2 የበግ ምላስ – የበሬ አንድ
3 ቁንዶ በርበሬ ያልተፈጨ
6 ቀረፋ ያልተፈጨ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
1 የሾርባ ማንኪያ ኮምጣጤ
አሠራር
1. ምላሱን ፍም ላይ አስቀምጦ አምስት ደቂቃ ማቆየትና መላጥ፡፡
2. የተላጠውን ምላስ ንጹህ ውኃ ላይ መጣድና እስኪበስል ድረስ መቀቀል፡፡
3. ቁንዶ በርበሬ፣ ቀረፋ፣ ጨውና ኮምጣጤ ጨምሮ ማንተክተክ፡፡
4. ሲበስል ማውጣት፡፡
5. በተፈለገው ፎርም ቆርጦና አሳምሮ ማቅረብ፡፡
– ጽጌ ዑቁባሚኣኬል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)