Friday, June 9, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በ50 ሚሊዮን ብር በሰመራ የተገነባው የከባድ ተሽከርካሪዎች የጥገና ማዕከል ሥራ ጀመረ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ  በ50 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የከባድ ተሽከርካሪዎች የጥገና ማዕከልና የሠራተኞች መኖሪያ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።                               

ከፍተኛ የከባድ ተሽከርካሪዎች የጥገና ማዕከሉ በሚያስተናግደው የጂቡቲ መስመር ላይ ይታይ የነበረውን ችግር በማስወገድ፣ የገቢና የወጪ ንግድ ለማቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ታምኖበታል፡፡

የድርጅቱ ኃላፊዎች የጥገና ማዕከሉ ሥራ መጀመር ለአካባቢው ኅብረተሰብ ከሚፈጥረው የሥራ ዕድል በተጨማሪ፣ በብልሽት ምክንያት መንገድ ላይ የሚቆሙ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ችግርና የትራፊክ አደጋን በመቀነስ የወጪና የገቢ ንግዱን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።

ከክልሉ የሙያና ቴክኒክ ኮሌጆች ጋር ትስስር በመፍጠር ተማሪዎች የተግባር ልምምድ የሚያደርጉበትን ሁኔታ በማመቻቸት፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በማፋጠን በኩልም እንደሚያግዝም ጨምረው አስታውቀዋል።

ኃላፊዎቹ እንደገለጹት፣ ሦስት ዓመት የፈጀው የሰመራ የጥገና ማዕከል በዕቃ ማመላለስ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት ለመስጠት ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟላ ነው።

ለጥገና ማዕከሉ ሠራተኞች መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ለግንባታው ከ50 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ወጪ ሲደረግ፣ የክልሉ መንግሥት ለጥገና ማዕከሉ ግንባታ 33 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ከሊዝ ነፃ መስጠቱ ታውቋል፡፡

የጥገና ማዕከሉ አገልግሎት የሚሰጠው ለትራንስ ኢትዮጵያ፣ ለጥቁር ዓባይ፣ ለደርባ ትራንስፖርት ኩባንያዎችና ለሌሎችም ደንበኞች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በጂቡቲ መስመር የሚሰማሩ ተሽከርካሪዎች ለሰርቪስና ለድንገተኛ ብልሽት ቀደም ሲል አዲስ አበባ በመምጣት የሚያባክኑትን ጊዜና ገንዘብ እንደሚቆጥብላቸው ተገልጿል።

የሰመራ የጥገና ማዕከል ከስዊድን በመጡ ባለሙያዎች የተገጣጠመ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች አብረው እንዲሠሩ በማድረግ የዕውቀት ሽግግር መፍጠር መቻሉን ኃላፊዎቹ ገልጸዋል።

የጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት የቴክኒክ መምርያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አውራሪስ ዘውዱ፣ የሰመራ የተሽከርካሪዎች የጥገና ማዕከል አገልግሎት መጀመር የድርጅታቸው ተሽከርካሪዎች  ቀላል ብልሽት ሲያጋጥማቸውና ለሰርቪስ ከዚህ በፊት እስከ አምስት ቀናት የሚያባክኑትን ጊዜ እንደሚያስቀርላቸው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች