Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

40 ኩንታል ብርቱካን የሰረቁ ግለሰቦች ታሰሩ

ትኩስ ፅሁፎች

ሲቪላ በተባለችው ትልቋ የስፔን ከተማ ከቀናት በፊት የተከሰተ ነው፡፡ ጉዳዩ ብዙዎችን ፈገግ ያሰኘና በድርጊቱ የተሳተፉን ደግሞ ያሳሰረ ነበር፡፡ በከተማዋ ጎዳና ላይ ጥርጣሬ በሚያጭር መልኩ ሲበሩ የነበሩ ሁለት መኪኖችን አንድ ፖሊስ ያስቆማል፡፡ አንደኛውን መኪና ከኋላ ባለው ቦታ ላይ ምን ጭኖ እንደሆነ ለማወቅም ፖሊሱ የኋላውን በር ከፈተው፡፡ ወዲያውም ፈጽሞ ያልጠበቀው ነገር አጋጠመው፡፡ አለልክ ተጭነው የነበሩ የብርቱካን ፍሬዎች በተከፈተው በር ዝርግፍ ብለው ወጡ፡፡ 40 ኩንታል የሚመዝን ብርቱካን የጫኑት ሁለት መኪኖች ብርቱካኖቹን ከየት እንዳመጧቸው ቢጠየቁም ምላሽ አልሰጡም፡፡ ነገር ግን ፖሊስ ባደረገው ማጣራት ካራምና በምትባል ከተማ ከሚገኝ አንድ መጋዘን የተሰረቁ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡ በድርጊቱ የተሳተፉ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የዘገበው ዘቴሌግራፍ ነው፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች