የጥንታዊ ሥልጣኔ መነሻ መሆኗ የሚነገርላት ግብፅ በውስጧ አስደናቂ ቅርሶችን ይዛለች፡፡ ከሁሉ በተለየ ሁኔታ ገኖ የወጣው የፒራሚድ ጥበቧ ደግሞ ረቂቅ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የሚታይበት፣ ዕንከን የለሽ አወቃቀሩ ደግሞ በሰዎች ሳይሆን ምጡቅ በሆኑ የሌላ ዓለም ፍጥረቶች የታነፀ ተደርጎ እንዲታሰብ ሁሉ የሚያስገድድ ነው፡፡ ፒራሚዶቿና ሌሎች ጥንታዊ ቅርሶቿ ከፍተኛ የቱሪዝም መስህብ በመሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች ወደ ግብፅ እንዲጎርፉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ቱሪዝም የግብፅ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እንዲሆን ካደረጉ ከእነዚህ ታሪካዊ ቅርሶች በተጨማሪ ከሰሞኑ ሌላ የቱሪዝም መስህብ የሚሆን ተደብቆ የቆየ መካነ መቃብር በተመራማሪዎች ተገኝቷል፡፡ 4,400 ዓመታትን ያስቆጠረው መካነ መቃብሩ ፒራሚዶች ከሚገኙበት ጊዛ ወጣ ብሎ ከሚገኝ ቦታ ነበር የተገኘው፡፡ መቃብሩ የግብፅ የአምስተኛው ሥርወ መንግሥት ንጉሣዊ ቤተሰብ የሆነች የአንዲት ሴት መቃብር እንደሆነ ባለሙያዎች መላምት ሰጥተዋል፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተው የግብፅ የጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስቴርም የአገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ የበለጠ ያጠናክራል ማለቱን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -