የ47 ዓመቱ ሮበርት ሎንግና የ34 ዓመቷ ባለቤቱ ጄኒ የ13 ዓመቱ ወንድ ልጃቸው የጭንቅላት ካንሰር እንዳለበት አሳምነውት በስሙ ዕርዳታ ሲያሰባስቡ ሰነባብተዋል፡፡ ምንም ዓይነት የጤና ችግር የሌለበትን ልጃቸው ‹‹የጭንቅላት ካንሰር አለብህ›› በሚል ኅብረተሰቡ የሕክምና ወጪውን ይርዳን በሚል ሲያጭበረብሩ የቆዩት የተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ነበር፡፡ ልጁ ካንሰር ያለበት ለማስመሰል ፀጉሩን ላጭተውና የሆስፒታል ጋዋን አስለብሰው ያነሱትን ፎቶ በፌስቡክና በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ለቀዋል፡፡ ከዚህ ባሻገርም የየዕለት እንቅስቃሴውን በሚያሳዝን መልኩ አቀናብረው በመፃፍ ብዙዎች አዝነው ኪሳቸውን እንዲዳብሱ አድርገዋል፡፡ ጥንዶቹ የተደረሰባቸው ማኅበረሰቡን ለወራት ያህል ሲያጭበረብሩ ከቆዩ በኋላ መሆኑን የዘገበው ያሆ ኒውስ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስነብቧል፡፡ የልጁ አባት ሮበርትም ከደሙ ነፃ ነኝ ብሎ ባለቤቱ ላይ አሳቧል፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -