Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልሆሎካስትን በሰባት አገር ፊልሞች

ሆሎካስትን በሰባት አገር ፊልሞች

ቀን:

አዲስ ቪዲዮ አርት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶች የተካተቱበት ፌስቲቫል ሲሆን፣ በቅርቡ የፌስቲቫሉ ሁለተኛ ዙር ተካሂዷል፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በስደትና በሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶችም ቀርበዋል፡፡ ከነዚህ ሥራዎች መካከል፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ጀርመኑ አዶልፍ ሒትለር ወደ ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያንን ያስጨፈጨፈበትን ሆሎካስት በመባል የሚታወቀውን ወቅት የተመረኮዙ የቪዲዮ ሥራ ጥበቦች ይገኙበታል፡፡

የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ወጥ ታሪክ፣ መቼትና ገፀ ባህርያት ሳያስፈልጉት አንዳች መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ ይኼንን መንገድ በመጠቀምም የተለያዩ አርቲስቶች ስለሆሎካስት የሚገልጹ ቪዲዮዎች አዘጋጅተዋል፡፡ ተመሳሳይ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ሥራዎች እንደ አዲስ ቪዲዮ አርት ባሉና በሌሎች አገሮችም በሚገኙ ፌስቲቫሎች ይታያሉ፡፡

ከቪዲዮ ሥነ ጥበብ በተጨማሪ በሆሎካስት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ዘጋቢና ፊቸር ፊልሞችም ለእይታ በቅተዋል፡፡ ‹‹ሆሎካስት›› የተሰኘው ፊልም ከናዚ ጭፍጨፋ ራሳቸውን ለማዳን ስለሚጣጣሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሚያወሳ ሲሆን፣ በሆሎካስት ዙሪያ ከተሠሩ ፊልሞች መካከል ይጠቀሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እ.ኤ.አ. በ1993 ለእይታ የበቃው ‹‹ሺንድለርስ ሊስት››፣ በ1997 የተሠራው ‹‹ላይፍ ኢዝ ቢውቲፉል›› እንዲሁም በ2002 ለተመልካች ቀርቦ በአጭር ጊዜ እውቅናን ያተረፈው ‹‹ዘ ፒያኒስት›› ተጠቃሽ ፊልሞች ናቸው፡፡

‹‹ዳያሪ ኦፍ አና ፍራንክ›› የተሰኘውን የአና ፍራንክ መጽሐፍ የተመረዞዙት ‹‹ዘ ዳያሪ ኦፍ አና ፍራንክ›› እና ‹‹አና ፍራንክ›› የተሰኙት ፊልሞችንም ማንሳት ይቻላል፡፡ የሆሎካስት ወቅት የእያንዳንዱ ቀን ውሎዋን የመዘገበችው የታዳጊዋ አና ፍራንክ መጽሐፍ አማርኛን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሟል፡፡

በአይሁዳዊና በጀመርናዊ ታዳጊዎች መካከል ያለ ጓደኝነትን የተመረኮከው ‹‹ዛ ቦይ ኢን ዘ ስትራይርድ ፒጃማስ›› የወጣው እ.ኤ.አ. በ2008 ነበር፡፡ ሞታቸውን የሚጠባበቁ አይሁዳውያን እስረኞች ፈጣሪን የሚሞግቱበት ‹‹ጋድ ኢን ትራያል›› የወጣውም በተመሳሳይ ዓመት ነበር፡፡ ሁለቱ ፊልሞች በሆሎካስት ዙሪያ ከተሠሩና አድናቆትን ከተቸሩ ፊልሞች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

‹‹ዘ ሰከንድ ሆሎካስት ሪሜምበረን›› የተሰኘው የፊልም ፌስቲቫል ባለፈው ሳምንት በጣልያን ባህል ማዕከል የተጀመረ ሲሆን፣ ለአንድ ወርም ይቆያል፡፡ የዝግጅቱ መክፈቻ የሆነው የፖላንዱ ‹‹ዘ ዙ ኪፐርስ ዋይፍ›› ነው፡፡ ፖላንድ ውስጥ የእንስሳት ማቆያ የነበራቸው ጥንዶች፣ ፖላንድ በጀርመን ስትወረር የሚገጥማቸውን ውጣ ውረድ ያሳያል፡፡ ብዙዎቹ እንስሳት በቦንብ ጥቃት ሳቢያ ሕይወታቸውን ቢያጡም ጥንዶቹ ማቆያውን ለመታደግ መጣጣራቸውን ይገፉበታል፡፡

