Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን ታሰረ

ጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን ታሰረ

ቀን:

ጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይን አዛብቶ በመዘገብ በሚል በዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶበት ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት ቀርቦ ድርጊቱን መፈጸምና አለመፈጸሙን በሚመለከት ለቀረበለት ጥያቄ ድርጊቱን መፈጸሙን በማመኑ፣ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለዛሬ ቀጠሮ መስጠቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ጋዜጠኛ ሰይፉ በሸገር 102.1 በሚያስተላልፈው ‹‹ታዲያስ አዲስ›› ፕሮግራም ላይ የተዛባ ዘገባ አቀረበበት የተባለው ጉዳይ በአርቲስት ቴድሮስ ተሾመ የተሠራውና ‹‹ሦስት ማዕዘን›› የተሰኘው ፊልምን የሚመለከት ነው፡፡ በስደት ላይ የሚያተኩረውና ‹‹ፍቅር ሲበቀል›› የተሰኘው መጽሐፌ በሦስት ማዕዘን ወደ ፊልም ተቀይሮብኛል በሚል የመጽሐፉ ደራሲ አቶ አትንኩት ሙሉጌታ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 13ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክስ አቅርቦ የ10 ሚሊዮን ብር ካሳ ጠይቆ ነበር፡፡

ክሱን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በስደት ላይ ያተኮሩትን ‹‹ሦስት ማዕዘን›› ፊልምና ‹‹ፍቅር ሲበቀል›› መጽሐፍ ጭብጥን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ፊልም ሠሪዎችና ደራሲያን ማኅበር እንዲገመግሙ በማድረግ፣ ሦስቱም አካላት በፊልሙና በመጽሐፉ መካከል መመሳሰል እንደሌለ በማስታወቃቸው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችንም በመመልከት ክሱ ተገቢነት የለውም በሚል ፍርድ ቤቱ አርቲስት ቴድሮስን በመጋቢት ወር 2008 ዓ.ም. በነፃ ማሰናበቱን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ክርክሩ በፍርድ  ቤት እየተደረገ በነበረበት ወቅት ጋዜጠኛ ሠይፉ ጉዳዩን አዛብቶ ዘግቧል በሚል ከሳሽ ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ዓቃቤ ሕግ አቶ ሠይፉ ላይ ክስ መመሥረቱ ተጠቁሟል፡፡ በመሆኑም አቶ ሠይፉ ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርቦ ድርጊቱን መፈጸሙን በማመኑ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የጉለሌ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አድሮ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት ለቅጣት ውሳኔ እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