Saturday, December 9, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

ክቡር ሚኒስተር

[የክቡር ሚኒስትሩ ሹፌር በጠዋት ከቤታቸው ሊወስዳቸው መጣ]

 

  • እንቅልፍ አልተኙም እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምን እንቅልፍ አለ?
  • ለምን አልተኙም?
  • ግጥሚያውን ሳይ ነዋ፡፡
  • አሸነፍን ተሸነፍን?
  • እኛ እኮ የለንበትም፡፡
  • ከተፋላሚዎቹ አንደኞቹ እኛ አይደለን እንዴ?
  • ከመቼ ጀምሮ ነው እኛ አውሮፓዊ የሆነው?
  • ስለምን እያወሩ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ስለአውሮፓ ዋንጫ ነዋ፡፡
  • እየቀለዱ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • የምን ቀልድ ነው?
  • ያመሹት እኮ ሥራ ላይ መስሎኝ?
  • በቃ በዊኬንድም አትረፉ ነው የምትሉን፡፡
  • አይ ያው ዊኬንዱ የሚታረፍበት አልነበረም ብዬ ነዋ፡፡
  • ዊኬንዱማ ሰላማዊ ነበር፡፡
  • ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገው ትተውታል ማለት ነው?
  • ሳትራገፍ ማራገፍ አይሻልም ብለህ ነው?
  • እና ምንም ወሬ አልሰሙም?
  • ያው የቤተሰብ ወሬማ ሰምቻለሁ፡፡
  • ኧረ ስለጦርነቱ፡፡
  • ስማ ጦርነት እኮ ቆሞ አያውቅም፡፡
  • የትኛው ጦርነት?
  • ከድህነት ጋር የሚደረገው ጦርነት፡፡
  • ምን አሉኝ?
  • ከሙስናና ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር የሚደረገው ጦርነት፡፡
  • ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ አሉ፡፡
  • ከመልካም አስተዳደር ጋር የሚደረገው ጦርነት፡፡
  • ከእነርሱ ጋ ግን ተዋግታችሁ ታውቃላችሁ?
  • ሌት ተቀን ነዋ፡፡
  • ታዲያ በየጊዜው ለምን እየጨመሩ ይሄዳሉ?
  • አየህ አጠቃቅህ ስትራቴጂካዊ መሆን አለበት፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • በጣም እስኪያድጉ ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ፡፡
  • ከዛስ?
  • ከዛማ ሳያስቡት ባንዴ ትገነድሳቸዋለህ፡፡
  • ግን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
  • ምን ዓይነት ጥንቃቄ?
  • እነሱ እንዳይገነድሷችሁ፡፡
  • አንተን ራስህን መገንደስ ነበር፡፡
  • ለማንኛውም እኔ የምልዎት ጦርነት ሌላ ነው፡፡
  • የምን ጦርነት ነው?
  • ከኤርትራ ጋር የነበረው ጦርነት?
  • ምን?
  • ምንም አልሰሙም?
  • የምን ጦርነት ነው?
  • የኢትዮጵያ ሠራዊት ከኤርትራ ሠራዊት ጋር ተጋጭቶ ነበር፡፡
  • በምን ምክንያት?
  • እሱን ነበር ልጠይቅዎት የነበረው፡፡
  • እሱማ አይነገርም፡፡
  • ለምን?
  • ወታደራዊ ሚስጥርን መጠበቅ አለብህ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ዋናው ችግርዎት እኮ ይኼ ነው፡፡
  • ምንድን ነው?
  • የማያውቁትን ነገር እንደሚያውቁ ሲያወሩ ነዋ፡፡
  • የግጭቱን ችግርማ አውቀዋለሁ፡፡
  • እሺ ምንድን ነው?
  • ምቀኝነት፡፡
  • ምን ማለት ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • በቃ በአገራችን ዕድገት የከፋው የኤርትራው መሪ ተመቅኝቶ ነው ውጊያ የጀመረው፡፡
  • አይ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በቃ ከዚህ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም፡፡
  • ድንቄም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን አልክ?
  • ድንቅ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለመሆኑ ፍልሚያውን ማን አሸነፈ?
  • አቻ ነው የወጣነው፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • መንግሥት ተመጣጣኝ ዕርምጃ ወስጃለሁ ነው ያለው፡፡
  • ለነገሩ ያን ምቀኛ መሪ ምን ማድረግ እንዳለብን አውቃለሁ፡፡
  • ምን ሊያደርጉት?
  • ቂጡን በሳንጃ መውጋት!

