Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ 347 የአቪየሽን ባለሙያዎችን ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በዲፕሎማ...

የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ 347 የአቪየሽን ባለሙያዎችን ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በዲፕሎማ አስመርቋል

ቀን:

የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ 347 የአቪየሽን ባለሙያዎችን ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በዲፕሎማ አስመርቋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ አብራሪዎች፣ 35 ቴክኒሻን፣ 43 የበረራ አስተናጋጆች እንዲሁም 244 በንግድና አገልግሎት በመስጠት ሥልጠና የወሰዱ ናቸው፡፡ ከተመራቂዎቹ ውስጥ የሩዋንዳ ዜግነት ያላቸውም ይገኙበታል፡፡

ፍለጋ

ከዛሬ ወደ – ትላንት ጉዞዬ

ለማንነቴ ወደ – ስሬ

ከቅርንጫፌ ከእንጭፍሩ

ከወደ ሰማይ – ሥሩ

በትዝታ ወደ አፈሩ

      ወደ ምድሩ

ከመሬቱም ወደ ንጥሩ

    ምግቡ

ወደ አስተዳደጉ

    መሠረቱ

ወደ ተራክቦ ዘሩ

    ጽንሱ

ከዚያማ – እንዲያ . . .!

እንዲያ! እያለ ነው

ፍሬው ጣዕሙን – የሚለየው

መጎምዘዙ ወይ ጥፍጥናው

መተለቁ ወይ ማነሱ!

ወይ መርገፉ ወይ ማፍራቱ

ወይም ሞቱ ወይ ሕይወቱ፡፡

    አዳነ ድልነሳሁ፣ ጨለማን ሰበራ፣ (1997)

********

ኬንያ በጦጣ ምክንያት አንድ ቀን ሙሉ በጨለማ ተዋጠች

ባለፈው ማክሰኞ ኬንያ ሙሉ በሙሉ በጨለማ ተውጣ እንደነበር ለዚህ ምክንያት የሆነው ድግሞ ጦጣ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በኬንያ ፓወር ዲስትሪቢውተርና ኬንጀን በሚተዳደረው ጊታሩ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ዝንጆሮ ትራንስፎርመር በማቃጠሉ 180 ሜጋ ዋት ኃይል ጠፍቷል፡፡ በዚህ ደግሞ መላ አገሪቱ ለአንድ ቀን በጨለማ ልትዋጥ ግድ ሆኗል፡፡ ‹‹ጦጣ በጊታሩ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጣሪያ ላይ ወጣ ከዚያም ትራንስፎርመር ላይ ወደቀና ትራንስፎርመሩን አቃጠለ፡፡ ይህ በጣቢያው ያሉ ማሽኖች ላይ ጫና እንዲፈጠርና እንዲቃጠሉ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በዚህ ደግሞ 180 ሜጋ ዋት ኃይል አጥተናል፤›› በማለት ኬንጀን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው በቀጣይ የሚያስተዳድራቸው የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከእንደዚህ ያለው በዱር እንስሳት ሊደርስ ከሚችል አጋጣሚ ይጠበቁ ዘንድ ደኅንነታቸውን እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል፡፡

*******

ለየት ያለ የሥራ ቅጥር ቃለመጠይቅ

ቻርልስ ሽዋብ የተባለ አንድ የአሜሪካ ኩባንያ የሥራ ማስታወቂያ አውጥቶ ለመረጣቸው ሰዎች ቃለ መጠየቅ ያረገው በአንድ ሬስቶራንት ቁርስ ላይ እንደሆነ ዘኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡ የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ዋልት ቢቲንገር ለቃለመጠይቅ የተጠሩት ባለሙያዎች የመረጡትን ዓይነት ቁርስ እንዲያዙ ካደረገ በኋላ በጎን ለአስተናጋጁ ምርጫቸውን አምጥቶ እንዲያመጣ በመንገር ምን ሊሉ እንደሚችሉ ለመመልከት መሞከሩንም ዘገባው ያብራራል፡፡ ‹‹ምርጫቸው ተቀያይሮ ሲመጣ ምን እንደሚሉ ማወቅ ስለፈለኩ ነው እንደዚያ ያደረኩት፡፡ ይበሳጫሉ፣ ግራ ይጋባሉ ወይስ እንዲሁ ነገሩን ለመረዳት ይሞክራሉ?›› በማለት በአጠቃላይ ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑና ችግሮች ሲያጋጥሙ በምን ዓይነት መንገድ ማለፍ የሚመርጡ ሰዎች ናቸው? የሚለው ለማየት እንደሚያስችለው ተናግሯል፡፡ ሥራ አስኪያጁ እንዳለው የተጠቀመው መንገድ አዕምሯቸውን ሳይሆን ልባቸውን ለመመልከት የሚያስችለው ነው፡፡ ተቀጣሪዎቹ በሕይወታቸው ትልቅ ስለሚሉት ስኬትም ይጠየቃሉ፡፡ ለዚህ የሚሰጡት መልስ የዓለም ምልክታቸው ሰፊ ነው ወይስ በራሳቸው ዙሪያ የተወሰነ ነው የሚለውን ለማወቅ እንደሚያስችልም ሥራ አስኪያጁ ይገልጻል፡፡

******

በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ የሌሊት ወፎች የተወረረች ከተማ

በአውስትራሊያ በደቡብ ዌልስ የምትገኘው ቤታሚንስ ቤይ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ የሌሊት ወፎች ተወራ እንደነበር ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ከተማዋ ባለፈው ሳምንት በባለግራጫማ ጭንቅላቶቹ የሌሊት ወፎች ስትወረር፣ ነዋሪች ከቤት ለመውጣት፣ በርና መስኮት ለመክፈት ተቸግረው ነበር፡፡ የወፎቹ ድምፅ ነዋሪዎችን ሲረብሽ እንደዋለም ዘገባው ያሳያል፡፡

ወፎቹን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረ ኃይል እንዳስታወቀው እንደዚህ ብዛት ያላቸው የሌሊት ወፎች ከዚህ ቀደም ታይቶ አይታወቅም፡፡ በመሆኑም አብዛኞቹ የከተማዋ ነዋሪዎች የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው ለመዋል ተገደው ነበር፡፡

ወፎቹን ከከተማው እንዲዋጡ ለማድረግ ጭስና ድምፅ ከመልቀቅ በተጨማሪ የከተማዋ የጓሮ አትክልቶችና ዛፎች ተጨፍጭፈዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...