦርነት ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

የተመድ ዋና ጸሐፊ ባንኪሙን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን በብራስልስ አግኝተው፤ ከኤርትራ መንግሥት ጋር ያለው ችግር በድርድርና በሰላም እንዲፈቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ ባወጣው መግለጫ ሁኔታው እጅግ እንዳሳሰበውና ሁለቱም አገሮች ቀደም ሲል የፈረሙትን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብሩ አሳስቧል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ በ1990 ዓ.ም. በድንበር ሳቢያ ወደ ሙሉ ጦርነት የገቡ ሲሆን፣ ድንበር ኮሚሽኑ የሰጠው ውሳኔ በኢትዮጵያ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...