‹‹ጋዜጠኞች ለሁላችንም ስለአገሮቻችን፣ ስለራሳችን፣ ስለመንግሥታት እውነቱን የማወቅ ዕድል ይሰጡናል፡፡ ይህም የተሻልን እንድንሆን ያደርጉናል፡፡ ጠንካሮች ያደርጉናል፡፡ ሰሚ ላጡትም ድምፅ ይሆኗቸዋል፡፡››
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ በየዓመቱ ሚያዝያ 25 (ሜይ 3) የሚከበረውን የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀንን በማስመልከት፣ ሚያዝያ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. በኋይት ሐውስ ሦስት ጋዜጠኞችን ከሩሲያ፣ ከቬትናም እንዲሁም ከኢትዮጵያ ስመኝሽ የቆየን (ሊሊ) ባነጋገሩበትና፣ ጉልበተኛ መንግሥታትን የሚገዳደሩ ጋዜጠኞችን በዘከሩበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ፡፡