Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

መቼም በአገሪቱ የሚታየው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ብዙ ሲያሳቅቀን ቆይቷል፡፡ መቼ እፎይ እንደምንል መተንበይም ከባድ ነው፡፡ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ተጠያቂ ከሆኑ ነጥቦች አንዱና ዋናው በወጪና ገቢ ንግዱ መካከል ያለው አለመመጣጠን ነው፡፡ ወደ ውጭ ከምንልካቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች የምናገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማንኪያ እንደሚሰፈር እጅግ ያነሰ ሲሆን፣ በአንፃሩ ከውጭ የምናስመጣቸው ዕቃዎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው በመሆናቸው፣ የምንዛሪ ፍላጎቱን ከፍተኛ ማድረጋቸው አሌ አይባልም፡፡

ከንግድ ባሻገር ለሥራ ጉዳይ፣ ለሕክምና፣ ሲያሰኝም ለጉብኝትና ለመሳሰሉት ጉዳዮች ወደ ውጭ የሚጓዙ ሰዎች የውጭ ምንዛሪ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የባንኮችን ደጅ መጥናት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እርግጥ ነው ነጋዴዎች ወይም በጥቅሉ አስመጪዎች በመደበኛ አካሄድ የባንክ መተማመኛ ሰነድ ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሞልተው የሚያፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ መጠን ለማሟላት ይሞክራሉ፡፡ ለሌሎች ጉዳዮች ዶላር የሚፈልገው ሰውም በራሽን እንደሚሰጥ በሚመስል አኳኋን እንደየባንኩ አሠራር የተለያየ መጠን ይለቀቅለታል፡፡ የእኔም ገጠመኝ ከዚህ ይነሳል፡፡

ከሰሞኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ውጭ መሄድ ስለነበረብኝ ለጉዞ የሚያስፈልገኝ ወጪ ለመሸፈን የሚያስችለኝ የውጭ ምንዛሪ መጠን በማስላት ለገንዘቡ የሚበቃውን የምንዛሪ መጠን በብር ይዤ ደንበኛ ወደሆንኩበት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎራ አልኩኝ፡፡ በምሄድበት አገር የሚኖረኝን የቆይታና የወጪ መጠን በማስላት ያስፈልገኛል ያልኩትን 1,500 ዶላር ጠየቅሁ፡፡

- Advertisement -

ምንም እንኳ የጠየቅሁት መጠን በእኔ ግምት አነስተኛም ቢሆንም፣ ባንኩ ግን ከ500 ዶላር በላይ እንደማይሰጠኝ አስታወቀኝ፡፡ የሚፈቀደው ይህ ብቻ ነው ተባልኩ፡፡ ወጥ አሠራር ግን አለመሆኑን ለመገንዘብ ብዙ አልፈጀብኝም፡፡ ከመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከመሳሰሉት የሚመጡ ሰዎች ስንትና ስንት ሺሕ ሲቆጠርላቸው አየሁና ይህን ለማድረግ ባንኩ የሚከተለው አሠራር እንዳለ ለማወቅ ጓጓሁ፡፡ እኔ ማግኘት የምችለው በባንኩ ከ50 ሺሕ ብር በላይ ተቀማጭ ቢኖረኝ አሊያም በባንኩ በኩል ከውጭ ገንዘብ ሲላክልኝ እንደነበር የሚያሳይ የባንክ መግለጫ ቢኖረኝ እንደሆነ ተብራራልኝ፡፡

እንግዲህ እንዲህ ያለው መጠይቅና መሥፈርት በሺሕ የሚቆጠር ዶላር ለሚሰፈርላቸው ለእነዚያ ሰዎች ስለመሥራቱ እርግጠኛ መሆን ይከብደኛል፡፡ ‹‹እገሌን አናግረው፤›› ‹‹እገሌ ፈቅዶልሃል ወይ?›› የሚሉ ጥያቄዎች የሚቀርቡበት አሠራር እያየን፣ ወጥና የማያዳላ የዶላር ጥያቄ መስተንግዶ ስለመኖሩ አጠያያቂ ነው፡፡

በአንፃሩ በዳሸን ባንክ የታዘብኩት ነገር ደግሞ አስገራሚና ተቃራኒውን የሆነ ነው፡፡ እርግጥ እዚህም ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሰዎች የሉም ብሎ መናገር ባይቻልም፣ ባንኩ ሲያደርግ የታየው ግን እንደየፈላጊው አቅም መጠን እስከ አሥር ሺሕ ዶላር ሲያቀርብ ነው፡፡

ግራሞትን የጫረውና ያልተለመደው የዳሸን ባንክ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት፣ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴልን በሰልፍ ያጣበቡ ደንበኞች የምሽቱ መግፋት ሳይበግራቸው እስከ ማታ ሦስት ሰዓት ድረስ ሆቴሉን በሠልፍ አጣበው እንዲጠባበቁ አስገድዷል፡፡ ሆኖም የባንኩ የሸራተን አካባቢ፣ የሒልተንና ሌሎች ቅርንጫፎች ግን ጥቂት መቶ ዶላሮችን እንኳ ለመመንዘር አለመቻላቸው ወይም እንደሌላቸው በመግለጽ ደንበኞችን ሲያሰናብቱ ማየትም ሌላው ግርምታዊ ክስተት ነበር፡፡

እንዲህ እያለ አንዴ ሲገኝ ሌላ ጊዜ ሲጠፋ የሚታየው የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት መዋዠቅ፣ ከዜጋው ይልቅ የውጭ ኢንቨስተሮች ሥጋት መሆኑ እየታየ ነው፡፡ በርካቶች በውጭ ምንዛሪ እጦት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት ለማድረግ ሥጋት እንዳደረባቸው ሲገልጹ እየሰማን ስለሆነ መንግሥት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ አዋጭ መንገዶችን ቀይሶ እፎይ ቢያሰኘን እያልኩ እመኛለሁ፡፡

(ማንያህልሽ አርጋው፣ ከአዲስ አበባ)

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...