በቀጣይ አራት ሳምንታት የሚታዩት ሰባት ፊልሞች ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ናቸው፡፡ ፊልሞቹ ባጠቃላይ በሆሎካስት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሲሆኑ፣ ወቅቱን ለማስታወስ መርሐ ግብር መሰናዳቱን አዘጋጆቹ ይገልጻሉ፡፡ ሆሎካስት በርካታ ፊልም ሠሪዎች ለፊልም ጭብጥነት ከሚመርጧቸው ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ እንደመሆኑ ብዙ ፊልሞች ተሠርተዋል፡፡

ከፊልሞቹ መካከል ‹‹ዳይ ፋልሸር›› የተሰኘው የጀርመን ፊልም በዝግጅቱ ተካቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1936 ናዚዎች ከጎናቸው የቆሙ አገሮች ኢኮኖሚ እንዲያሽቆለቁል ሲወጥኑ የሚያሳይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ  የተመሠረተ ፊልም ነው፡፡ የጣልያኑ ‹‹ሆቴል መይና›› እና የሃንጋሪው ‹‹1945›› በሚቀጥለው ሳምነት የሚታዩ ፊልሞች ናቸው፡፡

ፊልሞቹ የሚታዩት በጀርመንና በጣልያን ባህል ማዕከሎች ሲሆን፣ ከሃንጋሪ፣ ከእስራኤል፣ ከአውስትራሊያ፣ ከቼክ ሪፐብሊክ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከጣሊያን የተውጣጡ ፊልሞች ተካተዋል፡፡

‹‹1945›› በፌሬንስ ቶሪክ የተዘጋጀ የአንድ ሰዓት ተኩል ፊልም ነው፡፡ ፊልሙ መቼቱን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአንድ የሃንጋሪ መንደር ውስጥ አድርጓል፡፡ አብዛኞቹ የመንደሩ ነዋሪዎች በአንድ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ከታጎሩ በኋላ ወደ መንደሩ የሚመጡ ፀጉረ ልውጦችን በጥርጣሬ ሲመለከቱ ያስቃኛል፡፡ ለዝግጅቱ እንደተመረጡት ሰባት ፊልሞች፣ ሆሎካስት ስላደረገው ተፅዕኖ የሚያሳይ ፊልም ነው፡፡

‹‹ዘ ደት›› በተሰኘው ፊልም፣ እ.ኤ.አ. በ1965 ሦስት የሞሳድ ሰላዮች ወደ እንግሊዝ አምርተው የናዚ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ ይወስዳሉ፡፡ ከ30 ዓመታት በኋላ እርምጃቸው በግላዊ ሕይወታቸው ያስከተለውንም ፊልሙ ይስቃኛል፡፡ ፊልሙ በመጀመርያ በእስራኤላዊ አዘጋድ አሳፍ በርነስቲን የተሠራ ሲሆን፣ ከዓመታት በኋላ በእንግሊዛውያንና አሜሪካውያን ፊልም ሠሪዎች በድጋሚ ተዘግጅቶ ለእይታ በቅቷል፡፡

‹‹ኮል ሚ ዴ ጁ›› በአውስትራሊያዊ ሚካኤል ፐልፋን በርጌር የተዘጋጀ የሰማንያ ደቂቃ ፊልም ነው፡፡ በዝግጅቱ የተካተቱት ፊልሞች ለእይታ የሚበቁት ፊልሞቹ የተሠሩባቸው አገሮች በኢትዮጵያ ኢምባሲዎቻቸው አማካይነት መሆኑንም አዘጋጆቹ አሳውቀዋል፡፡

‹‹ዲቫይድድ ዊ ፎል›› የቼክ ሪፐብሊክ ፊልም ነው፡፡ በጃን ሀይብጃክ የተዘጋጀው ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ2000 ለእይታ የበቃ ሲሆን፣ በሆሎካስት ዙሪያ ከተሠሩና በመላው ዓለም ከታዩ ፊልሞች መካከል ይጠቀሳል፡፡

እንደ ሆሎካስስት ያሉ በታሪክ የማይዘነጉ ወቅቶች ለፊልም፣ መጽሐፍ፣ ሥዕልና ሌሎችም ጥበባዊ ሥራዎች መነሻ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ ለአንደ ወር የሚቆየው የፊልም ዝግጅቱ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ነገር ግን በአንደ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ፊልሞች ለእይታ የሚበቁበት ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ከአውሮፓ አገሮች የተውጣጡ ፊልሞች በኢሮፒያን ፊልም ፌስቲቫል እንዲሁም የሌሎች የዓለም ክፍሎች ጥበባዊ ውጤቶችም በተለያየ ርዕስ በጣሊያን፣ በጀርመንና በፈረንሣይ የባህል ማዕከሎች መቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ‹‹ዘ ሰከንድ ሆሎካስት ሪመምበረንስ›› እስከ ታኅሣሥ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...