የሰማይ መላእክት ገደብ ሳለባቸው
ገፍቶም ሳት ብሏቸው ÷ ከቶም ይዞላቸው
ኪሩቤ‘ም ባይናቸው ÷ ገልጠው አሏዩዋቸው፤
ሱራፊም በእጃቸው ÷ ነቅሰው አለዩዋቸው፤
እንዳንተ ተክህኖ ÷ ዳስሶ ፈትቷቸው
አካሌን ተየእጁ ÷ ምንስ ሊያገኛቸው።
አባ! አባ! ባሉ ÷ አባ ብትኮናቸው
መንጋህ በበረቱ ÷ በሰበሰባቸው
የበግ ለምድ ለባሽ ÷ ተኵላም አይነጥቃቸው።
ባለ ወርቁ ቅብዕ ÷ ሐውልተ ስምዕህ
ጀርባውን አዙሮ ÷ ለመቅደሱ ደንብ፤
ከቅዱሱ ማዕድ ÷ መዘጋጃ ቤት
ሕዝቡ ኹሌ ይራብ ÷ ቆሞ ታጠገብ።
የብርሃን ጸዳል ከሚፈስበት
በስተ ምዕራብ ዞሮ ÷ ለትንግርት ቢያዩት፤
ከመቅደሱ ርቆ ÷ የቆመው ሐውልት
ጀርባው በኋላዉ ÷ አዝሏል መልእክት።
በትረ ኃይሉን ይዞ ÷ ግራ ዘሙ እጅ
ዓለሙን ሲገዛ ÷ ሲነዳ እጅ በእጅ
እጅህ የጣለውም ÷ ይነሣ በአዋጅ፤
ሳለ ምልክቱ ÷ ምን ጊዜም በደጅ።
ኃይለ ልዑል ካሣ
ጥር 24/2010 ዓ/ም
አዲስ አበባ