 

[ክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊያቸው ጋ ደወሉ]

  • ምን ሆነሽ ነው ሥራ ያልመጣሽው?
  • ችግር ገጥሞኝ ነው፡፡
  • የምን ችግር?
  • ሐዘን ላይ ነኝ፡፡
  • ቻንድራ ሞተ እንዴ?
  • ኧረ አልሞተም፡፡
  • ታዲያ ዛራ ሞተች?
  • ዘሩ ነው የሞተው፡፡
  • ማነው ዘሩ?
  • ጐረቤቴ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ሆኖ ነው የሞተው?
  • ዱርዬዎች ነው የገደሉት፡፡
  • ለምን ገደሉት?
  • ማጅራት መቺዎች ናቸዋ፡፡
  • ባለሀብት ነው እንዴ?
  • ባለሀብት ቢሆንማ በቪ8 ነበር የሚሄደው፡፡
  • ታዲያ እሱ በምንድን ነው የሚሄደው?
  • በቪ11፡፡
  • ቪ11 ካለውማ ከቪ8 ስለሚበልጥ ከፍተኛ ባለሀብት ነበር ማለት ነው?
  • ቪ11 እኮ ማለት በሁለት እግሩ ነው የሚሄደው ለማለት ነው፡፡
  • መቼም የማታመጪው ነገር የለም?
  • ክቡር ሚኒስትር ይኼ የዝርፊያ ጉዳይ ግን ቢታሰብበት መልካም ነው፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • ይኸው ይኼኛው እኮ በ15 ቀናት ውስጥ ሁለተኛው ሞት ነው፡፡
  • አንቺ ሰፈርሽ ሞቃዲሾ ነው እንዴ?
  • ክቡር ሚኒስትር የሥራ አጡ ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ማጅራት መምታት ሥራ ከሆነ ሰነባበተ፡፡
  • አሁን እዚህ አገር ላይ ሥራ አጣሁ የሚል ሰው ነው የሚገርመኝ?
  • ምኑ ነው የሚገርምዎት?
  • አገሪቷ በፍጥነት እያደገች ባለችበት በዚህ ወቅት ገና ከቤትሽ ስትወጪ አይደል እንዴ ሥራ የሚያገኝሽ?
  • አገር ቀየሩ እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • ማን? እኔ?
  • ታዲያ ስለየትኛው አገር ነው የሚያወሩት ብዬ ነዋ?
  • እኔ ወሬ አልወድም፣ ሥራ ብቻ ነው የምወደው፡፡
  • ለነገሩ ክቡር ሚኒስትር እነዚህ ማጅራት መቺዎች የእርስዎ አለቃ ለመሆን ስማቸው ላይ ሚኒስትር የሚለው ብቻ ነው የጐደላቸው፡፡
  • ማን ነው ስማቸው?
  • ጠቅላይ፡፡
  • ወሬማ ማን ብሎሽ?
  • ለማንኛውም የሚዘርፉትም ተደራጅተው ነው ተብሏል፡፡
  • በምን?
  • በአነስተኛና ጥቃቅን!

[ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን አስጠሩት]

  • የተመደበልንን በጀት እንዴት አየኸው?
  • ክቡር ሚኒስትር ከፍተኛ በጀት ነው፡፡
  • ጥሩ ነዋ፡፡
  • ምን ጥሩ ነው?
  • እንዴት ማለት?
  • ባለፈው ከተመደበልን በጀት 30 በመቶውን ብቻ ነው እኮ የተጠቀምነው፡፡
  • ከባለፈው ስህተታችን ትምህርት ወስደናላ፡፡
  • የባለፈው ችግራችን እኮ የአቅም ማነስ ነው፡፡
  • እኮ አሁን አቅማችንን እናጠናክራለና፡፡
  • አቅማችን እኮ ምንም አልተጠናከረም፡፡
  • የእኔ አቅም ተጠናክሯል፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • በቅርቡ የጭስ አልባ ኢንዱስትሪውን ለመቀላቀል ወስኛለሁ፡፡
  • አልገባኝም?
  • በቃ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ለመሥራት አቅጃለሁ፡፡
  • ምን?
  • ጥራቱን የጠበቀ ሆቴል ነው የምገነባው፡፡
  • ከየት አምጥተው?
  • ስነግርህ? ከሚቀጥለው በጀት ዓመት ተመላሽ የምናደርገውን ገንዘብ አይኖርም፡፡
  • ሌላስ?
  • በግሌ ያሉኝን አምስት ቤቶችም ቢቻል ከእጥፍ ለመጨመር አስቤያለሁ፡፡
  • ካልተቻለስ?
  • ቢያንስ አንድ ሦስት መጨመር አለብኝ፡፡
  • እ…
  • ከዛም ባለፈ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፉ መግባት አለብኝ፡፡
  • ምን አሉኝ?
  • መንግሥት ይኼን ሁሉ የኢንዱስትሪ ፓርክ የገነባው እኮ እኛ እንድንገባበት ነው፡፡
  • ኧረ የግል ባለሀብቶች እንዲገቡበት ነው?
  • እኛ አርዓያ መሆን አለብን፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • በተደጋጋሚ ባለሀብቶች እንዲገቡ ተጨቃጭቀን አሻፈረኝ ስላሉ እኛ ገብተን እናሳያቸዋለን፡፡
  • ለመሆኑ ገንዘቡን ከየት ነው የሚያመጡት?
  • ለጋሽ አገሮች ለመንግሥት ለዘላቂ ልማት ፕሮግራሞች በጀት መድቧል፡፡
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እኔም ለፕሮጀክቶቼ ከመንግሥት በጀት እመድብላቸዋለሁ፡፡
  • የእርስዎ ፕሮጀክቶች ምንድን ነው የሚባሉት?
  • የሚኒስትሩ የዘላቂ ልማት ፕሮግራሞች!

