አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) አልፎ፣ አልፎ የተላጠና ፍሬው ወጥቶ የተከተፈ ዝኩኒ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በወፍራሙ የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
- 3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) ተከትፎ የተጠበሰ ድንች
- 1 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
- 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- 4 የተገረደፈ ቃርያ
- 2 የሻይ ማንኪያ ጨው
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማብሰል፤
- ዘይት ጨምሮ ሲቁላላ አዋዜ መጨመር፤
- ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ አዋዜውን ማቁላላት፤
- ዝኩኒውን ጨምሮ እንዳይፈርስ በዝግታ ማማሰል፤
- ዝኩኒው ከበሰለ በኋላ የተጠበሰውን ድንች መጨመርና ማንተክተክ፤
- ነጭ ሽንኩርቱን መጨመርና እሳቱን ማብሰል፤
- ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና ቃርያ ጨምሮ በማስተካከል ማውጣት፡፡
- ደብረወርቅ አባተ ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)