Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነትና በኮሚዩኒኬሽን አራት አዳዲስ ፕሮግራሞችን ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነትና በኮሚዩኒኬሽን አራት አዳዲስ ፕሮግራሞችን ሊጀምር ነው

ቀን:

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት በ2009 የትምህርት ዘመን አዳዲስ ፕሮግራሞችን እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ ትምህርት ቤቱ የሚጀምራቸው አዳዲስ ፕሮግራሞች፣ በዶክትሬት ዲግሪ ‹‹ፒኤችዲ ኢን ሚዲያ ኤንድ ኮሚዩኒኬሽን ስተዲስ››፣ በማስተርስ (ድኅረ ምረቃ) ፕሮግራም ‹‹ኤምኤ ኢን ፐብሊክ ሪሌሽንስ ኤንድ ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን፣ እንዲሁም በመጀመርያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ) ፕሮግራም ‹‹ቢኤ ኢን ፐብሊክ ሪሌሽንስ ኤንድ አድቨርታይዚንግ›› እና ‹‹ቢኤ ኢን ኮሚዩኒኬሽን ስተዲስ›› መሆናቸውን ሰኔ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በተዘጋጀው የአንድ ቀን ዐውደ ጥናት ላይ ተገልጿል፡፡

‹‹ፕሮግራሞቹ የተከፈቱት ከፍተኛ ፍላጎት ስላለ ነው፤›› ያሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ፣ ትምህርት ቤቱ ለአሥር ዓመታት ያህል በቅድመና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ሲያስተምር እንደቆየ፣ ነገር ግን በዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ስለማያስተምር  በዶክትሬት ዲግሪ የመቀጠል ፍላጎት ያላቸው ብዙዎቹ ባህር ማዶ ሄደው ለመማር እንደሚገደዱ፣ ይኽም በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል አነስተኛ እንዲሆን እንዳደረገና ለጆርናሊዝም ትምህርት ቤቶች ተግዳሮት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሚዲያ ኢንዱስትሪውን ለማስፋፋት ጠንካራ ምርምር ማድረግ ግድ ይላል፡፡ በዘርፉ የጠለቀ ዕውቀት ያላቸውን ባለሙያዎች ማፍራትም ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የጋዜጠኝነት ሙያን በዶክትሬት ዲግሪ የተማሩ ሰዎችን ማፍራት ዓይነተኛ መንገድ ነውም ብለዋል፡፡

‹‹ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መጠን የሚዲያው ኢንዱስትሪ እንዲሠራ ለማድረግ የጠለቀ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም በፒኤችዲ ፕሮግራም የተማሩ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ፤›› ሲሉ ዶ/ር ነገሪ የፕሮግራሞችን አስፈላጊነት አብራርተዋል፡፡

ፕሮግራሞቹን በባለሙያ ከማስገምገም ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙና ተግዳሮቶችም እንዳሉ የሚገልጹት ኃላፊው፣ ፕሮግራሞችን ለማስጀመር በቂ የሰው ኃይል ባይኖርም ባለሙያዎችን ለመቅጠር እየተንቀሳቀሱና በትምህርት ቤቱም ስድስት በፒኤችዲ ፕሮግራም የሠለጠኑ ባለሙያዎች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡ ለሚጀመሩት አዳዲስ ፕሮግራሞች የሚሆን በጀት የሚመድበውም ዩኒቨርሲቲው ሲሆን፣ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፎችን ዩኒቨርሲቲው ከውጭ ከሚያገኘው ሊጠቀም እንደሚችል ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...