የበርካቶችን ስሜት ከሚገዙ አገራዊ ስፖርታዊ ክንውኖች እግር ኳስ ቀዳሚውን ስፍራ ይወስዳል፡፡ ስፖርቱ ከአዝናኝነቱ ባሻገር የኢንቨስትመንት አማራጭ እየሆነ በሚገኝበት በዚህ ወቅት የብጥብጥና የሁከት መንስዔም ሆኗል፡፡ በፈረንሣይ አስተናጋጅነት እየተከናወነ ለሚገኘው የአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ይኼው ችግር በአሳሳቢነቱ እየተጠቀሰ ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይም እየተስተዋለ ያለው ክስተት ለሚመለከተው አካል ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› የሚለውን የቆየ ብሂል እያስተጋባ ይገኛል፡፡ እግር ኳስ ጨዋታዎችን ተከትሎ በሚፈጠሩ ሁከቶች አቅመ ደካሞችና ሕፃናት፣ እንዲሁም ቋሚና ተንቀሳቃሾች ንብረቶች ሳይቀር ሰለባ መሆን ከጀመሩ ወራትን አስቆጥሯል፡፡
‹‹በእንቅርት ላይ . . .›› እንዲሉ በ‹‹ነበር›› ታሪክ ብቻ ዕድገቱ የኋሊት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ እንደተቺዎች አገላለጽ፣ ከዚህ ችግሩ የሚያላቅቀው ሁነኛ መድኃኒት ያገኘ አይመስልም፡፡ በደጋፊዎች ስሜታዊነትና በስማ በለው አመራሮች መታመሱ ቀጥሎ ይገኛል፡፡
በአገሪቱ ከፍተኛው ሊግ ተብሎ የሚጠቀሰው ፕሪሚየር ሊጉ ከተመሠረተ ሁለት አሠርታት ሲያስቆጥር ለጫፍ ደርሷል፡፡ ሊጉ ስያሜውን ቀርቶ የዕድሜውን ግማሽ ያህል እንኳ መለወጥ እንዳልቻለ የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በሥሩ የሚገኙት ሊጎችም ዕድገቱን ሳይሆን ውድቀቱን፣ ‹‹መውረስ አለባችሁ›› የተባሉ እስኪመስል በየጨዋታ ሜዳው እግር ኳሱን የሁከት አውድማ እያደረጉት ለመሆናቸው ከሰሞኑ የሚታዩ እውነታዎችን ክስተቶችን ብቻ መጥቀሱ ከበቂ በላይ ስለመሆኑ የሚናገሩ አሉ፡፡
ለወትሮው አልፎ አልፎ ሲከሰት የቆየው የሜዳ ላይ የእግር ኳስ ሁከት፣ አሁን አሁን ፍፁም መልክና ይዘቱን በመቀየር ከተመልካቾች አካላዊ ጉዳት አልፎ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ሳይቀር እያሳጣ መሆኑን የሚገልጹ የእግር ኳስ ታዳሚዎች፣ የእግር ኳሱ አስተዳዳሪዎች የአመራሩ ብቃት በመንስዔነት መጠቀሱ እንደተጠበቀ ሆኖ የክለብ ደጋፊዎችና ተመልካቾች፣ የጨዋታ ዳኞችና ታዛቢዎች እንዲሁም የፀጥታ አካላትን ጭምር በተጠያቂነት ይጠቀሳሉ፡፡
ከሰሞኑ በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ባለፈው ዓርብ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ቡናና ሐዋሳ ከነማ መካከል በተደረገው ጨዋታ የተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በትልቁ ሲጠቀስ፣ በከፍተኛ ሊግና በብሔራዊ ሊግ ክለቦች ደግሞ አክሱም ላይ በአክሱም ከተማና ወልዋሎ፣ ወልዲያ ላይ በወልዲያና የአማራ ውኃ ሥራ ቡድኖች እንዲሁም በወልቂጤ ወልቂጤ ከተማና አምቦ ከተማ ሁከቱ ቀጥሏል፡፡ እንዲሁም ደቡብ ክልል ቡድኖች በሆኑት ጋርዱላና ኮንሶ ኒዎርክ ክለቦች በተመለከተ፣ የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ፣ በአካባቢው የፀጥታ ችግር መኖሩን በማሳወቁ ጨዋታው እንዳልተካሄደም ተነግሯል፡፡ ጅምሩ ያም ሆኖ ግን አሁንም የሚመለከተው አካል የመፍትሔ አቅጣጫ ሊያስቀምጥለት እንደሚገባ ነው ብዙዎች ሥጋታቸውን የሚናገሩት፡፡
ሌላው የአስተያየት ሰጪዎቹ ጥቆማ ደግሞ እግር ኳሱን በበላይነት የሚመራ አካል ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች ተጠያቂ ሊሆን የሚገባ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ምክንያቱም እስከዛሬ ድረስ እንዲህ እንዳሁኑ ችግሩ ጎልቶ ባይወጣም ከራሱ ከተቋሙ በሚፈጠሩ የአሠራር ክፍተቶች፣ እንዲሁም በጨዋታ ዳኞችና በራሳቸው በክለቦቹ ድክመት በሜዳ ላይ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ የተቋሙ አመራሮች የሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች በስማ በለው ካልሆነ እንደ ተቋም መሪ ጉዳዩን ተከታትለው አለመሆኑን በመጥቀስ ያጠናክሩታል፡፡ ለዚህም በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታዎች ሲኖሩ አንድ ወይም ሁለት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአጋጣሚ ጨዋታ ሲከታተሉ ከመታየታቸው ውጪ፣ ብዙዎቹ ጨዋታዎቹን እንደማይከታተሉ ጭምር ይገልጻሉ፡፡
በመጨረሻም ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ ክስተቱ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የቦርድ ሊቀመንበር መቶ አለቃ ፍቃዱ ማሞ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑን መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ ‹‹በእግር ኳስ የዳኞች ስህተት ሊኖር ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለዚህ ዓይነቱ ረብሻ ምክንያት ሊሆን አይገባም፤›› ማለታቸውም በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲነገር ተደምጧል፡፡ ጅምሩ ያሳሰበው የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በበኩሉ የፌዴሬሽኑን አመራሮች በመጥራት ማነጋገሩ ታውቋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ውሳኔውን ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
እግር ኳሱ የሁከት መንስዔ መሆኑ ለምን?
በደረጀ ጠገናው