[ክቡር ሚኒስትሩ በፓርቲያቸው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እየተገመገሙ ነው]

  • ክቡር ሚኒስትር ምን ይሻልዎታል?
  • ልማት ነው የሚሻለኝ፡፡
  • የእርስዎ ሌብነት እኮ አሳፋሪ ሆነ፡፡
  • እኔ የሚገርመኝ እናንተ የማትሰርቁ ነው የምትመስሉት?
  • የእርስዎ ግን ባሰ፡፡
  • ምን ማስረጃ አላችሁ?
  • ይኸው በአሥሩም ክፍለ ከተማ በስምዎት ሕንፃ አለዎት፡፡
  • ቢኖረኝስ?
  • በስምንት ክፍለ ከተማ ደግሞ የመኖሪያ ቤቶች አልዎት፡፡
  • ብርቅ ነው ታዲያ? ማን የሌለው አለ?
  • ለልማቱ ፀር እየሆኑ ነው፡፡
  • ከዚህ በላይ ልማት ምን አለ?
  • እርስዎ እኮ አስለሚ እንጂ አልሚ አይደሉም፡፡
  • እንግዲህ ቃላት እየሰነጣጠቃችሁ አታደናግሩን፡፡
  • ምን ማለት ነው?
  • እኔ እስከሚገባኝ የእኔ መልማት የልማታዊ መንግሥት መገለጫ ነው፡፡
  • መንግሥት የግሉ ዘርፍ በልማቱ ውስጥ እንዲሳተፍ እኮ ነው የሚፈለገው፡፡
  • እኔም እኮ በግሌ ነው እያለማሁ ያለሁት፡፡
  • እርስዎ ግን የመንግሥት ባለሥልጣን ነዎት፡፡
  • የግል ባለሀብቱ እምቢ ሲል እኮ ነው አርዓያ መሆን አለብኝ ብዬ የተነሳሁት፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር የእርስዎ ሙስና ከመጠን ያለፈ ሆኗል፡፡
  • እኮ እኔ ምን ላድርግ?
  • በቃ እርስዎ ላይ ዕርምጃ መወሰድ አለበት፡፡
  • ኧረ እኔ በቃ ግለ ሒስ አደርጋለሁ፡፡
  • እርሱን ካደረገ ችግር የለውም፡፡
  • ሙስና በቃ ሱስ ሆኖብኛል፡፡
  • ከዚህ ሱስዎት መላቀቅ አለብዎት፡፡
  • ይቻላል?
  • በሚገባ፡፡
  • እስቲ ራሳችሁ ተላቃችሁ አሳዩኝ፡፡
  • ምን ዓይነት አስቸጋሪ ሰው ነዎት?
  • ለመጨረሻ ጊዜ የምናገረው ነገር አለ፡፡
  • ምንድን ነው እሱ?
  • ሙስና ውስጤ ነው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ በግሉ ኢንሹራንስ ዘርፍ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ ለመያዝ ያስቻለውን ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ ነው? እንዴት? አለቃዬ ዕረፍት የለው፣ እኔንም አላፈናፍን ብሎኛል። ታድለሽ። ታድለሽ? ሥራ ገደለኝ ዕረፍት አጣሁ እኮ ነው ያልኩሽ? ገብቶኛል። ምነው እኔንም...

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...